እራሱን ዶክትር ኢንጂኔር ብሎ በመሰየም ብዙዎችን ሲያጃጅል የኖረው ሳሙኤል ዘሚካኤል ባለፈው ዓርብ(ሰኔ 6/2006
ዓ.ም) ጉዱ ሲጋለጥ ብዙዎች እውነታው አይንህን ላፈር ብለውታል፡፡ ሌሎች ደሞ በአታላይ ምግባሮቹ የብዙዎችን አፍ አስከፍቶ ስለተፀዳዳባቸው
እንኳን! ወንድ ደግ አደረገ! በማለት እያመኳሹት ይገኛሉ፡፡ይህንን አጭበርባሪ ወሮ በላ ‹‹የገባው ነው፣ የጨሰ አራዳ ነው›› እያሉ
ሲያደንቁት ታዝበናል፡፡ጉቦ የማይሰጡ ወይም የማይቀበሉ፣ ንሯቸውን በቅንነት የሚገፉ ደሞ ‹‹ገገማ፣ ያልገባው ፋራ›› ይባላሉ፡፡
አንድ
በ1990ዎቹ መጨረሻ አከባቢ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተማሪ እያለሁ የጓደኞቼ ወሬ ስለ‹‹ኮስት
ኔት›› ብቻ ነበር፡፡ ስለ ትምህርትና ተያያዥ ጉዳዮች ቢወራ እንኳን እነ ቢልጌትስ፣ስቲቭ ጆብስ፣ቶማስ ኤድስንና ሌሎች የአመሪካ
ቱጃሮች የዩኒቨርሲቲ ጥናታቸው አቋርጠው እንዴት የተከበሩ ባለሃብቶች እንደሆኑ ነበር የሚወራው፡፡ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች መቅጣና
ብሎም ትምህርት አቋርጦ ለ‹‹ኮስት ኔት›› ማስመዝገብያ የሚሆን ብር ፍለጋ መባዘን የወቅቱ ፋሽን ነበር፡፡ አብዛኞቹ ጓደኞቼ በሽዎች የሚቆጠር
ብር ከዚህም ከዚያም ተበድረው የ‹‹ኮስት ኔት›› ተመዝጋቢዎች ሆነዋል፡፡
በመሆኑም እኔም ከእነርሱ ስር እንድመዘገብ ሁሌም ይወተውቱኛል፡፡ ለእኔ ግን የ‹‹ኮስት ኔቱ›› ነገር ሊዋጥልኝ አልቻለም፤
ከኣብዛኞቹ ጓደኞቼ የሚቀርብልኝ ‹‹በአጭር ጊዜ የናጠጠ ባለሃብት
ትሆናለህ›› የሚሉት ፈሊጥ ተረት ተረት መስሎ ነበር የሚሰማኝ፡፡ አንድ ቀን ታድያ አንዱ ጓደኛየ ‹‹ከአዲስ አበባ የመጡ የ‹‹ኮስት
ኔት›› ቁንጮዎች›› በሚላኖ ሆቴል ትምህርት ስለሚሰጡ አብረን እንሂድ›› ብሎ ጋበዘኝና አብረን ሄድን፡፡ የተሰበሰብንባት አዳራሽ
በጣም ጠባብ ብትሆንም በሰው ብዛት አልተጨናነቀችም፡፡ አሁን ስሙን የማላስታውሰው ከአዲስ አበባ መጣ የተባለው ሰውየ ወደ አደራሽዋ
ሲገባ ፉጨትና ጭብጨባው ቀለጠ፡፡
ሰውየውም ተመችቶታል መሰለኝ ተነስተን እንደናጨበጭብ ነግሮን ቆመን አጨበጨብን አሁን የማላስታውሳቸው የማነቃቅያ መፈክሮችና
ጥቅሶች በጋራ አልናቸው፡፡ አጨብጭቡ ተባልን፤አጨበጨብን፡፡ ከዛም ሰዎችን እንዴት ማሳመን እንደሚቻል፣ እንዴት ባለፀጋ መሆን እንደምንችልና
የኮስትኔት ተዋረዶች እየሰፉ በሄዱ ቁጥር ምን ያህል ‹‹ኮምሽን›› እንደሚገኝ አስተማረን፡፡በማሃሉ ግን እሱ ሲጮህ እንደን ጮህ
ያዘናል፡፡ የሚናገረው ቢረባም ባይረባም እንደንጮህ፣ እንድናጨበጭብና እንድናፏጭ ይወተውቱናል፡፡ አብሬያቸው እንድሄድ የጋበዙኝ ልጆች
ክንፍ አውጥተው ለብረር ብቻ ነው የቀራቸው፡፡ ወሬው በጣም ተመችቷቸው ከመጠን በላይ ስክር ብሏል፡፡እኔ ግን ዝግጅቱ እስኪያልቅ
እንኳን መታገስ ስላልቻልኩ አደራሽዋን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ከዛም ‹‹ኮስት ኔት›› ሰለሚባል ነገር በተወራ ቁጥር ቀንዷን እንደተመታች
ላም አናቴን እየነቀነቅኩ መሸሽ ሆነ ስራየ፡፡
ጓደኞቼም ‹‹በለፀጋ የመሆን ራኢና ዓላማ የለህም፣ እኛ ባለፀጎች ስንሆን የእኛ ተቀጣሪ ትሆናለህ›› ብለው ተዉኝ፡፡ይሁን
ብየ ዝም፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ግን የጓደኞቼ ራኢ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ በሽዎች የሚቆጠር ብር ከፍለው የሆነ ምንም ዋጋ
የሌለው ብርጭቆ ነገር በኪሳቸው ይዘው መዞር ሆነ ስራቸው፡፡ ያ ጠፍጣፋ ብርጭቆ ነገር ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ይወራ ነበር፡፡ ምሳሌ
‹‹ውሃ ጥም ይከላከላል፣ ዓይን ያጠራል፣ ራስ ምታትና ሌሎች በሽታዎች ይፈውሳል፣ ትምህርት ይከፍታል ወዘተ›› እውነታው ግን ያብርጭቆ
