በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት የተጀመረው በአፄ
ምንሊክ ዘመንግስት ነበር፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1894 ዓ.ም፡፡ይህ አንጋፋ ተቋም ከዕድሜው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የቴክኖሎጂ
ሽግግር አላደረገም ማለት ይቻላል፡፡ለዚህ አባባል የሚያጠናክርልን ደግሞ ከ130 ዓመታት በኋላም ደምበኞቹን በአግልግሎት ማርካት
አለመቻሉ ነው፡፡የሚሰጣቸው አግልግሎቶች በጥራት፣በዘመናዊነትና በተደራሽነት ኋላቀር ናቸው፡፡
ድርጅቱ ከተመሰረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ግልፅ የሆነ ለውጥ ያመጣው በስም
ብቻ ነው፡፡እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር፡-
1. በ1894
ዓ.ም የቴሌፎን፣የቴሌግራፍና የፖስታ ቤት ሚኒስተር በሚል መጠራያ ተቋቋመ፡፡በ1941 ዓ.ም በፋሽስት ጣልያን ታላቅ ውድመት ደርሶበት
ነበር፤ ከቴሌግራፍና ፖስታቤት ጋር፡፡
2. በ1952
ዓ.ም አፄ ሃይለስላሴ ከስደት እንደተመለሱ በአዋጅ ቁጥር 131/52 የንጉሱ ቴሌኮምኒኬሽን
ቦርድ(Imperial
Board of Telecommunications) ተብሎ እንዲጠራ ተደረገ፡፡
3. በ1975 ዓ.ም በደርግ መንግስት የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን
አገልግሎት(Ethiopian Telecommunications Service)ተብሎ ተጠራ፡፡
4. በ1981 ዓ.ም ደግሞ የደርግ መንግስት እንደገና የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ባለስልጣን (Ethiopian
Telecommunications Authority) ብሎ ሰየመው፡፡ የቴሌኮም ዘርፉ የማስፈፀምና የመቆጣጠር ስልጣንም ተሰጠው፡፡
5. 1996
ዓ.ም ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በአዋጅ ቁጥር 49/1996 መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ተጠሪ (Ethiopian
Telecommunication Agency) ተብሎ እንዲጠራ ወስኖ ነበር፡፡
6. ብዙ ሳይቆይ ግን በዚሁ ዓመተ ምህረት በመመርያ ቁጥር
10/1996 መሰረት እንደገና የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን(Ethiopian
Telecommunications Corporation) ተብሎ እንዲጠራ ሆነ፡፡
7. የስያሜ ለውጡ አሁንም ቀጠለና በ2010 ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም ተባለ፡፡ይህ ስያሜ ግን በኢትዮጵያውያን የወጣለት አልነበረም፡፡
ለሁለት ዓመታት እንዲያሰተዳድሩትና መንግስት መሰረታዊ የሆነ ተቋማዊ ለውጥ ያመጣሉ የሚል እምነት የጣለባቸው ፈረንሳውያን ናቸው ፤በ30 ሚልዮን ዩሮ !
