Friday, February 12, 2016

‹‹ለአፍሪካውያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው›› አትሌት ኃይለ ገብረስላሴ


እውቁ አትሌት ኃይለ ገብረስላሴ ‹‹ለፍሪካውያን በጣም ወሳኙ ነገር ዲሞክራሲ ሳይሆን ጥሩ ገዢ ነው፤ እንዲህ ሲሆን ነው አህጉሪቱ ልትለወጥ የምትችለው፡፡ካልሆነ ግን በፍፁም ልትለወጥ አትችልም›› ያለው ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት 1,700 ሰራተኞች እንዳሉትና በሪልስቴት ጀምሮ በስፖርት ማዘውተርያ፣ ስኒማ ቤት፣ መኪና ድለላ፣ሆቴል፣ ሪዞርት፣ የቡና እርሻ እያለ በወርቅ ቁፋሮ እስከ መሰማራት እንደደረሰ የሚገልፀው አትሌቱ፣ ጋዜጠኛው የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፕርትን ጠቅሶ ‹‹በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ማድረግ ከባድ ነው፤ችግሮች ያጋጥሙሃል?›› ብሎ ሲጠይቀው፤

ይህን የሚያደርገው ብዙ ሰዎች እንደሚሉት በውጭ ሃገራት መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ ዕድል እንዳለው ነገር ግን ‹‹ይህ ሃገሬ ነው፤ እችው ነች እናቴ…በሃገሬ ኢንቨስት በማድረግ ቅድምያውን በመውሰድ ለሌሎች አርአያ መሆን እፈልጋለሁ›› ብሏል፡፡ በመቀጠልም ‹‹እናትህ መጥፎ ብትሆን አናቴ አይደለሽም ማለት ትችላለህ?›› በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሶለታል፡፡
‹‹ብዙ ሰዎች ዲሞክራሲ ያስፈልገናል ይላሉ፤ አንተ ለምን ዲሞክራሲ አያስፈልግም ትላለህ?›› የሚለው ጥያቄ ሲመልስ ‹‹እንዲህ በማለቴ አዝናለሁ፡፡በእርግጥ፣ ዲሞክራሲ ያስፈልገናል፤ነገር ግን፣ መቅደም ያለበት የትኛው ነው? ሁሌም ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ እንላለን…ግን ዲሞክራሲ በመጠኑም ቢሆን ቀንጦት ነው›› ብሏል፡፡

በ2010 ዓ.ም በሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ሊወዳደር እንደሚችል ፍንጭ የሰጠው አትሌት ሃይለ ለ25 ዓመታት ዓለምን ዞሮ ያካበተው ልምድ ቀላል እንዳልሆነና ይህንን ልምዱን ለሃገሩ በሚጠቅም መልኩ የሚያካፍለው በፕረዚዳንትነት፣ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ይሁን በሚኒስተርነት ግን ወደፊት የሚታይ ይሆናል ብሏል፡፡

ተወዳጁ አትሌት ሃይለ ገብረስላሴ ‹‹ዲሞክራሲ ለአፍሪካውያን ቅንጦት ነው›› በማለቱ ብዙ ፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ሳይበሳጩበት አልቀሩም፡፡የአንዳንዶቹን አስተያየትና ግብረመልስ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ እርሶስ ምን ይላሉ? መልካም ንባብ፡፡




5 hrs · 
ኃይሌ ገብረስላሴ ስለዴሞክራሲ ደፍሮ ትንታኔ ከሰጠ እኔም አፍሬ የጣልኳቸውን ፅሁፎች ለቃቅሜ መፀሀፍ ለማሳተም ድፍረት አገኘሁ። እዚህ አገር ችግር የፈጠረው የሚና መደበላለቅ ነው። ሀብትና ዝና ከመጣ ግራ ክንፍ፣ቀኝ ክንፍ መሀል ሜዳ፣ ሁሉም ላይ ተስልፎ ልጫወት የሚል ብዙ ነው። እኔ ኃይሌን ብሆን የምሰጠው መልስ "እኔ ሯጭ ነኝ። ስለዴሞክራሲ ከምትጠይቀኝ ስለቦስተን ማራቶን የአትሌቶች ድልድል ብትጠይቀኝ ይሻላል" ብዬ እመልስ ነበር። ብዙሀንን የሚወክል ስርአት ወክሎ ያልተሟላ ቁንፅል ምላሽ ከመስጥት ዝምታ ሙሉ መልስ ነው። ምነው ኃይሌ?! እኛ አትሌቲክስን ለቢቢሲ አላማን? ምን አሳስቶህ ነው?? ኃይሌ ሆነና ጠቀመን እንጂ "የአፍሪካ ዴሞክራሲ ምን ይመስላል? " ተብሎ ሲጠየቅ "ቀይ ነው" አለማለቱም የአትሌቲክሱን ለውጥ የሚያሳይ ማስረጃ ነው ይቺን ገንዘብና ዝናውን ተጠቅሞ ነገ ደግሞ የኔንም ስም በሌለሁበት ላለማስቀየሩ ዋስትና የለም።

