<<…ልጃገረዶች በገምቦ ውሀ ቀድተው ሲመለሱ
ገምቦውን በድንጋይ ሳፈነዳው ደስ ይለኝ ነበር፤››
<<… ለጥምቀት ኪዳነ ምሕረት ታቦቶችን አጅበን
ሄደን ማታ ጫካው ዳር እሳት እያነደድን ስንሞቅ ከአንድ ልጅ ጋር ተጣላን፤ የተለኳኮሰ ጭራሮ ወረወረብኝ፤ እሱ ተለቅ ያለ ሰውነቱም
ደንዳና ነበረ፤ ድብድቡን ስንጀምር በያዘው ዱላ ጭኔ ላይ ዠለጠኝ፤ ዱላ ስላልያዝሁ ስጋ ለመብያ የያዝሁትን ሰንጢ አወጣሁ፤ ፈራና
ሲሮጥ ወደቀ፤ የወደቀበት ሄጄ አንዴ ወጋሁት፤እሱን ወደሀኪም ቤት ወሰዱት፤እኔን ፖሊሶች እጆቼን በገመድ አስረው አሳደሩኝ፤…>>
‹‹አንድ ጊዜ አፄ
ኃይለ ስላሴ አስጠርተውኝ ሰውን ሁሉ አስወጡና ብቻችንን ቀረን፤…ለምንድን ነው ሃይማኖትህን የለወጥኸው?
ነገሩ ግራ ስለሆነብኝ ፈገግ ብዬ ‹‹የነገረዎት ሰው ተሳስቶአል፤ሃይማኖቴን
ለውጬ አላውቅም፤…የለም ድሮ ቤተ ክርስቲያን ታዘወትር ነበር፤አይደለም?‹‹ዱሮ ቤተ ክርስቲያን አዘወትረ ነበር፤አፆም ነበር፤አቆርብ
ነበር፤አሁን ይህንን ሁሉ አለማድረጌ ሃይማኖት መለወጥ አይደለም፤››…ታድያ ምንድን ነው?‹‹የክርስቶስ ትእዛዞች በጣም ከባዶች ናቸው፤ለነገ
አታስብ ይላል፤እኔ ሎጆች አሉኝ፤ግራህን በጥፊ ሲመታህ ቀኝህን ስጥ ይላል፤ እኔ መልሼ መማታት ይቃጣኛል፤…፤››
ከላይ ያሰፈርኳቸው ጥቅሶች በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያ የተፃፈውና ‹‹አገቱኒ››
የተባለ መፅሐፍ በመቀንጨብ ነው፡፡ ፕሮፌሰሩ በዘውዳዊውና በወታደራዊው ነፍሰበላ አገዛዞች ቀንደኛ የውስጥ አማካሪም ባለስልጣንም
ነበሩ፡፡ እነዚያ አገዛዞች የኢትዮጵያ ማሕበራዊ፣ምጣኔ ሃብትና ፖለቲካ ለጀብድ ሲሉ ብቻ በመደፍጠጥ እንዳልነበረ አድረገውታል፡፡እርሰ
በርስ መጠላለፍ፣መገዳደል፣ጎራ እየለዩ መዋጋት እንደ ዘላቂ መፍተሔ በመፈረጅ የአንድ ምእተ ዓመት ትውልድ እርሰ በርሱ እንዲፋጅ
አድርጓል፡፡የፈጣሪ መልክተኛ በማስመሰልና‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም›› በሚል ባዶ መፈክር ሃረራችን በሁሉም ዘርፍ በመጨረሻ ደረጃ እንድትቀመጥና
የዓለም የድህነት ተምሳሌ እንትሆን ነበር ያደረጓት፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን አፄ ሃይለስላሴና የደርግ ባለስልጣናት በግል አግኝተው የማነጋገር
ዕደሉ ነበራቸው፡፡ ስልሳዎቹ የንጉሱ ባለስልጣናት እንዳይገደሉ፣የጊዜው ምሁራን በቀይሽብር ንጭ ሽብር እንዳይጨፋጨፉ ግን አልመከሩም፤ሐሳብ
አላስቀየሩም፡፡እንዳውም በእሳት ላይ ጋዝ የማርከፍከፍ ስራ ያከናውኑ እንደነበር ነው የታሪክ ድርሳናት የሚያወሱት፡፡በጣም የሚያሳዝነው
ግን ያ ከፋፋይና ጠበኛ አባዜያቸው በ80 ምንናምን ዓመታቸውም ጭምር ከማሻሻል ይልቅ እያባባሱት ነው ያሉት፡፡ለማስመሰል ያህልም
‹‹ከደሙ ንፁህ ነኝ›› በሚል ጲላጦሳዊ አባባል ተጠምደው ይገኛሉ፡፡
በባህላችን መሰረት የሽምግልና ዘመን ለስጋ የሚተጋበት ሳይሆን በቁርባን(ስጋወ
ደሙ በመቀበል)፣በፆም፣በፀሎትና በስግደት የሚተጋበት ነበር፡፡ስጋን አሸንፎ ለንብስ የሚኖሩበት ጊዜ እንደ ፍንዳታ ጠብያለሽ በዳቦ
እያሉ ያችንም ያንንም መንተንኮስ እብደት ነው፡፡ቆዳ ሲሸበሸብ አንደበት መሰብስብ አለበት፡፡አስከ ወገብ ድረስ መቃብር ውስጥ ሰምጦ
እንደ ሰማ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ መለብለብ የመጃጀት ምልክት ነው፡፡
አገቱኒ፣ ገፅ 144
ፕሮፌሰር የአውራጃ ገዢ ሁኖ መመደብ እነዲህ አቀለሉት
እሳ?የሚቆረቆሩለት ማሕበረሰብ የማገልገል ፍላጎት ቢኖርዎ ንሮ እንዲህ ባላማረጡ ነበር፡፡እውነተኛ አገልጋይ ገጠርና ከተማ በማለት
አያሳብብም፤ የደረጃ ከፍና ዝቅ ማለትም አያሳስበውም፡፡እርሶ ግን ‹‹ደርግ መጥቶ ገላገኝ›› ነበር ያሉት፡፡ዳሩግን ደርግ እርሶን
ቢገላግልም ኢትዮጵያውን እናቶች ላለመውለድ እስኪሳሉ ድረስ ልጆቻቸውን በግፍ ጨፍጭፎባቸዋል፡፡ለዘጠኝ ወራት በማሕፀናቸውን ተሸክመው፣ለዓመታት
አዝለውና አጥብተው በስንት መከራ ያሳደጉትን ልጅ አጋድሞ በሬሳው ላይ እንዲደንሱና ለተገደለበት ጥይት እንዲከፍሉ አስገደዷል፡፡
እውነትዎ ነው ፕሮፌሰር ያኔ(በደርግ ዘመን) ማነጋገርና
ሐሳብ ማስቀየር ይችሉ ነበር(ለዛም ነበር ሃገራችን በእርሰ በርስ ጦርነት ተጠምዳ በልጆችዋ ደም ስትታጠብ የነበረው)፡፡ አሁን ግን
እያጎዊ ደባቸው ተደርሶበታልና ማንም ጆሮ ሊሰጣቸው አይፈልግም፡፡ከፓርቲ ወደ ፓርቲ የሚያደርጉት ዙረትም በዱላ ከመመዣረጥና በድንጋይ
ከመፈነካካት ውጪ ያሰቡት ትርፍ አላስገኘላቸውም፡፡ማንነትዎ አንዴ ንፋስ ገብቶበታልና በሄዱበት ሁሉ ቀድሞዎት ከች ይላል፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን በቅርቡ ለሕትመት ባበቁት ‹‹መክሽፍ
እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› መፅሐፍ ምክንያት አነጋጋሪነታቸው ይበልጥ ጨምሯል፡፡ከድያቆን ዳኒኤል ክብረት ስለመፅሐፉ አስተያየቱን ሰጥቶ
ነበር፡፡የፕሮፌሰሩ መልስ ግን አይጣል ነው፤ የወረወሯቸው ቃላት ከአንድ የስማንያ ምናምን አዛውንት አይጠበቁም፡፡ ያውቃል እንዲባል የሚፅፍ፣የደብተራ ተንኮል፣አንባቢ
እንዲባል መፅሐፉን ሰያነብ አቢቤዋለሁ የሚል ጉረኛ እና በሌሎች ሐይለቃላት ወርፈውታል፡፡በዚህ የተነሳ ብዙ አንባቢዎች የታዘቡትን
ፅፈው ነበር፤ አርሳቸውን ደግፈውና ነቅፈው፡፡
በፕሮፌሰሩ አስተሳሰብ የእርሳቸው መቃወም፣አለማንበብ፣የግል
አስታየት መስጠት ‹‹(ድቁንናውን ሆን ብለው ትተውታል) የዳኒኤል ጭፍሮች›› አሰኝቷል፡፡ ደጋፊዎቻቸው ግን ‹‹ጭፍሮች›› አይባሉም…
የእውቁ ፕሮፌሰር አድናቂዎች ናቸዋ!ደግሞ የርሳቸው ፅሑፍ ቢያነቡም ባያነቡም አዋቂዎች ናቸው… የሚጠበቅባቸው ፕሮፌሰሩ ቢሳሳቱም
ባይሳሳቱም(ለነገሩ ፕሮፌሰር ተብሎ አይታሰብም) የድጋፍ ጭሆት ማስተጋባት ብቻ ነው፡፡እንደውም ይህን ዓይነቱ በአመክንዮ ያልተደገፈ
የድጋፍ ሆይ ሆይታ ሳይሆን አይቀርም እንደ ቅማል አናት ላይ እንዲፈናጠጡ ያደረጋቸው፡፡‹‹ ውሻ ከሮጡለት፣ ልጅ ከሳቁለት›› ይባል
የለም?