እንግዲህ እኔ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ቴሌ ሰባት ጊዜ የስያሜ ለውጥ እድረጓል፡፡የስም
ለውጥ ግን የታሰበው የአስተዳደርና የቴክኖሎጂ እምርታ አላስገኘም፡፡ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ታላላቅ ድርጅቶች በግንባር
ቀዳሚነት መምራት ሲገባው ዛሬም ድረስ የኋሊት እየተራመደ የእድገት ማነቆ ሆኖ ቀጥለዋል፡፡
በሰራተኛ አያያዝም እንዲሁ በጣም ደካማ ነው፡፡ድሮ ሰራተኞች የሚቀጠሩትና
ጥቅማጥቅሞች የሚያገኙት በዝምድና እንደ ነበረ የነገራል፡፡ይህ አሰራር ግን አሁንም ቀጥሏል፡፡ቅጥር የሚፈፀመው በግልፅ ማስታወቂያ
አወዳድሮ ቢሆንም ዕድገትና የስራ ዝውውር ግን ዛሬም በአውቀዋሎሁ ባዮች ጥቆማ መከናወኑን ኢፍትሐዊ እንዳደረገው ሰራተኞች ይናገራሉ፡፡በተለይ
በ2003 ዓ.ም በድርጅቱ የተከናወነው መሰራታዊ ለምጥ(ትራነስፎርሜሽን)ምክንያት
ብዙ ሰራተኞች ያለአግባብ ተባሯል፤ብዙዎችም በማይፈልጉት የስራ ክፍል በግዳጅ ተመድቧል፡፡የአስተዳደሩ ድርሻ የተሰጣቸው ፈረነሳውያንና
በጥቆማ ያሰባሰቧቸው የድርጅቱ ሰራተኞች በቅጥር አሳብበው ሴቶች እህቶቻችንን ሲደፍሩ እንደነበር ይነገራል፡፡ከእንደዚህ ዓይነት አስነዋሪ
ተግባርና ስልጣን ያለአግባብ መጠቀም ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተባረሩት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለሳቸው ብዙዎች አሳዘኗል፡፡
ሰራተኞች እስከ መደብደብ የደረሱ ፈረንሳውያንም ነበሩ፡፡በተለይ ኢሪክ የሚባለው
ጂኒ የያዘው ነበር የሚመስለው፡፡ቀስ ብሎ መናገር አይሆንለትም፤ሁሌም እንደ ጮሀ ነበር፡፡በቢሮው ውስጥ ሳይቀር ያጨስ ስለነበር ኮሪደሩ
ሁሉ በየሲጋራ ጭስና መጥፎ ሽታ ይታወድ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ብዙዎች ለ‹‹passive smoking››ተጋልጧል፡፡ሃገራችንም እንደ
ሲጋራው አጭሷታል፡፡በጣም የሚያሳዝነው ግን ኢትዮጵያውያን በለፉት ከ30 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ለኢምንት ለውጥ መዝረፋቸው ነው፡፡
የድርጅቱ ትራንስፎርሜሽን(መሰረታዊ የሆነ ተቋማዊ ለውጥ) የተጀመረው የሰራተኛ
ማሕበሩን በማፈረካከስ ነበር፡፡አብዛኞቹ የማሕበሩ አመራሮች የኢህአዴግ አባላት የነበሩ ሲሆን የአቶ አዲሱ ቦሬ የስም ማጥፋት ዘመቻ
የተጀመረው ቲፒኦና ኢንጂኢን(teransformation program office and next generation network)አንደ
ተቋቋሙ ነበር፡፡አዲሱ ቦሬ የለውጥ ተቀናቃኝ፣የማሕበሩ ስልጣን ላለመልቀቅ መሳርያ እስከ መማዘዝ ድረሷል፣ያለ አግባብ በልፅጓል፣ድሮ
የኢህአፓ አባል ነበር ወዘተ በማለት በትራንስፖርትና መገናኛና ሚኒስተር ተገምግሞ ግለ ሂሱን ባለመቀበሉ ከአባልነት እንዲገለል ተደርጓል፡፡ከዛም
የሰራተኛ ማሕበሩ አመራር ለሁለት ተሰነጠቀ፡፡አዲሱና ደጋፊዎቹ በአንድ ብዱን የለውጥ ፀር ተብለው ተፈረጁ፤የነሱ ተቃራኒ የሆኑ ደግሞ
ከለውጥ ጋር ተራማጅ በመምሰል ተደራጁ፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ሲመሰረት ደግሞ አዲሱ ቦሬ ከስራ ከተባረሩት ሰራተኞች አንዱ ሆነ፡፡ነገር
ግን እስካሁን ድረስ የሰራተኛ ማሕበሩ የቢሮ ቁልፍ በእጁ እንደሚገኝና በፍርድ ቤትም እየተከራከረ መሆኑን ነው የሚነገረው፡፡
የአዲሱ የማሕበር አመራሮች ምርጫ
ኢትዮ ቴሌኮም ከተመሰረተ ወዲህ የቀድሞው የሰራተኛ ማሕበር
አመራር ህጋዊነት እንደሌለው የመንግስት ባለስልጣናት ተነገሩና በራሳቸው ምርጫ ሌላ የሰራተኛ ማሕበር አመራር አቋቋሙ፡፡ነገር
ግን ከስም ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም፡፡ሰራተኞች በለውጥ ማዕበል ሲጠራረጉ የት እንደ ነበረም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ምናልባት ግን
በጥቆማው ድርሻ ሳይኖረው አይቀርም የሚል መላ ምት አለ፡፡በዚህ ምክንያት የሰራተኛው እምነት ማግኘት አልቻለም ነበርና የካቲት
29፣2005 ዓ.ም በመንገድ ትራስፖረት መገናኛ ሚኒስተር የመሰብሰብያ አደራሽ የምበኞች
አገልግሎትና(customer service division) ኢንፎርሜሽን ሲስተም(information system
division) የስራ ክፍሎች የሚወክሉ አድስ
የሰራተኛ ማሕበር አመራሮች ተመርጧል፡፡
ከምርጫው ስነ ስርዓት በፊት ግን ማን እንደ መረጣቸው
የማይታወቅ አክስት የሰራተኛ ማሕበር አመራሮች ነን ባዮች በየተራ መግለጫዎች ሰጥተዋል፡፡እነሱ በሰጡ ማብራርያ መሰረት፡-
የሰራተኛ ማሕበሩ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ትንቀሳቃሽና
ሌላ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ቋሚ ተቀማጭ ግንዘብ አለው፡፡ በአጠቃላይ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለው
ተገልፀዋል፡፡
ሰራተኞች ቤት እንዲሰራላቸው በየወሩ ከደሞዛቸው እየተቆረጠ
በባንክ የሚጠራቀመው ገንዘብም ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱንና በዝግ አካውንት መቀመጡን አብራርተዋል፡፡ስለሆነም ከድርጅቱ ጋር
በመተባበር ለሰራተኞች ቤት ለማስገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም የቆላ አበል አከፋፈል ወጥነት የለውም፡፡የቆላ
አበል(hardship allowance)አንደኛ(በጣም ቆላማ)ሁለተኛ ደረጃና መጠነኛ ወይም ቀላል ተብሎ ይከፈላል፡፡ በዓፋር ክልል
የሚገኘው ዳሎል በኢትዮጵያ ደረጃ ተወዳዳሪ የለለው ረባዳ በረሃና የማያንቀላፋ እሳተጎመራ የሚንተገተግበት ስፍራ ቢሆንም በቴሌኮምኒኬሽን
የቆላ አበል ክፍያ ስርዓት መሰረት ግን በሁለተኛ ደረጃነት ተመዝግቦ እንደሚገኝ ተገልፀዋል::
የሰራተኞች ጥያቄዎችና እሮሮዎች
ማብራርያዎቻቸውን ከጨረሱ በኋላ የዕለቱ የመድርክ መሪዎች
ቀጥታ ወደ ሰራተኞች ጥያቄና መልስ ነበር ያመሩት፡፡የኢትዮ ቴሌኮም የጥሪ ማእከል ሰራተኞች(Call center)መድርኩን የተቆጣጠሩት
ሲሆን በስሜታዊነት ነበር የአስታየትና ጥያቄ በረዶ ሲያዘንቡት የዋሉት፤በተሳታፊዎች ሞቅ ያለ ጭብጨባ ታጅበው፡፡
ከተሳታፊዎች ከቀረቡት ጥያቄዎች በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1. ይህ የማሕበር አመራር ከየት መጣ?ቢሮው አይገኝም፤እስካሁን ድረስ አራት ጊዜ ቢሮ ቀይሯል፤ የድሮው የሰራተኛ ማሕበር ቢሮ በነ አዲሱ
ቦሬ(የድሮው የሰራተኛ ማሕበር ሐላፊ) እንደ ተያዘ ነው፡፡ የፍርድ ቤት ክርክሩ ምን ላይ ደረሰ?
2. እንሹራንስ ለኛ ምን ይጠቅማል?የመኖርና አለመኖራችን ጉዳይ የፈጣሪ ውሳኔ ነው እኛ ከናንተ የምንፈልገው በህይወት እያለን ከቤት ክራይ
ችግር እንድትገላግሉን እንጂ ስንሞት እንድትቀብሩን አይደለም፡፡
3. ከሕገ መንግስቱን የሚቃረኑ የሕብረት ስራ ስምምነቶች አሉ፡፡እኛ የጥሪ ማእከል ሰራተኞች ታመን ስንማቅቅና
ለመሞት ስናጣጥር የትነበራችሁና ነው አሁን ከሞትን በኋላ እንደ ጥንብ አንሳ አሞራ የመትንጋጉት፡፡ለመቅበር ነው ወይስ ሬሳችን ለመቀራመት?