Lula Lula ምነው ቢል ሀይሌ በግሩ እንጂ የሚበልጥ በሌላ ነገር አይበልጥ እዴት ከሀይሌ ጋር እራስህን ታወዳድራለህ

Tariku Semunegus እሱ የበቃኝ black label ማስታወቂያ በትልቁ በአደባባይ የለጠፈ ጊዜ ስውየው ማን እንደሆነ እራሱንም አያውቅም ገንዘብ ብቻ

ኃይሌ አልገረመኝም። ድሮም ጀግናችን የሆነው በእግሩ እንጂ በጭንቅላቱ አልነበረም። በእግር ደሞ ይሮጥበታል እንጂ አይታሰብበትም። (ከጥቂት ዓመታት በፊት ቀጥታ ስርጭት ላይ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በኢትዮጵያ መምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ላይ ያላገጡትን ልብ ይሏል።) Gemechu Merera Fana

Yoseph Ewe ህሊናውንም ከጫማው ጋር አብሮ ሳይሰቅለው የቀረ አይመስለኝም smile emoticon
ሀይሌ የተናገረውን ሰማውት። ዲሞክራሲ ለአፍሪካ ቅንጦት ነው ብሏል። ነገር ግን የሚያስፈልገን "good governance" ሳይሆን ያለው "good governor" ነው። ብዙ ሰዎች "በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር መካከል ምን ልዩነት ኖሮ ያንን ያሉ" ሲሉ አይቻለው። ልክ ነው ዲሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን መነጠል አንችልም። ሀይሌ ግን ያተኮረው ሥርዓት/system/ ላይ ሳይሆን ግለሰብ ላይ ነው። ለዚያም ይመስለኛል "የሚያስፈልገን good governor ጥሩ ገዢ/መሪ ነው" ያለው።
በእሱ እይታ ቀና የሆነ መሪ ካገኘን ዲሞክራሲ ባናገኝም አሁን ካለንበት ደረጃ መለወጥ እንችላለን ነው። ሀይሌ በተዘዋዋሪ እየነገረን ያለው አፍሪካ ለማደግ የቻይናን ኮሚኒስት ፓርቲ አካሄድ ትከተል የሚል ይመስላል smile emoticon
የሀይሌ አባባል ሌላ ያስታወሰኝ ነገር መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችን ሰብስቦ ሲነጋገር አንዱ ተናጋሪ ለመለስ "ከሥልጣን እንደማይወርዱ አውቃለው ግን የምጠይቅዎ በቅንነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ነው" ያለውን አባባል ነው። ለማንኛውም እኛ ያጣነው ዲሞክራሲም መልካም መሪም ነው። የሚያስፈልገንም ሁለቱም ነው። Abenezer B. Yisihak
 
Ethiopianism Spirit Forward In my understanding, Haile is not suggesting that we don't deserve democracy. He probably want to emphasis the huge problems Africans are facing even at the basic level.
Like · Reply · 1 · 1 hr

Abenezer B. Yisihak I think so
 
Eshetu Homa Keno Most scholars agree that democracy and good governance have symbiotic relationship. One does not follow from the other. When there is effective democracy there's good governance, and vice-versa.
Like · Reply · 59 mins
Ethiopianism Spirit Forward
Ethiopianism Spirit Forward I don't agree with the vice-versa. Democracy is a much bigger term than good governance. It is possible to have good governance without holding a single election.
 
Tibebu Sime Haile is a bull. Why on earth democracy is a luxury for us Africans ? Are we not human beings ? He probably wanted to please the TPLF bosses.
 
Dawe Nedjo እርግጠኛ ነኝ ሃይሌ ይህን ከማለቱ በፍት ፍቱን ደጋግሞ በመስታዎት አይቶ ዝንጀሮ ብር እንጂ ዲሞክራስ አያስፍልገውም ብሎ መሆን አለበት ይሄ ከፓርክ ያመለጠ ጭላዳ።

Abate Azagae ሀይሌ የታወቀ አድርባይነት የተፀናወተው ሰው ነው፡፡ ይኼንን ባህሪውን የቅንጅት አመራሮች እስርን ተከትሎ በሽምግልናው ወቅት ለታሳሪዎች በሽማግሌዎቹ የተገባውን ቃል ከፈረሙ በኋላ ሲጣሱ ፀጥ ብሏል ፡፡ ቀጥሎ በቤጂንግ ኦሎምፒክ የተናገረውን ሸምጥጦአል ፡፡

