በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ በተነሳው ግጭት ዘጠኝ
ባለስልጣናት ጨምሮ ብዙ ዜጎች ተገድሏል
የአማራና የትግራይ ተወላጆች እየተጨፈጨፉ ነው
በጋምቤላ ክልል፣ጎደሬ ወረዳ መጢ ከተማና አከባቢው
በደርግ ዘመን የሰፈራ ፕሮግራም በክልሉ የሰፈሩ የአማራና የትግራይ ተወላጆች ‹‹አከባቢያችን ልቀቁ›› በሚል ሰበብ እየተጨፈጨፉ
ነው፡፡አከባቢያችንን ልቀቁልን ባዮቹ አማፂዎች የህፃናትና ወጣቶች አንገት በገጀራ እንደሚቀሉ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡ጨፍጫፊዎቹ የአከባቢው
ባላባቶች ነን ባዮች ሲሆኑ የታጠቁ ፖሊሶችና ማልሻዎችም እንደሚገኙበት ታውቀዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ትናንት የደረሰ ቢሆንም በጣም
ዘግይቶ በመድረሱ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሊታደግ አልቻለም፡፡በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ግርግሩን ለማብረድ ወደ
አከባቢው ቢንቀሳቀሱም ቀውሱን ሊቆጣጠሩት እንዳልቻሉ ነው የሚነገረው፡፡ አብዛኛዎቹ የአማራና የትግራይ ተወላጆች ቤትና ንብረታቸውን
ጥለው ከ19 ኪ.ሜ በላይ በእግራቸው በመሸሽ በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማ እንደሚገኙ ምንጮቼ ገልፀውልኛል፡፡
እነዚህ ዘጎች ቤትና ንብረታቸው ጥለው ለመሸሽ በመገደዳቸው ያለ ምግብና መጠለያ
በቴፒ አየር ሜዳ ላይ ይገኛሉ፡፡በመሆኑም ወደ ቤተሰቦቻቸውን በመደወል የድረሱልን ጥሪዎች እያሰሙ መሆኑን ታውቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment