Sunday, December 9, 2012

ልጅነት፡ የዘነበ ወላ መፅሐፍ





“ይህች የምንኖርባት ዓለም እንደ ሆቴል ቤት ብንመስላት፣ በለሆቴሉ አንደዬ ነው፡፡ ያሰኘንን አዘን ልባችን የፈቀደውን ከውነን እንደሰታለን፡፡ በመጨረሻም ሒሳብ ስንል(ባንልም ጭምር) አስተናጋጁ መላከ ሞት ፀእዳ ልብሱን ተጎናፅፎ ነጭ ጓነቱን አጥልቆ በትሪ የያዘውን ደረሰኝ ያሳየናል፡፡ ደረሰኝዋም “እባክዎትን ሕይወትዎን ይክፈሉ“ ትላለች፡፡”

”ጥሩ ነው በአካል የገዘፍክ መሆን፣ ጥሩ ነው ከሳምሶን የእጥፍ እጥፍ አድገህ መገኘት፡፡ ይሁን እንጂ፣ የአካልን ግዝፈት በማንበብና በመማር ገርተህ ሕሊናህን ከአእምሮህ አዋህደኸው ተሰጥኦና ዝንባሌህን አውቀህ መጓዝ ካልቻልክ ግን እጣህ የዳይኖሰር ይሆናል፡፡ ዳይኖሰር ከሚልዮናት ዓመታት በፊት በዓለማችን ላይ የነበረ ገዙፍ እንስሳ ነበር፡፡ የአካሉን ግዝፈት፣ ከሕሊናው ብስለት ጋር አዋህዶ መምራት ባለመቻሉ ከምድረ ገፅ ጠፋ፡፡ እናንተም እንደሱ እንዳትጠፉ ማንነታችሁን ፈትሹ፡፡“
ልጅነት፡ የዘነበ ወላ መፅሐፍ

No comments:

Post a Comment