ዱሮውንስ ከዘውዳውያንና አምባገነናውያ ደርጎች ጋር ስልጣን
ከተጋሩ እስስቶች ምን ይጠበቃል?የዘውዳዊው ስርዓት ባለስልጣን፣የአምባገነኑ የደርግ ስርዓት መካሪና የመርማሪ ኮምሽን ሊቀ መንበር፣
የኢሰመጉ መስራች፣የተልያዩ የፖለቲካ ፓሪቲዎች አባል… በቃ እንደ እስስት ከሳሩም፣ከቅጠሉም፣ከድንጋዩም፣ከእንጨቱም፣ከሰይጣኑም፣መልአኩም
ለመመሳስል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡
የሚገርመው ግን አንድም አልተሳካላቸውም፤ ሁሉም ‹‹ከሽፎባቸዋል!››፡፡ለዛም
ሳይሆን አይቀርም የራሳቸው መክሽፍ በኢትዮጵያ ታሪክ መክሽ በማስመሰል የሞንጫጨሩት፡፡ያ ቆሽታቸው አሮ፣ህሊናቸው በስሜት ደምብሮ፣ዓይናቸው
በጥላቻ ታውሮ እንደ ሰካራም የታፈነ ምስጢራቸውን የገነፈሉበት መፅሐፍ አለማንብብ ‹‹በአላዋቂነት›› የሚያስፈርጅ ከሆነ አላዋቂው
ሌላ ሳይሆን ራሳቸው ናቸው፡፡ ምንም እንኳ የፕሮፌሰርነት ማዓርግ ቢከናነቡም በአንድ የእውቀት ዘርፍ ብቻ መሆኑን ማወቅ ነበረባቸው፡፡
መፅሐፋቸው እንድናነብላቸው ከፈለጉም የአፃፃፍ ስነ ስርዓት ተከትለው መፃፍ
እንዳለባቸው ማወቅ ነበረባቸው፡፡በድርብ ሰረዞች የተሰረዘና የአንባቢን ክብር ከግምት ውስጥ ያላስገባ የግል ድንፋታ አጭቆ የግድ አንብብ ማለት የአንባቢ
ምርጫ አለማወቅ ነው፡፡ያለነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን መሆኑን አልባነኑበትም ሽማግሌው፤ በመረጃ ብዛት(information
overload) የተጥለቀለቀ ዘመን ነው ዘመኑ፡፡የጊዜ እጥረት እንጂ የመረጃ እጦት ታሪክ ሆኗል፡፡
ፕሮፌሰር ‹‹ምንም ስለማያውቁ መፅሐፉን አለነበቡትም››
አሉን አይደል? ከአክብሮት ጋር በጣም ተሳስቷል፡፡አንድ መፅሐፍ ከልተነበበ የአንባቢው ችግር ሳይሆን የፀሐፊው ግድየለሽነት ወይም
የችሎታ ማነስ ነው የሚያሳየው… ሌሎች ፕሮፌሰሮች እንዳስተማሩን ከሆነ፡፡ጊዜው የሻገተ፣የሸበተ፣እጅ እጅ የሚል ወዝ የሌለው ፅሑፍ
ለማንበብ የሚያስገድድ አይደለም፡፡ብዙ እጅግ በጣም ብዙ በሆኑ አማራጮች የተንበሻምበሸ ዘመን ነው ያለነው፡፡
ፕሮፌሰሩ የተፉትን ሁሉ እንደ ውሻ ተደፍተው የሚልሱ
አፋሽ አጎመባሾቻቸው ‹‹የኢትዮጵያ የነፍስ አባት›› ስላሏቸው ብቻ ራሳቸው እንደሊቅ ቆጥረው ‹‹እኔ የፃፍኩት ካላነበባችሁ፣ያልኩትን
እንደ ውዳሴ ማርያም ካልደገማችሁ፣ አዋቂዎች አይደላችሁም፡፡›› ማለት ራሱን የቻለ አላዋቂነት ነው፡፡ለነገሩ አፍንጫ ላይ ያለ ቅርናት
ሽታ ለሌላ ሰው እንጂ አፍንጫው ለተነከረው አይሸተውም፡፡

What is the point? Right your first book and argue with facts we are sick of rumors.
ReplyDeletei like this tsihuf .mesfin is a great animal not professor.
ReplyDeleteMinew Mengistu yane mesfinin begelagelin gadoch!!!!!!
ReplyDelete