እንደ ማንኛውም የአደስ አበባ አብያተ ክረስትያናት ራስ ደስታ ሆስፒታል አከባቢ ያለው ዮሃንስ ቤተ
ክርስትያንም ዙርያው በጎደና አደሮች የተከበበ ነው፡፡ የእነዚህ ወገኖች አኗኗር በጣም ያሳዝናል፡፡ የሚለብሱት ብትቶ እጅግ በጣም
ከመቆሸሹ የተነሳ ከለሩ ምን እንደሆና ከምን እንደተሰራ ማወቅ አይቻልም፡፡እንትንፋሳችውን ለማቆየት ምእመናን የሚጥሉላቸውን ትርፍራፊ(ቡሌ)
እየቀማመሱ ይኖራሉ፡፡ እንደውም ይህም ከተገኘ ነው፡፡ ከቀናቸው በካርቶን ወይም በፕላስቲከ ላይ ከለሆነም ያው ወለሉን ጠረግ ጠረግ
አርገው እዛው ይተኛሉ፡፡ ቀን በፀሐይ ለሊት ደግሞ በብርድ ሰለሚለበለቡ መላ አካላቸው በልዟል፡፡እንኳን ባእድ ቤተሰብም አይለያቸውም፡፡
በተለይ ክረምት ሃይለኛ ዶፍና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ሲወርድባቸው ስቃያቸው ከልክ በላይ ይሆናል፡፡እነዚህ ወገኖች አበዛኞቹ ህፃናትና
ሽማግሌዎች ሲሆኑ በእምነት ደግሞ ክርስተያኖች ናቸው፡፡ ይህ ስለሆነም ቤተክርስትያኑ በተንጣለለ ግቢ ውስጥ በሚሊዮንች በሚቆጠር
ገንዘብ ተገንብቶ ባደው ለምን እንደሚያድር ይገርመኛል፡፡ የተገነባው በክርስትያኖች ገንዝብ፣ ስሙ ”ቤተ ክርስትያን“ ነገር ግን
ማንም አይኖርበትም… እነዚያ ምስኪኖች ከአጥሩ ውጪ ስቃያቸውን ሲበሉ ይኖራሉ፡፡ ጥዋትና ማታ በቤተ ክረስትያኑ አጠገብ ሳልፍ ይህ
ነገር ሁሌም ይከነክነኛል፡፡ ’ሰይጣን’ የሚፈታተነኝ እየመሰለኝም አማትባሎሁ፡፡ ነገር ግን ለውጥ የለውም፡፡ አንድም እኔ ራሴ ’ሰይጣን’
ሆኛሎሁ አልያም ’ሰይጣን’ ብሎ ነገር የለም፤ ግን ’ሰይጣን’ ያማትባል እንዴ?
ከቤት ወደ ስራ እንዲሁም ስራ ውየ ወደ ቤት ስገባ ሁሌም በዛች ቤተ ክርስትያን አጠገብ ማለፍ ግድ
ይለኛል፡፡ በዚ ጊዜ ነበር አንድ በጣም የተጎዛቆሉ አባት ከቤተ ክርስትያኑ አጥር በውጪ በኩል ግንቡ ላይ ደገፍ ብለው ያየሁት፡፡
ሽማግሌው በጣም ተዳክመዋል፤ አሁንም አሁንም ያስላቸዋል፡፡ ”እሁ እሁ አሁ” የላሉ … እጅግ በጣም የተዳከመ የጣር ሳል፡፡ በተጨማደደ
ቆዳ የተሸፈነ አጥንት እንጂ ስጋ የላቸውም፡፡ መንም አይናገሩም፤ አየኖቻቸው ግን የቁለጨልጫሉ… ከሩቅ የሚታይ ዋሻ ውስጥ ሁነው
የሚያበሩ ሁለት ላምባዲናዎች ይመስላሉ፡፡ አኳኋናቸው አንጀት ይበላል፡፡ ለቁርስ ብየ የገዛሁት ዳቦ አውጥቼ ሰጠኋቸው፡፡ ግን ሊበሉት
አልቻሉም … እንዴት የዋጥላቸው?ቤት ሂጄ የነበረኝ ትርፍ አሮጌ አንሶላና ሹራብ ይዤላቸው መጣሁና ሰጠኋቸው… አኖቻቸውን በማቁለጭለጭ
ሲየመሰግኑኝ አስተዋልኩ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል እንዲህ እዛው ቆይቷል፡፡
ዕለተ ሐሙስ፣ሕዳር 19 ቀን 2004 ዓ.ም ግን እዛ ቦታቸው ላይ አልነበሩም፡፡ በአከባቢው ከነበሩ
ጎደና አደሮች አንዱን ስጠይቅ በግድየለሽነት
”በክህ እሳቸው ላሽ ብሏል“ አለኝ፡፡ ገባኝ፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ማለቱ ነበር፡፡ በጣም አዘነኩ፡፡ ከናቴ በላይ የምወዳት
አያቴ ትዝ አለችኝና አምርሬ አለቀስኩ… በቃ የኔኑ የሞተች ነበር የመስለኝ፡፡ ለሊቱን ሙሉ በሐሳብ ማዕበል እናጥ አደርኩ፡፡ ስንት
ወገኖች አዚህ ዓልም በሞት ተለዩ? ስላነዱ/ዋ ሳስብ ሌላው/ዋ ደግሞ እየተተካ በማያቋርጥ ሐሳብ ውስጥ ገባሁ፡፡ ሰው መፈላስፍ የሚጀምረው
