የቢግ በራዘር አፍሪካ(ወንድም ጋሼ) ሬያሊቲ ሾው አዘጋጆች የዲ.ኤስ.ቲቪ ባለቤቶች ሲሆኑ ዓላማቸውም በማስታወቂያ የሚገኘውን
ገንዘብ ማግበስበስ ነው፡፡ስፖንሰሮቹ ኮካኮላ፣ታላቁ የህንድ ቴሌኮም
ካምፓኒ ኤርቴልና ኤም-ኔት ናቸው፡፡የነዚህ ካምፓኒዎች ዋና ዓላማ ገበያቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስፋፋትና ተወዳዳሪዎቻቸውን ከገበያ
ውጪ ማድረግ ነው፡፡የህን የሚያደርጉት ደሞ ከልክ በላይ ስነምግባር በጎደለው መንገድ ነው፡፡አሁን ደሞ ልቅ የሆነ ወሲብ ማስተላለፍ
ጀመሯል፤ መምህርት ተብየዋ እህታችን ቤቲም የመጀመርያዋ አፍሪካዊ ልቅ ወሲበኛ(porn star) ሆናለች፡፡
ልቅ ወሲብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተወገዘ ተግባር ቢሆንም በበይነ መረብ አማካኝነት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ለዚሁ መስፋፋት
ግንባር ቀደምት ደሞ ህገ ወጥ የሆኑ የወሲብ ተቋሞች ናቸው፡፡እነዚህ ተቋሞች ብዙ ወጣት ሴቶችን በማስገደድ የወሲብ ግርድና ወይም
ባርነት እንዲገፉ ያደርጓቸዋል፡፡የባስ ብለውም ተገድደው ያደረጉት የወሲብ ቅሌት በድረ ገጾቻቸው በመልቀቅ በዓለም ደረጃ እንዲታዩ
ያደርጋሉ፡፡በተለይ ደሞ ወጥ የሆነ የበይነ መረብ ህግ ቤለላቸው ሃገሮች፡፡
አሁን ግን ዲ.ኤስ.ቲቪ ያለማንም ሃይ ባይ እነዚህ ልቅ ወሲቦች ለተመልካቾቹ በቀጥታ እያስተላለፈ ይገኛል፡፡ለዛውም በአፍሪካ ስም!፡፡ስለሆነም ማንኛውም የወሲብ በይነ
መረብ በየትኛውም ሃገር ህገ ወጥ በመሆኑ እንደሚዘጋው ሁሉ የህ የልቅ ወሲብ ቴሌቪዥን ጣብያም ህገወጥ ሆኗልና በሃገራችን ኢትዮጵያ
መታየት የለበትም እላለሁ፡፡ግለሰቦች የፈለጉት የማድረግ መብት ስላላቸው በቢግ በራዘር አፍሪካ መሳተፍ አትችሉም ልቅ ወሲብም አትፈፅሙም
ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ነገር ገን የኢትዮጵያ ባንዴራ እንደመለያቸው መጠቀም የለባቸውም፡፡ለባንዴራችን ህልውናና ክብር ሲባል
ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቻችን ደምቷል፤ ተሰይፏልና፡፡
በርካሽ የቴሌቪዥን ጣብያ አማካኝነት ርካሽ የሆኑ ወገኖች ሊያረክሱት አይገባም፡፡ልቅ ሰዎች ልቅ ዓላማቸውን ወደሚፈፅሙበት
ስፍራ በመለያነት አንግበውት የሚሄዱ ሳይሆን የሃገራችን መከታ የሆነው ጀግና ሰራዊታችን ህይወቱን ለመገበር ሲመርሽ በክብር የሚያነግበው፤ ምንጊዜም የሃገራችው አምባሳደሮች
የሆኑ ድንቅ አትሌቶቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ የሚያደርጉት ድንቅ መለያችን ነው፡፡
ስለሆነም እንዚህ ርካሾች የሚሳተፉበት፤ልቅ ተግባራቸውን በቀጥታ ለዓለም የሚያስተላልፉበት ዲ.ኤስ.ቲቪ በሃገራችን መታየት
የለበትም፡፡ልክ እንደሌሎች የወዲብ በይነመረቦች መዘጋት አለበት፡፡
No comments:
Post a Comment