የፌስቡክና የክፍል ጓደኛየ ሄኖክ ፍቃዱ፣ የሚከተለው ዜና እውን እንደሆነ በማሰብ እንዲፅፍ በአስተማሪው ታዝዞ ነበር።የቢሆን
ዜናው «የሪያል
ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብዱን ለማሰልጠን ተስማሙ» ይላል።የስነ ፅሑፍ ችሎታው በጣም የሚያስደንቅ
ነው።በተለይ የአነባብ ክህሎቱና መረዋ ድምፁ የሃገራችን ጋዜጠኞችን ያስንቃል።የዕለቱ እስተማሪም ከሌሎች ተማሪዎችን በተለየ ከተቀመጠበት
ተነስቶ በማጨብጨብ አድናቆቱን ገልፆለታል።እስኪ እኔ ደሞ ለውድ አንባቢዎቼ «እንደ ወረደ» ላቅርብላችሁና የተሰማችሁን ሁሉ በሉ
ወይም አድርጉ።
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብዱን ለማሰልጠን
ተስማሙ
ዕለቱ አርብ ነው፣ ቀኑ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 11፣ 2013 ዓ.ም፣ ስፔን ዴ- ማድሪድ አዳራሽ።
የዓለም የስፖርት ጋዜጠኞች የተናጋሪውንና የአውሮፓ ሻምፔንስ ሊግ፣የእንግሊዝ ፕሪመር ሊግና የስፔን ላሊ ሻምፔኑን የ38 አመቱን
አሰልጣኝ ይጠብቃሉዘ። ሁሌም ከአንደበቱ አዲስ ነገር የሚፈልጉት ጋዜጠኞች መድርኩን በፈገግታ ያጅቡለታል፣ አሰልጣኝ ጆሴ ደሳንቶስ
ሞሪንሆ።
በዕለቱ ከበርካታ ጋዜጠኞች ጥያቄዎችን ከተቀበለ በኋላ ስዓቱን ተመለከተ።ከሰጣቸው ደቂቃ አንደም ማሳለፍ የማይፈልገው
አሰልጣኝ የመጨረሻ እድሉን ለአንድ ጀርመናዊ ጋዜጠኛ ሰጠ።ጥያቄውም እንዲህ ይል ነበር፣«ከ33 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ
አፍሪካ ወንጫ ያለፈችን አገር ለማሰልጠን ተስማምቷል ይባላል፣ እውነት ነው?» አለ።
በስፔን ዴ-ማድሪድ አደረሽ የነበሩ ጋዜጠኞች በሙሉ ማለት ይቻላል የስላቅ ድምፅ ያሰሙ ጀመር። የአንድ ወንድና የእንደ
ሴት ልጆች አባት የሆነውን፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ከአራት የተለያዩ ክለበቦች ጋር ከአስር ዎንጫዎችን በላይ የሰበሰበ አሰልጣኝ
ጆሴ ሞሪንሆ ግን መልሱን ከመመለሱ በፊት ፈገግ አለ።ወደ ማይኩ ጠጋ ሲልም የጥያቄውን መልስ የሚጠብቁ ጋዜኞች በአደራሹ ድምፃቸውን
አጠፋው።
«ስሟ ኢትዮጵያ ይባላል፣የብዙ አትሌቶች ማፍለቅያ ናት፣ብዙ ታሪክም አላት» ሲል ነበር ማብራረያውን የጀመረው።አንድ ኢትዮጵያዊ
ስለሃገሩ ከሚሰጠው መግለጫ የማይተናነስ በሚመሰል መልስ ንግግር አደረገ።« እግር ኳስ ወዳዱን ህዝቧን በቴለቪዥን መስኮት ብቻ ሌላ
ቡድን እየደገፉ የዓለም ዋንጫን እንዲመለከቱ ማን ገደባቸው?» ይላል ተጠያቂው አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ሲጠይቅ።
ከእንግሊዝ እስከ ስፔን፣ ከጣልያን እስከ ጀርመን፣ በተለያዩ ታላለቅ ክለቦች ሲታደን የነበረው ፣በታላላቅ የእር ኳስ
ሀያላን አገሮች «ካዝናችንን ሰብረን እናስፈርምህ» ጥያቄ የጎረፈለት የአውሮፓ ታላላቅ ዋንጫዎች በሙሉ በስሙ ያሉት፣ ቆፍጣናውና
ልዩ ሰው ነኝ ባዩ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ፣ አሁንም ልዩ ሰው መሆኑን ለማሳየት የምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር ኢትዮጵያን መርጧል።
በመጋቢት 17 ቀን፣ 2013 ዓ. ም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር ብሄራዊ ቡድኑን ለሶስት ዓመታት ለማሰልጠን ሲስማማ በሪያል
ማድሪድ በአመት ከሚያገኘው ሶስት ሚልዬን ዶላር በአራት እጥፍ ተጨማሪ ክፍያ ይቀበላል። ለስራውንም በኢስ አበባ ምድር ነሀሴ
22 ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ በይፋ ይጀምራል።
ጆሴ ሞሪንሆ እውነትም «ልዩ ነው» ባይነኝ፣ በጣም አደንቀዋሎሁ። እንደውም የእግር ኳስ ችሎታም ሆነ ፍቅር ባይኖረኝም
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያሎሁ በርሱ ምክንያት ለተወሱኑ ዓመታት የቼልሲ ጨዋታዎችን መከታተል ጀምሬ ነበር።ቅሉ ቼልስን ለቆ ወደ ጣልያን
በማምራት ኢንተር ሚላንን ማሰልጠን ሲጀምር የእግር ኳስ ስሜቴ «እንኳን ዘንቦብሽ…» ነበረና ጭራሹን አቆምኩት እንጂ።ከላይ ያነበባችሁት
የሄኖክ የቢሆን ዜና እውን ቢሆን ግን የአዲስ አበባ ስቴድዮም ቋሚ ተሰላፊ ከመሆን ወደ ኋላ አልልም ነበር።
No comments:
Post a Comment