ትዝ ይለኛል፣ጥር ወር 1998 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ
የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ ነበር፡፡ያኔ እንደ አሁኑ የሞባይል መስመር እንደልብ ስለማይገኝ በሩቅ የሚገኙ
ቤተሰቦችን በስልክ ለማግኘት ማዞርያ ወዳለበት የቴሌኮምኒኬሽን ቢሮ መሄድ ግድ ይላል፡፡እናም
የመጀመርያው ግማሽ ዓመት የማጠቃለያ ፍተና እንዳለቀ ወደ ቤተስብ ስልክ ለመደወል በመቐለ ከተማ ወደነበረው ብቸኛ የቴሌኮምኒኬሽን
የደምበኞች አግልግሎት ማዕከል አመራሁ፡፡
ሰልፉ አይጣል ነው፤በጣም ረጅምና አሰልቺ ነበር፡፡ቢሮው
ውስጥ ያሉ ወንበሮች ተጠጋግተው በተቀመጡ ደምበኞች ተጨናንቋል፡፡ሰልፉ ከቢሮ ውጭም ቀጥሏል፡፡ወደ ውጭ ሃገርና ወደ ተለያዩ የሃገራችን
አከባቢዎች መደወል የሚቻለው የደዋይ ስም፣የሚደውሉለት ሰው ስምና አድራሻ በማስመዝገብ ነበር፡፡እኔም እንዲሁ አደረኩና ተራየ እስኪደርስ
ተሰልፌ መጠቅ ጀመርኩ፡፡አብዛኞቹ አስተናጋጆች ትላልቅ በለማሰርያ መነፅሮች ያደረጉ የዕደሜ
ባለፀጋ እናቶች ነበሩ፡፡ጊዜው ይነጉዳል፤የተስተናጋጆቹ ስልፍ ግን ፈቀቅ አይልም፡፡ለሰዓታት ተሰልፈን ከጠበቅን በኋላ አንድ የቴሌ
ጥበቃ መጥተው በያዙት በትር ወደ አንዱ ተሰላፊ እየጠቆሙ‹‹ሰዓት ስለደረሰ ከዚህ በኋላ ያላችሁ ደምበኞች ከሰዓት ኑ››በለው አስናበቱን፡፡
ከሰዓት በኋላ ቀደም ብየ ነበር በቦታው የደረስኩት፡፡ነገር ግን ያኔም ከሃያ
በላይ የሚሆኑ ስልፈኞች ቀድመውኛል፡፡ከነሱ ቀጥየ ተሰለፈኩ፡፡ከፊት ለፊቴ የነበሩ ሰልፈኞች ተስተናግደው ወደየመጡበት ተመልሷል፡፡የኔ ስም ባይጠራም ባትዕግስት መጠበቁን ቀጠልኩበት፡፡ምናልባት
ላገኘው የፈለጉት ሰው አልቀረበም ይሆናል በማለት፡፡ሌላ ተጨማሪ ግማሽ ሰዓት ጠበኩኝ፤ምንም ለውጥ አላገኘሁም፡፡በመጨረሻም ትዕግስቴ
ተሟጦ አለቀና ስሜን የመዘገቡት ሴትዮ ወዳሉበት በመስታወት የተጋረደ መስኮት ጠጋ ብየ የኔ ስም ለምን እንደማይጠራ በቁጣ ጠየኳቸው፡፡አስተናገጇ
ሴትዮ መነፅራቸውን ወደ ላይ ከፍ እያረጉ ዓኖቻቸውን ጠበብ አርገው ተመለከቱኝና ‹‹ስምህ ማን ነበር?››
ብለው ጠየቁኝ፡፡ነገርኳቸው፡፡ጧት ያስመዘገኩት ወረቀት ላይ ገልበጥ ገልበጥ እያደረጉ ከፈለጉ በኋላ ‹‹ትንሽ ጠብቅ፤ እጠራሃለሁ››
አሉኝ፡፡ምንም አማራጭ ስላልነበረኝ አሁንም መጠበቁን ቀጠልኩበት፡፡
ከአስራ ምናምን ደቂቃ በኋላ ጠሩኝና የፈለኩት ቤተስብ ሊገኝ ስላልቻል ሌላ
ቀን እንድ መጣ ነገሩኝ፡፡‹‹ኤጭ! ምን ዓይነት መስራቤት ነው በግዚሔር?አይጠፋ አይለማ፤ሰራተኞቹ
ቀርፋፋ ድርጅቱ ቀርፋፋ… ››እያልኩ ሳጉመርም የሰሙኝ አስተናጋጇም ቀበል አድረገው‹‹አረባክህ በቴሌ ነው እንዲህ የምታሽሟጥጠው?ባይ
ገርምህ የቴሌ ሰራተኛ ለመሆን ሰባት አብያተ ክርስትያናት ተሳልመህም አታገኘውም›› አሉኝ፡፡ለጊዜው ምን ለማለት እንደ ፈለጉ አልገባኝም
ነበር፡፡ኋላ ላይ ነገርየው ሳሰላስለው ቴሌ በቀላሉ ሊወጣ የማይችል ተራራ መስሎ ታየኝ፡፡የሰትዮዋ አባባል እልህ ውስጥ ከተተኝና
በቴሌ ተቀጥሮ የመስራት ፍላጎቴን ሰማይ ሰቀለው፡፡