ሲመረው ነው ይባል የለም? ያው በአቅሜ መፈላሰፍ ጀመርኩ፡፡ የሰው ልጅ ግን ለምን ተፈጠረ? ለምነስ ይወለዳል? ከተወለደስ ለምን
ይሞታል? ወዘተ የሚሉ ጥያቅየዎች በሕልናየ መመላለስ ጀመሩ፡፡ መልስ ግን ከየት ይምጣ? አዎ! የሰው ልጅ ታላቁ አሳዛኝ ተፈጥሮ
እንደሚሸነፍ እያወቀ መታገሉን ነው፡፡ ለዛም ይመስልኛል ማኛውም ህፃን ሲወለድ እሪ ብሎ የሚያለቅሰው፡፡ እያደገና እያወቀ በመጣ
ቁጥርም እውነታው ቀስ በቀስ እንደ ንጋት እየተገለጠለት ይሄዳል፡፡ ያኔ ቅስሙ ሊሰበር ይችላል፤ ይፈራል፣ይሸበራል፣ይጨነቃል፣ ይደናገራል፣ካንዱ
ቦታ ወደ ሌላው ይዞራል፣ ከአንዱ ሃይማኖት ወደ ሌላው ይቀይራል፡፡ሳይሞት መሞቱን ይረዳና በመራራ ሃዘን መሰቃየት ይጀምራል፤ ጉልበቱ
ይዝላል፣ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በዚ መሃል ራሳቸው የሚያጠፉ ይኖራሉ፡፡ ካል ሆነም የመጨረሻዋ ትንፋሹ እስክትወጣ ድረስ ትግሉን ይቀጥላል፡፡
ሂይወት
ትግል ነው፡፡ በትግል ጊዜ ደግሞ ብዙ ጦርነቶች ያጋጥማሉ፤ እንደየሰው የጦርነት ስልትና ጥንካሬም አንደዳነዶቹን በድል ልያጠናቅቅ
ይችላል፡፡አዎ!
የሂይወት ውጣ ውረድ፣ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው፡፡ እንዱን ጦርነት ስታሸንፍ ሌላው እየተከተለ መከራ ያሳይሃል፡፡ለተወስነ ጊዜም
ቢሆን እያንዳንዱ ጦርነት በድል ሲጠናቀቅ ሊያስደስት ይችላል፡፡ ካልሆነ ግን በቁስል ላይ ስንጥር የመጨመር ያህል የሰቀቀን ጊዜው
እየረዘመና ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ይሄዳል፡፡ ይህ ነው የዓልም የስቃይና ደስታ መደበላለቅ፡፡ ያንዱ ስቃይ ለሌደስታ ነው፣ የለላው
ስቃይ ደግም ያንዱን ደስታ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚያስደስተንም ሆነ የሚያሳዝነን አንድ ዓይነት አይደለም፡፡
ለምሳሌ እኔን በጣም የሚያሳዝነኝ ሰዎች በሐዘን፣በበሽታና በችጋር ሲሰቃዩ ማያት ነው፡፡ የቀፈኛል፣ከልክ
በላይ ይሰቀጥጠኛል፡፡ ሰዎች ሁሉም ነገር ከአቅማቸው በላይ ሁኖ ሰያቀረቀሩ ማየት እጅጉን ይከፋኛል፡፡አያርገውና ለዚህ ምክንያቱ
እኔ ከሆንኩ ደግሞ የማይጠግን የልብ ስብራት ይደርስብኛል፡፡በአንፃሩ የሚያስደስተኝም ሰዎች በደስታ እንደ ህፃን ሲቦርቁና በሳቅ
ሲፍነከነኩ ማይት ነው፡፡ በተለይ ለዚህ የመንፈስ እርካታን ሐሴት
ምክንያቱ እኔ ከሆንኩ የሚሰማኝ የደስታ ስሜት እጅግ በጣም የላቀ ነው፡፡ በቃ መግለፅ ከምችለው በላይ ነፍሴ በሐሴት
ትሰክራለች፣ቅቤ ተጠጣለች፡፡ ያን ጊዜ ጦርነቱ ብቻ ሳይሆን ትግሉም ጭምር በታላቅ ድል የተወጣሁ ይመስለኛል፡፡
በዚህ ምክንያት የንጊዜም ፀሎቴና ሚኞቴ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው፡፡አንደኛው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ
ለሰዎች ደስታ ማጣት ምክንያት እንዳልሆን ሲሆን ሌላው ደግሞ የሰው ልጆችን መከራና ስቃይ ለማስወገድ ካልቻለኩም ለመቀነስ የሚያስችል
ብቃት እንዲኖረን መፀለይና በተቻለኝ መጠን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ግን እስካሁን ምን ሰራሁ? ምንም! ባዶ ምኞት ብቻ፡፡ በጣም!
እጀግ በጣም የሚያሳዝነው የነዚያ የሚበሉት፣ የሚለብሱትና የሚጠለሉት አጥተው በየጎደናው አስፓልት ላይ ቀን አናት በሚበረቅሰው በፀሐይ
፣ለሊት ደግሞ እንደ ጅብ በሚናከሰው ውርጭ ሲገረፉ የሚኖሩት ምስኪን ወገኖች ነው፡፡ ወገን ከወደቀበት ለመነሳት ሲታገሉ እያዩ እንዳላዩ
ማለፍ እንዴት ያሳፍራል? ጊዜ ጥሏቸው፣ እርጅና ሳይፈልጉትና ሳይዘጋጁ ደርሶባቸው ነብሲ ግቢ ነብሲ ውጪ ሲጣጣሩ አይቶ አለሁላችሁ!ብሎ
አለመድረስ ምንኛ ያሳዝናል? ይህ ነው መቋጫ የለለው የሂይወት ጦርነት፣ እንደምትሸነፍ እያወቁ መታገል፡፡
የሰው
ልጅ ሲወለድም ሆነ ሲሞት በደንገት ነው፡፡ ስንወለድ በዚህ ቀንና ዓመተ ምህረት(ዓመተ ዓለም) ከእናቴ ወ/ሮ እንትና እና ከአባቴ
አቶ እንትና ፣ በዚህ አከባቢ ወይም ሃገር መወለድ አለብኝ ብለን
አናቅድም፡፡ ብቻ ተፈጥሮ አየትም አምጥታ የትም ተጥለናለች፡፡ ስንሞትም እንዲሁ የቦታና ጊዜ መርጫ የለንም፡፡ ብቻ ግን እያደግን
ስንመጣ አንድ ቀን፣ በሆነ ቦታ፣ በሆነ ምክንያት መሞታችኝ እንደማይቀር እናውቃለን፡፡ በተለይ የኔ ያልነው ውድ ቤተሰባችን ድንገት
በሞት ስንጣ ተስፋ አስቆራጭ የልብ ስብራት ይደርስብናል፡፡ በሐዘን አለንጋ እነገረፋለን፡፡ የህ ከባድ ሐዘን ምንጊዜም የማይጠፋ
አስቀያሚ ጠባሳ ትቶብን ይሄዳል፡፡ በዓለም ላይ ያለን አመለካከት ሙሉ በሙሉ ይቀየራል፡፡ የኛ መጨረሻም እንድያ መሆኑን መርዶ ይነገረናል፡፡
ተድያ
ሂይወት እንዲህ ከሆነች ለምን የጥፋት መለዮ ለበሰን የሌሎችን ዓለም ለማጨለም ሌት ተቀን እንዳክራለን? ለምንድ ነው በሰው ልጅ
ቁስል ላይ ስንጥር የምንጨምረው? እንዴ! ይህ ነገር መቆም አለበት፡፡ብያንስ መቀነስ አለበት፡፡ በቁስል ላይ ቁስል መጨመር ሳይሆን
የቆሰለውን እንዲድን ፣ ያልቆሰለውም እንዳይ ቆስል መከላከል አለብን፡፡ ካልሆነ ግን አንዱ ሌላውን እያቆሰለ፣ እየተቆሳሰልን የቁስለኞች
ዓለም ነው የንፈጥረው፡፡ የቆሰለ አካል አይነካም፤ ቢነካም ያሰቃያል፡፡ የቆሰለ ሰውም ሆነ እንስሳ ቁስሉን ማስታመም እንጂ ሌላ
አማራጭ የለውም፡፡ ቢነሮውም ትዕግስት ያጣል፡፡ በጨረሻም የስቃይ ንሮው በማያዳግም ሞት የፈፀማል፡፡ ይህ የሰው ልጅ ታላቁ ሽንፈት
ነው፡፡ የሚያሳዝነው ድግሞ መጨሻችን ሽንፈት(ሞት) መሆኑን እያወቅን መታገላችን ነው፡፡ የምንታገለው ዘላለማዊ የሆነ ድል ለመቀዳጀት
ሳይሆን ለትንሽ ጊዜ በሂይወት ለመሰንበት ነው፡፡
ዓለም
የቤት ክራይ ነች፡፡ሰለዚህ ለዚች አጭር ጊዜ በደስታ ማሳለፍ አለብን፡፡የክራይ ዘመናችንን አሟጥጠን መጠቀም የግድ ይለናል፡፡ምክንያቱም ሂይወት እነዴ ከመለጠች አመለጠች ነው፤
መልሰን አናገኛትም፡፡ ይህ የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ ቀንና ሌሊተ፣እረምትና በጋ እንደሚቀያየሩ ሁሉ አሮጌም በአዲስ በተካት አለበት፡፡
ህፃንነት በወጣትነት፣ወጣትነት በጎልማሳነት፣ጎልማሳነት በእርጅና፣ እርጅና ድግሞ በሞት የፈፀማል፡፡ ይህ የማይዛነፍ የተፈጥሮ የእኩልነት
መገለጫችን ነው፡፡ያለዕድሜ መቀጨትና በቁም መሞትን ትተን ማለት ነው፡፡
ኤጭ!
ብዙ ለፈለፍኩ፡፡ ደግሞ ግጥም ልመክር መሰለኝ፡፡
ሸኩ፣ጳጳሱ፣ቄሱ፣ቀለበሱ
እስላሙ፣ክርስትያኑ፣እምነት
የለሽ ፈረሱ
ተማሪ፣መመህሩ፣ተመራማሪ፣ቅኔ
መወድሱ
መሃይም፣ምሁሩ፣ፕሮፎሴር፣የእውቀት
አድማሱ
ገዢ፣ተገዢ፣አምባገነን፣ንጉሱ
ድሃ፣ሃብታም፣ስግብግብ
ከርሳም ነብሱ
በደግሙ፣ቢጠነቁሉ፣ጉድጓድ
ቢቆፍሩ ስር ቢምሱ
ሁሉም
ሞቱ፣ ተቀበሩ አፈር ለበሱ
ትል
በላቸው፣ በሰበሱ ተረሱ፡፡
ነገር ግን
ያ
ታታሪው አገልጋይ ፣ለሌሎች የኖረው
ያዘነውን
ያፅናናው ፣የተራበውን ያጎረሰው
፣የታረዘውን ያለበሰው
፣የተጠማውን ያጠጣው
ቤት
አልባውን ያስጠለለው ፣የተረሳውን ያስታወሰው
ራሱን
ችላ ያለው ፣ሂይወቱም ጭምር ፣ለሌሎች አሳልፎ የሰጠው፡፡
ሁሌም
ይታወሳል፣ዘመን ይሻገራል፣ትውልድን ያኮራል
በልብ
ሐወልት ይተክላል፣የጀግኖች ተምሳሌት ይሆናል
ስሙ
እንደ ሂትለር አይወገዝም፣ይወደሳል፣ይወረሳል
እንደ
ጋንዲ፣ማርቲን ሉተር ኪንግ፣እንደ ማንዴላ ይሸለማል ይከበራል
የተዘጋውን
የነፃነት በር ይከፍታል፣በሌሎች ፈንታ ይታሰራል ይሞታል
ቁስላችሁ
ቁስሌ ይላል፣ያክማል፣ይፈውሳል፡፡
እኔም
የሱ
ተከታይ ነኝ፣አምላኪው እሆናሎሁ
በፅናቱ
እፀናሎሁ፣በብርታቱ እበረታሎሁ
ወገኖቹን
አከብራሎሁ፣ጠላቶቹን እጠላሎሁ
መንገዱን
እከተላሎሁ፣ጅምሩን እፈፅማሎሁ
መንገዱን
እከተላሎሁ፣ጅምሩን እፈፅማሎሁ፡፡
ሰላም!
No comments:
Post a Comment