ጉንበት 25 ቀን 2005 ዓ.ም (አዲስ አበባ) - በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ መንግስ ሊመልሳቸው ይገባል ያላቸውን ጥያቅየዎችን በማስማት በሰላም ተጠናቅቋል፡፡ስማያዊ
ፓርቲ ‹‹መንግስት በ3
ወር ውስጥ ጥያቄያችንን ካልመለስ በተጠናከረ መልኩ ድምፃችንን እናሰማለን!›› በማለት
ዝቷል፡፡
ከጥያቄዎቹ መሃልም ያለ አግባብ
የታሰሩ የፖለቲካ ፣የሀይማኖትና
የህሊና እስረኞች ይፈቱ፡፡ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአግባቡ
ወደ ቦታቸው ይመለሱ፡፡ አፈናቃዮችም
ለፍርድ ይቅረቡ፤ የኑሮ ውድነቱ ዘላቂ
መፍትሔ ይሰጠውና ሌሎችንም
ጥያቄዎች ይገኙባቸዋል፡፡
ከሳምንታት በፊት በፌስ ቡክና በሌሎች ማህበራዊ ድረ ገፆች የህገ መንግስቱ
አንቀፅ 30ን በመጥቀስ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችን ይመለስ›› በሚል መፈክር ሲስተጋባ የነበረው ጥያቄ በ50ኛው
የአፍሪካ ህብረት የወርቅ እዩበልዩ ምክንያት ለዛሬ መተላለፉን ፓርቲው መግለፁ ይታወሳል፡፡
በዚህ
መሰረት ሰልፉ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ስምንት ድረስ በፍፁም ጭዋነትና ሰላማዊ በሆነ መልኩ የተካሄደ ሲሆን ቀበና
ከሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት አንስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርቸር ጎዳናዎችን በማምራ መድረሻውን ኩባ አደባባይ አድርጓል፡፡
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በ1997
ዓ.ም የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ አመፅ አምርቶ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት በመቅጠፉ በሃገራችን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት አመፅ እንደ መጥራት ተደርጎ ሲወሰድ የኖረ ሲሆን የዛሬው
ሰልፍ ይህን ፍራቻ ሊያስወግድ ይችላልና በጣም የሚበረታታ ነው፡፡ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የዚሁ ዓይነት ሰላማዊ ትግል ሊከተሉት
ይገባል፡፡ በውጭ ሃይሎች የሚሽከረከሩ፣ አሜሪካና አውሮፓ ደምነው አዲስ አበባ ላይ ንፋስና በረዶ የቀላቅለው የሚያዘንቡ አለመሆናቸውን
የጥፋት መልእክተኞች አለመሆናችውን ያስመሰክራሉና፡፡
No comments:
Post a Comment