4. ሴቶች ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ላይ በጎደና ላይ ሲጣሉ የት ነበራችሁ?
5. የኖክ ዲቪዥን ሰራተኞች በሽፍት ሲሰሩ አበል ይከፈላቸው ነበር የጥሪ ማእከል ሰራተኞች የይገባኛል ጥያቄ
ካቀረብን በኋላ ቆመ ለምን?የጥሪ መእከል(call
center) ሰራተኞች ታመው የዕረፍት ቀን ቢጠይቁ አይፈቀድላቸውም ለምን
በአይኤስ ዲቪዥን(IS Division) መመደብ በኤንጂኦ(NGO) እንደ መቀጠር ይቆጠራል በማለት ተሳታዎችን ሳቅ
በሳቅ የደረጉ አስታየት ሰጪዎች ነበሩ፡፡የጥሪ ማእከል ስራ የትንፋሽ ስራ ነው፡፡ነፍሰ ፁሮች ደምበኛ በማስተናገድ ላይ እያሉ ተዘርረው
ይወድቃሉ(ፌንት ያደርጋሉ)፡፡የሚያጠቡ እናቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ ልጅ አጥብተው እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል እንዴት ነው በአንድ
ሰዓት ውስጥ አያትና ጀሞ ደርሰው መምጣት የሚችሉት?የሚሉ
ጠያቂዎቸም ነበሩ፡፡ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሌሊት ሽፍት የሚሰሩ ሴቶች ቀን እንዳይተኙ የቤተሰብ ሐላፊነት ያስገድዳቸዋል፡፡ስለሆነም
ከእንቅልፍ ማጣት የተነሳ በስራ ላይ እያሉ የሚቃዡ መኖራቸውን ተጠቁመዋል፡፡
6. ማንኛውም ሰራተኛ ዓርብ ዓርብ አምስት ተኩል ከስራ ይወጣል፡፡ የጥሪ ማእከል ሰራተኞች ግን ይህ እድል
አይሰጣቸውም ለምን?
7. ለአምስት ዓመታት በድግሪ የትምህርት ደረጃ ሰርተን ለተቆጣጣሪነት ስልጣን ተወዳደረን በትምህርት ደረጃው
ዲፕሎማ ሁኖ ለሰምንት ወር ብቻ የሰራ ሰራተኛ ፉክክሩን አሽንፎ ተመርጠዋል/ተሸመዋል ለምን?
የሴቶች እድገት በስራ ላይ ከሚያሳዩት ተሳትፎ በተጨማሪ
አምስት በመቶ የማካከሻ ድጋፍ(affirmative action) ውጤት ይጨመርላቸዋል መባሉም በመጠኑም ቢሆን ትችት ቀርቦበታል፡፡ከ10ኛ
ወደ መሰናዶ(preparatory)ለማለፍ የማካከሻ ደጋፍ፣ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ እንዲሁ በድጋፍ፣ ከዩኒቨርሲቲ በጥሩ ነጥብ እንዲ መረቁና
የተሻለ ስራ እንዲያገኙም ቅድምያ ይሰጣቸዋል፡፡በማለት ቀሬታቸውን የገለፁ ነበሩ፡፡ነገር ግን የተሳታፊዎች ተቀባይነት ያገኘ አይመስለኝም፤ከራሴ
ጀምሮ፡፡ምክንያቱም አብዛኞቹ ሴቶች ጊዜቸውን ቤተሰብ በመስተዳደር ሰለሚያሳልፉ በትምህርትና በንባብ ራሳቸውን ለማሳደግ መቸገራቸው
ግልፅ ነው፡፡ከእርግዝና እስከውልዶ ማሳደግ በአብዛኛው በሴቶች ጫንቃ የተጣለ ማሕበራዊና ስነ ህይወታዊ ግዴታ መሆኑን አይካድም፡፡
ሌላው ጥያቄ ሰራተኞች በከተማውስጥ የሚኖሩበት አከባቢ
ለቀው የቤት ክራይ ፍለጋ ሲንቀሳቀሱ ለመጓጓዣ ገንዘብ ለምን እንደማይከፈላቸው ነበር፡፡ ከክፍለ ሃገር ወደ ከተሞች (አዲስ አበባና
ሌሎችም) እንዲሁም ከከተሞች ወደ አዲስ አበባ ሲንቀሳቀሱ ራሳቸውና ቤተሰባቸውን ጨምሮ እስከ 50 ኩንታል ድረስ የመጓጓዣ ወጪ ይሸፈንላቸዋል፡፡
የሰራተኞች እድገትና የስራ ዝውውር በጥቆማና በተጠባባቂነት
ለስድስት ወር በመስራት መከናወኑ በመኮነን አስታየታቸውን የሰጡም ነበሩ፡፡አንድ የክፍል አለቃ ስራ ሲለቅ ወይም ወደ ላይ ሲያድግ
የበታቹ ከሆኑት አንዱን በመምረጥ በውክልና ይስቀምጠውና ውክልናው ከስድስት ወር በኋላ ስልጣኑ ይፀድቅለታል፡፡በዚህ አማካኝነት ያለውድድር
ከተራ ሰራተኝነት ወደ ስፖርቫይዘርነት ወይም ማናጀርነት፤ከማናጀርነትም(N-3)ወደ ኦፊሰርነት(N-2)ያደጉ የተመንደጉ ሰራተኞች ብዙ
ናቸው፡፡
ነገር ግን ይህ ዕድል የሚያገኙት በአለቃቸው ተወዳጅ
የሆኑ ሰራተኞች ብቻ ናቸው፡፡አንድ ሰይድ የሚባል ሰራተኛ ብዙ ጊዜ ለኤን4 ደረጃ (supervisor) ለመወዳደር አመልክቶ ስሙ
ባለመጠራቱ ምሬቱን የገለፀው ‹‹እኔ ሰይድ አባላለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ስሜን እቀይራሎሁ››ብሎ በመተረብ ታሳታፊውን በማሳቅ
ነበር፡፡
በመጨረሻ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሴትዮ የሰጡት ገምቢ
ምክርና አስታየት ስሜት የሚነካ ነበር፡፡
‹‹ታሪክ ሰርተን እንለፍ›› ሲሉ ነበር ምክራቸውን የጀመሩት፡፡
‹‹የሰራተኛ አቤትታ አዳምጦ ለችግሮቹ መፍትሔ ማምጣት
ታሪክ መስራት ነው፡፡
የሰራተኞች ህይወት መለወጥ ታሪክ መስራት ነው፡፡ደምበኞችን
በጥራት ማገልገል ታሪክ መስራት ነው፡፡የአገልግሎት የጥሪ ማእከል ቆላ እንደ ሚገኝ እጅግ ወበቃማ በረሐ ነው፡፡ ድምፅ ቀነስሽ፣ጨመርሽ፣ተቆጣሽ
እያሉ ሰራተኛን መገምገምና እድገት መከልከል ተገቢ አይደለም፡፡›› ብለዋል፡፡
ከጥያቄና መልስ በኋላ ቀጥታ ወደ ምርጫው ስነ ስርዓት
በማምራት የማሕበሩ አመራር ተወካዮች በስም በመጠቆምና እጅ በማውጣት በተከናወነ የድምፅ አሰጣጥ ተመርጠዋል፡፡
ከተላላኪነት ተላቀው የማነጅመንቱን ስግብግብነት ሕጋዊ
በሆነ መልኩ በመገዳደር የሰራተኛው መሰረታዊ ጥቅማጥቅሞች ያስጠብቁ ይሆን?እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኛ ማሕበር አመራር ሰራተኛውን በገንዘቡም ቢሆን የቤት ባለቤት
እንዲሆን ይረዱታል ወይስ እነደ ድሮዎቹ በተስፋ እየደለሉ ገንዘቡን እየመዘበሩ ይቀጥላሉ?እስኪ የነገ ሰው ይበለንና አብረን እናያለን፡፡
No comments:
Post a Comment