Yared Wube ሀይሌ ባርነትን አሜን ብሎ የተቀበለ የዘመናችን ሀባታም ባርያ ነዉ ሀይሌ ከዚህ በለይ ማሰብ አይችልም ዲሞክራሲ በአሰተሳሰብ የከበሩ ሰዎች የሰዉ ልጅ ዲሞክራሲያዊ መብቱ እስካለተጠበቀለት ድረስ አነደሰዉ እየኖረ አደለም ብለዉ ያምናሉ
ሀይሌ ግን በእግሩ የከበረ ስለሆነ በሚችለዉ እና በተሰጠዉ ማሰቢያ ዲሞክራሲን ለአፍሪቃ ቅንጦት ነዉ በሚል ተርጉሞታል 
ለሀይሌ የምመክረዉ ግን ሁሉም በየሞያዉ ይዋል እላለሁ:: አንድ ነገር ትዝ አለኝ ሁለት ሰዎች ቁጭ ብለዉ የሀኪም ወረፍ ይጠብቃሉ አንዱ ሲጋራ አጫሽ ነዉ ታዲያ ሌላኛዉ ሊመክረዉ ፈልጎ ወንድሜ በአለም ላይ ካለዉ ህዝብ 70 ከመቶዉ በምን ምክንያት እንደሚሞት ታዋቃለህ አለቅም ሲለዉ ሰዉየዉ እንዳንተ በሲጋራ ጦስ ነዉ ሲለዉ ሰዉየዉ በጣም ተናዶ
ሰማ ወንድሜ የቀረዉ 30 በመቶዉ በምን እንደሚሞት ታዉቃለህ ሲለዉ አይ አላቅም ልክ እንዳንተ በማያገባዉ እየገባነዉ አለዉ ይባላል!!

"ጦጣ ነኝ፤ ዴሞክራሲ ቅንጦቴ ነው! ሙዜን ስጡኝ" lol
Haile G/Selassie - A Creature resembling a human being! Hmm

Bizu Ha The likes of him such as man called Teddy Afro are just bunch of ignorants packed with words to deceive their followers but inside them, they are always after their greed and voraciousness for money, land and luxury of their own. They are not to blame though; we make them who they are today by idolizing them. We cared for them and they never do for us. Teddy Afro was in a fiesta in Seattle right during the time Oromo children blood spilling everywhere in Oromia. They all are after what they are...
Like · Reply · 4 hrs
Esayas Abebe
Esayas Abebe Teddy??? What did he do??? Please don't make a big mistake comparing him with this monkey!!!

Unlocking Chain ምን በቀደደው አፉ ነው በናትህ ኃይሌ እንደዚህ አይነት የበከተ ንግግር የተናገረው? አፉንም እንደእግሩ በርግዶ ነው እንዴ ሲሮጥ የኖረው... ለነገሩ ምን ያድርግ አላደገበት...አልኖረበት...አያነብበት.... He also said that he wanted to be politician to share his experience. He even couldn't differenciate between good governance and democracy! What a shame!

Bedasa Oda ሐይል ስንተኛ ክፍል ደርሶዋነል? ወይስ አንደወያኔ ነው
Adugna Birhanu Haile in the eyes of the people:
"Haile is the modern idiot, too stupid bunch of ignorant who lost his international personality while falling from the top to downhill, from hero to zero into his rubbish view and finally forced the Ethioian ppl for total boycott of his businesses and sanctioned to never ever talk about political and social issues."

Abdulwahid Jemal I think it is beter to have a good mind than speedy legs

Sani Kelifa What a disgrace my friend....U need a good advisor before u open ur mouth.. ...U got lost big time... from hero to zero!
I wouldn't like to comment bad on u but ur damn rubbish view forced me to do so.
Sorrrrrry!



Deginet Habte የቀድሞው ባለስልጣን እና የባለቤት አልባዋ ከተማ ደራሲ አቶ ኤርማያስ ለገሰ ሀይሌ /ስላሴን ሲገልፀው " እግሩ በሙዜም ውስጥ ይቀመጥ ጭንቅላቱ ግን ወደር የሌለው የመጨረሻ አድርባይ ነው።" ይለዋል ።ስለዚህ በአለም አደባባይ ተደጋጋሚ ድሎችን በመጎናፀፍ የሀገሩን ባንዲራ እያዉለበለበ ሀገሩን ያስጠራ መሆኑን ሳንረሳ፤ በእውነትና በእውቀት ሳይሆን ባድርባይነት በዬግዜው ለሚዘላብደው ንግግር ግን በስድብ ሳይሆን አስተሳሰቡን መቃወም ተገቢ ይመስለኛል

(እኔም የምጋራው ይህ በመጨረሻ የተሰጠው አስተያየት ነው፡፡በሙያው እናከበረዋለን…ደጋግሞ አኩርቶናልና፡፡ያለ ሙያው ገብቶ መዘባረቁን ግን የህዝብ ግንኙነት አማካሪ የሌለው መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡)


No comments:

Post a Comment