Thursday, December 20, 2012

ህልም ወይስ ሸክም?





ምን ዓይነት ቀን ነው እባካችሁ?
መላቅጡ ጠፍቶባችሁ፣ ወረዳችሁ፣ወጣችሁ
እንደገና አሁንም ወረዳችሁ ደግሞ ወጣችሁ
ሄዳችሁ፣ሄዳችሁ፣ሄዳችሁ ደግሞ ተመለሳችሁ
ጥበበኛውን ጠይቃችሁ፣ ጥበቡን ተቀዳጃችሁ፡፡

አቤት መገላገል!እንዲህ ነው መታደል
እናንተን ብያርገኝ፣ ከሰው ብስተካከል
የምን ዕረፍት ማጣት?የምን መንቀዋለል?

ምንድን ነው ምስጢሩ?
ምን ነበረ ምክሩ?
የጥበብ ነገስታት ንገሩኝ ዝርዝሩ
አንድም ሳታስቀሩ፡፡

ደከምከም ብሎኛል፣ተጫጭኖብኛል
ሂድ! ሂድ አንተ! በል ቀጥል!ይለኛል
 እሺ ምን ላድረግ? ምን ይሻለኛል?

ምንም ሱስ የለኝም፣ ምንም አልለመድኩም
አልቅምም፣ አላጭስም፣ ምንም አልጠጣም
ብቻ ግን፣ ምን እንደሆነ ባይገባኝም
የሆ ነገር አለ፣ ለሊት እማያስተኛ
ቀን ዕረፍት አይሰጠኝም፣አይገረምም?
በቃ
ሲርበኝ እበላለሁ፣ውሃም እጠጣሎሁ
ከዚ በላይ ለኔ? ምን አድርገዋሎሁ?

ብርድ ብርድ ይለኛል፣ ፍርሃት ይሰማኛል
ደግሞ ይሞቀኝና፣ ብርታት ይሰጠኛል

ኡፍፍፍፍህ!አሁን አወቅኩት
ግን እንዴት ርሳሁት?
ማማጡን ሲያስፈራኝ
ጊዜው ቢረዝምብኝ
ያረገዝኩት ህልሜ፣ አፍኜ ገድልኩት?

No comments:

Post a Comment