ሰኔ 1999 ዓ.ም የዓመቱ መጠቃለያ ፈተናና የመመረቂያ ፕሮጃክታችንን ሰርተን
ጨርሰናል፡፡ የቀረን ነገር ቢኖር ሐምሌ 8 የሚደረገው የምረቃ ቀን ነበር፡፡በማሃሉ የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከ
2.75 በላይ ጂ.ፒ.ኤ ያላቸው አዲስ ተመራቂዎች አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ የሚገልፅ መስታወቂያ በግቢያችን ውስጥ ለጠፈ፡፡ሳላቅማማ
ለምዝገባው አስፈላጊ ነው የተባለው መረጃ ይዤ መቐለ ወደ ሚገኘው የመስራቤቱ ፅሐፈት ቤት ሂጄ ተመዘገብኩኝ፡፡ከዛም ነሐሴ ወር ላይ
አብሮውኝ ከተማሩት ጓደኞቼ ጋር ለቃለ መጠይቅ ተጠራንና ቃለመጠይቁን አደረግን፡፡
ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ቃለ መጠይቁን ማለፋችንን የሚያሳይ ውጤታችንና መስከረም
6 አዲስ አበባ መገኘት እንዳለብን የሚገልፅ ማስታወቂያ በሰሌዳ ላይ መለጠፉን ጓደኛየ በስልክ ደውሎ ነገረኝ፡፡(ፀጋይ ትኩእ፣ የድሮ
ጃቫ የዛሬው ውኪሊክስ ከምስጋና በቀር ውለታህን ከፍዬ አልጨርሰውምና ፈጣሪ አብዝቶ ይክፈልልኝ፡፡)መጀመርያ አላመንኩትም ነበር ኋላ
እውነቱን ሳረጋግጥ ግን በደስታ ብዛት የምሆነውን አጣሁ፡፡ቤተሰቦቼ በውሉ ሳልሰናበት እየበረርኩ መቐለ ገባሁ፤ከመቐለም በአውቶብስ
ወደ አዲስ አበባ፡፡የኢህዴግ ታጋዮች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የወጣው የህወሐት ዘፈን እየዘፈንኩ፡፡
ተጋዳላይ/አስፋው መዓር አፉ
አዲስ አባባ ሓሊፉ
ዬ!
መስከረም አንድ 2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሚሊንየም በመላ ሃገሪቱ በድምቀት
በመከበር ላይ ነበር፡፡ለኔ ግን ‹‹ተሌኮሙኒኬሽን ለመግባት ሰባት አብያተ
ከርስትያናት መሳለም ይጠበቅብሃል፡፡›› የተባልኩት መስራቤት እንዲህ በቀላሉ መቀጠር በመቻሌ የሚሊንየሙ ድምቀት እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡መስከረም
6 በሚሊንየም ተወዳጅ ዘፈኖች ታጅበን በአውቶብስ ተሳፍረን የኢትዮጵያ ዋና ከተማና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ወደ ሆነችው አዲሰ
አበባ ገባን፡፡የአዲስ አበባ ንሮ በዘመድ ቤት ጥገኝነት ተጀመረ … የገጠርና የከተማ የንሮ ልዩነት… የህይወት ምስቅልቅል … አራምባና
ቆቦ፡፡
ወይ ጊዜ ጊዜ መስታወት
ስንት አየንበት
አለች ዘፋኝዋ!
የአዲስ አበባ ንሮ እያስለመለመ ቀጠሏል፡፡መብራት ሃይል
ይዚች ከተማ አይጠፋ አይለማ ህይወት ተምሳሌት ሳይሆን አይቀርም… የንሮ ብልጭ ድርግም፡፡ቴሌ ለደምበኞቹ ብቻ አይደለም‹‹መስመሩ
ለጊዜው ተይዟል…›› ያለው ለኛ ለሰራተኞቹም የንሮው መስመር ላልተወሰነ ጊዜ መያዙን በእጅ አዙር ነግሮናል፡፡የቴሌ ቅጥረኝነትና
የአዲስ አበባ ህይወት ገና አላለቀም…መቸ ተነካና፡፡ ይህ ፅሑፍም ይቀጥላል…እሱ እስከ ፈቀደ ድረስ፡፡
No comments:
Post a Comment