ቢከፋን ቢደላን ዘላለም ላንኖር
ምነው ባንጣላ ሁሌም ብንፋቀር?
እውነትን አጣምመን ውሸት በንናገር
አብረን ጥረን ግረን ብናሳድግ ሃገር
አገር ወገን ትቶ ማን ይሰደድ ነበር
ባናስቀይም ወንድም ባንጎዳ እህት
ከምር በንዋደድ አበረን ብንደሰት
ሌላ ባልፈለግን እችው ነች ገነት
ገሃንም ያደረጋት የፍቅር እጦት
ቂምበቀሉን ትተን ከልብ ብንዋደድ
ስስት ምቀኝነት ተንኮል ብናስወግድ
ለኔ ብቻ ባንሆን ጥቅም ባናሳድድ
እህት ወንድሞች ነን የለንም ባዕድ
ግንዱኮ አንድ ነው የሰው ልጆች ሁሉ
ጥቁር ሆነ ቀዩ ነጭኑም በትሉ
ቤተሰብ ነንና ይቅር መጋደሉ
ጭቅጭቅ ንትርክ ጥላቻ በደሉ
በቃ! እንበለው ይቅር ተባባሉ
ክርስትያን ፓጋን እንዲሁም ሞስሊም
በፖለቲካ እምነት በርእዮት ዓለም
መፎካከር ይቅር መሬት አትጨልም
እርሰ በርስ ተከባብረን እንኑር በሰላም!
ታሕሳስ
22 ቀን 2003 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment