![]() |
| Ana Gomes |
አና ጎሜዝ ‹‹በብዙ ኢትዮጵያውያን ሃና ጎበዜ››
ተብላ እንድ ምትጠራ አዲስ ስታንዳርድ ድረ ገፅ አስነብቦናል፡፡ግን ለምን ሃና ጎበዜ ተባለች?የነገደ ጎበዜ(ዶ/ር) ታናሽ መሆንዋን
ነው?ይህ ከሆነ ታድያ የጎበዜ ልጆች ለሰይጣናዊ ስራዎች የተፈጠሩ ናቸው እንዴ?
ነገደ ጎበዜ የመኢሶን ከፍተኛ አመራር ነበር፡፡ከደርግ በለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ኢህአፓዎች ከያሉበት እየተፈለጉ
በቀይ ሽብር እንዲረሸኑ ከደረጉ ነፍሰ በላ ቶክላዎች በግንባር ቀደምትነት ይሰለፋል፡፡በ97ቱ የምርጫ ወቅትም ብሔር ከብሔር ጋር
በማጋጨት የኢትዮጵያ ሰለም ለማናጋት በየድረ ገፁ ብዙ ዘመቻዎች ማካሔዱ አይዘነጋም፡፡እንደውም እርጅና ካልተጫጫነው በስተቀር አሁንም
ቢሆን ከዚሁ የፀረ ሰላም አቋሙ ከማራመድ ዝንፍ ሊል እንደማይችል በቅርበት የሚያውቁት ያውቃሉ፡፡
ሃና ጎበዜም ልክ እንደ ነገደ ጎበዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የቀለም አብዮት እንዲካሄድ ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ሌላው ቀርቶ ባልዋን አውሮፓ አስቀምጣ ከብርሃኑ ነጋ(ዶ/ር) ጋር ከመማገጥ ወደ ኋላ አላለችም፤ብርሃኑ በድህንነቶችና በፖሊሶች እንዳይ ይያዝ ለመከላከል በሚል ሰበብ በሸራተን ሆቴል እንድ እንሶላ ተጋርቷል፡፡
ያ ቅሌትዋን ያጋለጡት ጋዜጠኞች ቢሆኑም እስከ አሁንም ድረስ ቀንድ አብቅላ ለመዋጋት እስኪያምራት ድረስ የሚያቅበዘብዛት
ግን ከአንድ ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያን ሄራልድ ያወጡት ፅሑፍ ነበር፡፡ፅሑፉ ጭብጥ ‹‹ፍቅርበምርጫ ላይ ምን አገባው?›› የሚል ሲሆን የሃና ጎበዜ ፍርደ ገምድል የምርጫ ሪፖርት በአመክንዮ ባዶ የሚያደርግ ነበር፡፡የጠ/ሚኒስትሩ
ፅሑፍ ታድያ በበርካታ የአውሮፓ ህብረት በለስልጣናት ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ የሃና ጎበዜ ታማኝነት በጥያቄ
ውስጥ ያስገባ ስለ ነበር፡፡
በዚህ ምክንያት የጠ/ሚኒስተሩን ስብእና ለማጉደፍ ያልሸረበችው ሴራ እልነበረም፡፡የዴሞክራሲ አለመስፋፋት፣የመልካም
አስተዳደር እጦት፣የሰብአዊ መብቶች አያያዝ፣የፕረስ ነፃነትና ሌሎች እንከኖችን እንደ ምክንያት በማቅረብ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት
እርዳታ ሊሰጠው አይገባም፤እንደውም ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል›› በማለት ብዙ ጊዜ ተከራክራ ሰሚ በማጣትዋ አሁንም ድረስ እንደ ተልባ
እየተነጣጣች ትገኛለች፡፡
ሰትዮዋ በተለይም ባለፈው ሳምንት በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ በመጣችበት ወቅት በሪፖርተርና በአዲስ ስታንዳርድ ቃለ መጠይቅ የተደረገች ሲሆን
በቃለ መጠይቁ ላይ ስለጠ/ሚኒስትሩ ባይነሳባትም እርሷ ግን የሰጠቻቸው መልሶች ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም የሚያጎድፉ አጉል ቃላ
በመዘርዘር ተጠምዳ ነበር፡፡
ለምሳሌ የአዲስ ስታንዳርዱ ጠያቄ ስለ መለስ ምንም
ባያነሳባትም እርሷ ግን 11 ጊዜ ስሙን በማንሳት ልትወነጅለው ሞክራለች፡፡በሁለቱም ቃለመጠይቆች ግን የኢትዮጵያ ችግሮች እንዳለ
መለስ የፈጠራቸው ናቸው በማለት አይኖችዋን በጨው አጥባ ተናግራለች፡፡ይህ ደግሞ ሃና ጎበዜን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ቴፕ ሪኮርደር
ያስቆጥራታል፤ አክራሪዎቹ የድያስፖራ ተቃዋሚዎች የሞሏትን ብቻ ነበርና በእነዝያ ቀለ መጠይቆች የደገመቸው፡፡
እነ አለማዮ ገብረማርያም(ደ/ር አል ማርያም)፣ኤልያስ
ክፍሌ፣ብርሃኑ ነጋና የኢሳት ኣራጋቢዎችና ሌሎች የወሸከቱትን ሁሉ ደግማዋለች፡፡እነሱ በጠ/ሚኒስተር መለስ ሞት የተደሰቱት ያህልም
ደስታዋን ገልፃለች፡፡ግን ሰው በሞመቱ እንዴት ነው ደስታ ሊሰጥ የሚችለው?ሌላው ይቅርና በውግያ ላይ የነበሩ ወታደሮችም ጠላታቸውን የሚገድሉት
እጅ አልሰጥም ብሎ መዋጋቱን ከቀጠለበት ብቻ እኮ ነው፡፡
ማንም ሰው ይወለዳል ይሞታል፡፡ልደትና ሞት የማይነጣጠሉ
የአንድ ሳንቲም ገፅታዎች ናቸው፤‹‹ንሮ ንሮ ከመሬት…›› ይባል የለም? ህይወት ወደ ኋላ እንድ ንጓዝ አትፈቅድልንም፤እስካሁን ባለው
የቴክኖሎጂ እድገት መሰረትም ማናችንም ብንሆን ከመቃበር አናመልጥም፡፡ድሮም ዘንድሮም የሰው ልጅ ይወለዳል…ይሞታል፡፡
ይህ ነገር በጠ/ሚኒስተር መለስ ሞት የተደሰቱትም
ይጨምራል፡፡እንዚህ የአንዲት ሃገር መሪ በመሞቱ እየተደሰቱ ያሉ በጥላቻ ታውረው ማሰብ የተሳናቸው ሰዎችም ነገ ወደ መቃብር ይወርዳሉ፡፡በተለይም
ሃና ጎበዜ በሚቀጥለው ጥሪ የ60 ዓመት ሽማግሌ ትሆናለችና ከዚህ ዓለም የምትሰናበትበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

Just stay calm and read or try to study what the realty and history of our politics are...... I think you are technically too young to write for a mass .... i regret for the minutes you took out of my day... please go home and read little baby...
ReplyDelete