ወንድማችን አብራሃ ደስታ ለጌቶቹ ሲል ማንነቱን ከሸጠ ቀይቷል፡፡ማንነቱን የሸጣት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይሆን አይቀርም፤ ምናልባትም ለማርክ ሊሆን ይችላል፡፡ ሳስበው ሳስበው ‹‹የምሁራን ሰርትፊኬት›› ለማግኘት ማንነቱን መሸጥ ነበረበት መሰለኝ የሚፅፈው፣የሚናገረው፣የሚቃወመውና የሚደግፈው ሁሉ የጌቶቹን ፍላጎት በማጤን ነው፡፡እንዳውም ሲያስተምርም እነሱን እያሰበ ሳይሆን አይቀርም፡፡እኔ በህይወቴ እንዲህ ዓይነቱ ታዛዥ ሰው ይቅርና ለማዳ እንስሳም አይቼ አላውቅም፡፡እንስሳ የፈለገው ያህል ለማዳ ቢሆንም የማይመቸው ነገር ሲያጋጥመው መምፈራገጡ አይቀርም፡፡
የአብርሃ ታዛዥነት
በመፅሐፍ ቅዱስ ከምናውቀው የአብርሃም ብቸኛው ልጅ ከይስሐቅ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ምክንያቱም (ምስጢራዊ ትርጉም ግምት ውስጥ
ሳናስገባ) ሁለቱም የሚጨነቁት ስለሌሎች እንጂ ስለራሳቸው አይደለምና፡፡ይሁን እንጂ የይስሐቅ ታዛዥነት ለሰማያዊ ፅድቅ ሲሆን
የወንድማችን አብርሃ ግን ምድራዊ ነው( ምናልባት የአብርሃ ጌቶችም ራስህን ሽጠህ እኛን ለስልጣን ካበቃህን የአራት ኪሎ ቤተ
መንግስት ብቻ ሳይሆን ሰማያዊው ቤተ መንግስትም ትወርሳለህ ብለው ቃል በመግባት ካላሳመኑት በስተቀር)፡፡
አብርሃ ደስታ
ምድራዊና ሰማያዊ ቤተ መንግስት ትወርሳለህ ብለው ካላሳመኑት በስተቀር ‹‹በመቐለና መቀሌ ስሞች የትርጉም ልዩነት የለም›› ይላል ብየ አላምንም፤በጭራሽ፡፡ለምን ቢባል፤ መቐለ የትግርኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙ
ደግሞ ለሁለት ወይም ከሁለት በላይ ከፈለ ማለት ነው፡፡መቀሌ ግን በትግርኛ ቀርቶ በማንኛውም ቋንቋ ትርጉም የለውም፤ በአማርኛም
ጭምር፡፡ህሊናው ለሳተ፣ጤናው ለተቃወሰ፣ማንነቱን ለሸጠ ሰው ግን ልዩነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ማገናዘብ ለተሳነው ሰው ልዩነት ብሎ
ነገር የለማ፡፡ለነገሩ ማገናዘብ ቢችል ንሮ ማንነቱን አይሸጥም ነበር፡፡የአብርሃ ችግር ደግሞ ማገናዘብ እንደተሳነው አለማወቁን ነው፡፡
በመሆኑም የህን ፅሑፍ የምፅፈው አብርሃ ደስታ መሳሳቱን ላስረዳው ፈልጌ ሳይሆን ሌሎች ወገኖቼ እርሱ የፈፀመው ስህተት
ትክክል መስሏቸው እንዳይሳሳቱ ለማስገንዘብ ነው፡፡ባለማወቁ የሚሳሳት
ሰው ምንጊዜም ቢሆን ለመታረም ዝግጁ ነው፡፡ከእውቀት ማነስ ለሚሳሳቱ ሰዎች የሚያውቁ ሰዎች እንዲያስተካክሉ ሊነገሯቸው
ይገባል፡፡ምክንያቱም እንዚህ ሰዎች እየተሳሳቱ ያሉት ሆን ብለው አይደለም፤ ስለማያውቁ ነው፡፡እናም ማሳወቅ በቅንነት ለሚሳሳቱ
ሰዎች ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
እያወቁ የሚሳሳቱ፣
ሆን ብለው የሚያበላሹ ሰዎች ግን ዓላማ አላቸው፡፡ለማወቅም አይፈልጉም፣ አስተካክለው ለመናገርና ለመፃፍም ደንታ አይኖራቸውም፡፡ተናጋሪው
ማህበረሰብ ማንነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል አይፈልጉማ፡፡ይህ ደግሞ በተናጋሪው ማሕበረሰብ ያላቸው ንቀት ያሳያል፡፡ከምንም ተነስቶ
አንድን ማሕበረሰብ መናቅ ደግሞ ባዶነትን ያሳያል፡፡ባዶ የሆነ ሰው ደግሞ
ለሌሎች ይቅርና ለራሱም ደንታ የለውም፡፡እኛም ማስተካከያ እየጠየቅን ያለነው ባለማወቃቸው ለተሳሳቱ ሰዎች እንጂ
እያወቁ ለሚያበላሹ ሰዎች አይደለም፡፡እኔም ይህን ፅሑፍ እየፃፍኩ ያለሁት ሆን ብሎ ለማበላሸት ለተነሳው ድንጋይ ራስ አለመሆኑን
ይታወቅልኝ፡፡
አብርሃ ‹‹‘መቐለ’ ከማለት ‘መቀሌ’ የሚል ስም የመረጥኩበት ምክንያት እየፃኩ ያለሁት ባማርኛ ስለሆነ ነው።›› ይለናል፡፡ቋንቋ መሰረትና ስርዓት ያለው መግባብያ ነው፡፡ ቋንቋ መሰረት
አለው፤ተናጋሪ ከሌለው ሊኖር አይችልምና፡፡ቋንቋ ስርዓት አለው፤ ከስርዓት ውጪ ከተጠቀምንበት ትርጉም አይሰጥምና፡፡ትርጉም የማይሰጥ ከሆነ ደግሞ ዓላማው ይስታል ማለት ነው፤
