Tuesday, January 29, 2013

ፕሮፌሰር ? መስፍን ወልደማርያም፡ በኢትዮጵያ የረዥሙ ዓረፍተ ነገርና ነውጠኛ ስብእና የክብረ ወሰን ባለቤት???




በዓለማችን የረዥሙ ቃል  ባለቤት በደቡብ አፍሪካ  የሚነገር አፍሪካንስ(Afrikaans)የሚባል ቋንቋ ሲሆን 136 ፊደላት አሉት፡፡የዓለማችን ድንቃ ድንቆችን በዘገብ የሚታወቀው ‹Guinness Book of World Records> የዓለማችን ረዥሙ ዓረፍተ ነገር 1,288 ቃላት እንዳለውና  ክብረወሰኑም በዊሊያም  ፎለክነር እንደተያዘ ዘገቦ ነብር፡፡ ኒገል ቶም የሚባል ፀሐፊም  469,375 ቃላት ያሉት ዓረፍተ ነገር  በአራት ጥራዞችን(ቮሊሞች)ከፋፍሎ አሳትሟል ፡፡ ነገር ግን የቋንቋ ስነ ስርዓት(ገራመር)የተከተለ አይደለም፡፡

የህን አስቅኝ መረጃ እንድፅፍ ያነሳሳኝ በአዲስ ታይምስ መፂሔት ቋሚ ዓምደኛ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የፃፏቸው መጣጥፎች ካነበብኩኝ በኃላ ነው፡፡ፕሮፌሰሩ ሲፅፉ ዓረፍተ ነገሮችን በድርብ ሰረዞችን እየከፋፍሉ ይዘጓቸዋል፡፡ በፕሮፌሰሩ አፃፃፍ አራት ነጥብ የዓረፍተ ነገር መዝጊያ ሳይሆን የአንቀፅ ማሳረጊያ ነው የሚመስለው፡፡አንድ አንቀፅ ካልሞላ በስተቀር አራት ነጥብ አያስቀምጡም፡፡

እናም በሃገራችን የረዥሙ ዓረፍተ ነገር ባለቤት ፕሮፌሰር መስፍን ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ እኔ በ355 ቃላት የታጨቀ ዓረፍተ ነገር አንቢቤላቸዋለሁ…በግዕዝ ተፅፎ ያነበብኩት ረዥሙና የሚያቅለሸልሽ ዓረፍተ ነገር፡፡ በዚህና በሚመርጧቸው ዘረኛና በጭፍን ጥላቻ የታወሩ ቃላት ምክንያት አንድም ያርሳቸው መፅሐፍ ጀምሬ የጨረስኩት የለም፡፡ ለማዓርጋቸውና ዕድሜቻው የሚመጥን ስብእና የተላበሱ ሰው መስለው አይታዩኝም፡፡ በቅርቡ ስላሳተሙት ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› የሚለው መፅሐፋቸው በቁም ነገር መፂሔት ያደረጉት ቃለ መጠየቅ ሳነብ በጠያቂያቸው ላይ ሲሰነዝሯቸው የነበሩ ሃይለ ቃላት ለዓመታት የተቋጠረ ቂም እንዳላቸው ያሳብቃሉ፡፡ ጠያቂውም ግራ ሳይገባው አልቀረም የኃላኃላ ተጠያቂ  ነው የሚመስለው፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሰለአዲሱ መፅሐፋቸው የግሉ አስታየት ስንዝሮ ነበር፡፡የፕሮፌሰሩ የመልስ ምት  ግን በዱላ ቀረሽ የቃላት ውረፋ ጀምሮ የተቋጨው፡፡የመግቢያቸው ዓረፍተ ነገር ‹‹አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም›› ይላል፡፡እንግዲህ አስቡት በፕሮፌሰሩ  አባባል ከርሳቸው ወድያ አውቆ የሚፅፍም ሆነ የሚናግር በሃገራችን አበቆለም፡፡ማሳረጊያ ነጥባቸው ያየን እንደሆነም‹‹ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል! እንዲህ ያለ ሰው ስለእውቀት ለማውራት ለምን ይነሣል? ከበሽታ በቀር ምን ሌላ ይገፋፋዋል?›› ነው የሚለው፡፡ስለእውቀት የሚፅፉ ከሆነና እንደ መዓርጋቸውና ዕደሜቻው እንዲከበሩ ከፈለጉ ሰው ማክበር አለባቸው፡፡ ሌሎችን እንዳሻቸው እየተዛለፉ እንዲጨበጨብላቸው የሚጠብቁ ከሆነ በእርግጥም ጤንነት አይደለም፡፡ እንደኔ እምነት ማንኛውም ሰው ለመፃፍና ለመናገር የፕሮፌስርነት ማዓርግ እስኪሰጠው ድረስ መጠበቅ የለበትም፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ስለ ግላዊ ስሜታቸው እንጂ ስለሙሁራዊ አስተሳሰብ ደንታ የላቸውም፡፡ ስለ ስነ አመክንዮ(ሎጅክ)ምንም አይጨነቁም፤ መፅሐፎቻቸው የወጥ የሆነ ሃሳብ አያቀርቡም … ባንዴ ሁለት ዛፍ ላይ ለመንጠላጠል የሞክራሉ፡፡አጥብቀው የተቃወሙትና የኮነኑት ሐሳብ ወይም ግለሰብ መልሰው ሲክቡትና ሲያሞካሹት ይስተዋላል… ከገዠው ፓረቲ ብሰተቀር፡፡ፕሮፌሰር የሚያክል መዓርግ መሸከሙ ሳይከብዳቸው የቀረ አይመስልም፡፡በየጊዜው የሚያሳትሟ መፅሐፎችና በየሚድያው የሚያቀረቧቸው መጣጥፎች የገቢ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለሃገራችን አንድነትና ሰላም ግን ምንም አይፈይዱም፡፡

No comments:

Post a Comment