መሳይ ነገር ምንም ጥቅም የሌለው ድንጋይ ነበር፡፡በአቋራጭ የመበልፀጊያ መንግድ የተባለው ‹‹ኮስት ኔትም›› የውሃ ሽታ ሆነ ቀረ፡፡አቋራጭ
የመበለፀግ ህልም የትም ሳያደርሳቸው ተቆርጦ ቀረ፡፡
ሁለት
እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ከመድሃኒኣለምና አዲሱ ገበያ አከባቢ ወደ ፕያሳ የሚወስደው መንገድ በቀላል ባቡር መስመር
ግንባታ ምክንያት ጊዮርጊስ አከባቢ ከተዘጋ ቆይቷል፡፡ሆኖም ግን ሶስት የአማራጭ መንገዶች ነበሩ፡፡ አንዱ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን
በሚገኘው ማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ መሽሎክ ይቻላል፤ መንገድዋ በጣም ጠባብ ብትሆንም፡፡ ሁለተኛው በአፍንጮ በር በኩል በራስ መኮነን
ድሊ አድርጎ በአምፒር በኩል ፕያሳ ያደርሳል፡፡ ሶስተኛውና መደበኛው ግን በሰባራ ባቡር አድርጎ በቀድሞው ማስታወቅያ ሚኒስተር በኩል
ወደ ፕያሳ የሚወስደው ነው፡፡ ሹፌሮቹ ግን ሶስት አማራጮች ከመጠቀም ይልቅ አቋራጭ መንገድዋን ስለሚመርጡ ሁሉም ቀድመው ለማለፍ
በሚደረገው ትግል ያቺ አቋራጭ መንገድም ተዘጋግታ ታርፋለች፡፡ከዛማ በያሉበት ሆኖ ክላክስ መንፋት፣ ፍረቻ ማብራት መቁነጥነጥ ነው፡፡ሁሉም
ባቋራጭ ካሰቡበት ቦታ ለመድረስ በሚያደርጉት ትንቅንቅ አንዳቸውም ሳይነቃነቁ ተሳፋሪውን ይዘው ቁጭ ይላሉ፡፡ ማን አልፎ ማን ወደ
ኋላ ይቀራል? አማራጫቸው አንድም ሁሉም በአቋራጭ መጓዝ ነው አልያም ተዘጋግቶ ዝም፡፡
ሶስት
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ተአምራት ገለታ የሚባል ‹‹አዋቂ›› የዓለም ቁልፍ በእጁ መሆኗን በተከታዮቹ አማካኝነት በማስነገር
የአዲስ አበባ ህዝብ ማሳበዱን ይታወሳል፡፡ሰውየው እንደ ወፍ በራል፣ እንደ ንፋስ ይሰወራል፣ በአንዲት ቅፅበት በሁለት የተለያዩ
ቦታዎች ይገኛል፣ ለምፃሙን ይፈውሳል፣ የሞተውን ያስነሳል፣ ድሃውን ባለፀጋ ያደርጋል እየተባለ ሲወራለት ህዝቡም ‹‹እውነት ነው
በርሶ መጀን›› እያለ ከደመው፡፡ ጮማ አስቆረጠው ያለውን ሁሉ አስረከበው፣ ‹‹እያንጓለለ›› ተዘፈነለት፡፡በፈፀማቸው ዘግናኝ ወንጀሎች
ተከሶ እስር ተፈረደበት፡፡ አሁንም ግን ብዙ ሰዎች ‹‹አይይ አበባ ታምራትን አስሮ ማሰር አይቻለም፣ ስንሰሉን በጣጥሰው፣ የተቸነከረው
በር ሰብረው ይወጣሉ›› እያሉ ወናፈ መንፋቱን ቀጠሉበት፡፡ለወደፊትም አይታወቅም፤ታምራት ገለታም እንደ ታምራት ላይኔ ሱኳሩን ቅሞ
እንደጨረሰ ‹‹እየሱስን ተቀብሎ›› የዚች ዓለም ንሮ ምን ያደርግላችኋል፣ መጪውን ዘላለማዊ ህይወት እንድትወርሱ ንብረታችሁን ለኔ
አስረክቡኝ ሊል ይችላል፡፡
እነ መላኩ ፈንታ በሙስና ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ‹‹ ከመንግስት ባለመስማማታቸው እንጂ ሙስና ስለመፈፀሙ
አልታሰሩም›› ብለው የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ህግ አልባኞች የህጉ ልዕልና እንዲከበር አይፈልጉም፡፡ በመሆኑም ስርቆም ይታሰር፣ዋሽቶ
ወይም ተሳድቦም ይታስር ብቻ ህግ ተላልፎ የተገኘ ሁሉ መንግስት ስለጠላው ነው የታሰረውና ይፈታ ይባላል፡፡ ይህም ማለት ህገመንግስቱን
ትቶ ብዙጯሂዎች ያላቸው የፈለገው ዓይነት ወንጀል ቢፈፅሙም መፋት አለባቸው፡፡
I appreciate you Asfaw you wrote a wonderful thing. In Ethiopia just the people believe in perch i had faced a problem like you when i was in Mekelle.
ReplyDeleteThe problem of the people they want to be billionaire in short time. This come from stilling.