መግባብያነቱ ይቀራል፡፡መሰረቱና ስርዓቱ የሚመነጨው ከተናጋሪው ማሕበረሰብ ነው፡፡መቐለ መሰረቱ ትግርኛ ስለሆነ ትርጉም ሊሰጥ
የሚችለው የቃሉ አጠቃቀም እንዴት እንደሆነና ምን ማለት መሆኑን ለሚያውቁ
የትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ነው፡፡
የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመቐለ ትርጉምና የአጠቃቀም ስርዓት ለማወቅ ከፈለጉ ለሚያውቁ ሰዎች መጠየቅ ይችላሉ፡፡መጠየቅ የበታችነት ምልክት ሳይሆን
የብልህነት ምልክት ነው፡፡ብልህ ሰዎች ለራሳቸው ክብር ይሰጣሉ፤ ክብራቸው ሊጠበቅ የሚችለው የሌሎች ክብር ሲጠበቅ መሆኑን
ስለሚያውቁም ከመሬት ተነስተው የሌሎች ክብር አይነኩም፡፡በመሆኑም ስለሌላው ማሕበረሰብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ልምድ፣ እምነትና ስርዓት
ወዘተ ክብር አላቸው፡፡
ስለዚህ መቐለ ትግርኛ
ስለሆነ የአማርኛና የሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎችም በፈለጉት መንገድ ሊፅፉት አይችሉም፡፡ለትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ክብር
አላቸዋ፡፡ከትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ጋር ተከባብረውና ተግባብተው መኖር ይፈልጋሏ፡፡አብርሃ ግን ለራሱም ለትግርኛ
ተናጋሪው ማሕበረሰብም ደንታ የለውም፡፡በመሆኑም መቐለ ብሎ ከመፃፍ ይልቅ መቀሌ ብሎ ይፅፋል፡፡
በትግርኛ ሲፅፍ መቐለ ብሎ ይፅፋል፤ በአማርኛ ሲፅፍ ደግሞ መቀሌ እያለ ይፅፋል፡፡
እዚጋ ልብ እንበል፡፡ አብርሃ ሆን ብሎ እያበላሸ ያለው የትግርኛ ቋንቋ
የአጠቃቀም ስርዓት ብቻ ሳይሆን የአማርኛም ጭምር ነው፡፡የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የአማርኛ አጠቃቀም በየትኛም ቦታና ጊዜ እንዲበላሽባቸው
አይፈልጉም፡፡የሌሎች ቋንቋ አጠቃቀምም እንዲበላሽ አይፈልጉም፡፡ሌላ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ተከባብረውና ተግባብተው ለመኖር እስከፈለጉ
ድረስ፡፡እናም የትግርኛ ቋንቋ የአጠቃቀም ስርዓት እንዲሽሩና ሆን ብለው እንዲያበለሹ በማድረግ የአማርኛ አጠቃቀምም እንዲሻር እያደረገ
ነው፡፡

I don't like Abreha Desta but on the issue of Mekelle he had given us brilliant explanation that we can't even oppose. Guys don't be stiff necked, Abreha can't be all the time wrong and you can't be all the time right. When Abreha writes truth you have to surrender and when he is wrong oppose him. It's so.
ReplyDeleteእኛ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ቃላት እየሰነጠቅን ከምንውል ድህነትን ምናቸንፍበት ፣ ወጣት ለስደት ወጥቶ ከሚረግፍበት ኣስተሳሰብን የሚቀይር ወይም ሙሰኞችን ወደ ልቦናቸው የሚመልስ ትምህርት ኣዘል ነገሮችን ብንወያይ ምን ኣለበት መቐለ ይበል መቀሌ ወይም መከለ በከተማዋ የእድገት፣ የባህል ኣልያም የመዋቅሯ የሚያመጣው ለውጥ ኣለ? ይልቁንስ ኣገራችን ከሚያናጋ ከተማዋን ከሚበዘብዝ ህዝቧ ከሚያናቁር ሰርጎ ገብና ሙሰኞች ኣስመልክተህ ኣንዲት ኣረፍተ ነገር በፃፍክ። 'ትበላው የላት ትከናነበው ኣማራት' ኣሉ ኣበው ። ከተማዋን እንዲህ ባለ መንገድ እቆረቆርላታለሁ የምትል ከሆነ ተሳስተሃል ኣላፊ ኣግዳሚውን ከሚያዳልጥ ወይም ያቆሻታል ብለህኣ ስበህ የሙዝ ልጣጭ ከኣስፓልት ኣንስተህላት ታውቃለህ ? ወገኛ ነህ
ReplyDelete@ asfaw gedamu..ስለ መቀሌ እና መቐለ ያለው ልዩነት ጥራት ባለው መልኩ አስፍረኋል.ይሁንና በትግሬ እና በትግራይ ያለው ልዩነትስ...
ReplyDelete