Sunday, December 8, 2013

‹‹ብዙ ሚልዮነሮች እንዳሉን መነገሩ ሰምቻለሁ። እኔ ግን ቅሬታ አለኝ›› አብራሃ ደስታ




አብራሃ ደስታ የዓረና ፓረቲ ከፍተኛ አመራር ሁኖ ከተመረጠ ወዲህ ‹‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ›› ነገር ሁኖላችኋል፡፡የሚፅፋቸው ነገሮች እርሰበርሳቸው የሚጣረሱና ታማኝ ምንጭ የሌላቸው የፈጠራ ወሬዎች ብቻ እየሆኑ ነው፡፡የሚፅፋቸው ነገሮች ምንጭ አልባ ከመሆናቸው በተጨማሪ ትናንት የፃፈው ዛሬ ራሱ ያፈርሰዋል፤ዛሬ የፃፈውን ደግሞ ነገ ይሽሯል፤የነገውም ከነገ ወድያ…

አብራሃ ግን ኢህአዴግን የሚቃወመው ‹‹ህገ መንግስቱ የሰጠን የመናገር ነፃነት እየሻረብን ነው፣ የሃይማኖት፣ሰላማዊ ስልፍ የማድረግ፣የመቃወምና ሌሎች መብቶች እየጠሰ ነው… በአጠቃላይ ቃሉን አይጠብቅም›› በማለት ነው፡፡አብርሃ እንዲህ ብሎ መቃወሙ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት ቃሉ ሳይጠብቅ ሲቀር እንደሚቃወመው ሁሉ እራሱም ቃሉ መጠበቅ አለበት፡፡ምክንያቱም እሱ ራሱም ፖለቲከኛ ነውና ከወዲሁ እርሰ በርሳቸው የሚጣረሱ ነገሮች መፃፍና መናገር የለበትም፡፡

አብራሃ ፖለቲከኛ ብቻም አይደለም የዩኒቨርሲቲ አስተማሪም ጭምር ነው፡፡አስተማሪ ደግሞ ሁለመናው መልካሙን ነገር የሚያስተምር መሆን ይጠበቅበታል፤ከነዚህ አንዱ ቃል መጠበቅ ነው፡፡ሌላው ደግሞ ነገሮች ሳያጣሩ ለውሳኔ አለመቸኮል ወይም ሊሆን ይችላል ብሎ ብቻ አለመናገር ነው፡፡አለዝያ ገን ምንጩ ያልተረጋገጠ ወሬ ይዞ እምቢልታ መንፋት በስም ማጥፋት ወንጀል ሊያስከስሰው እንደሚችል ማወቅ ይኖርበታል፡፡

ጆሲሮማናት የተባለ የፌስቡክ ተጠቃ አብራሃ ደስታን እስመልክቶ እንዲህ በማለት ፅፏል፡
ኣብርሃን መጀመሪያ በፌስቡክ ሳውቀ ነገሮችን የሚያመዛዝንና ኣንድ ተራ ተቆርቋሪ ግለሰብ፣ ሃሳቡን በነጻነት የሚገልጽ ኣይነት ነበር የመሰለኝ፡፡ የፈለገውን የፖለቲካ ርእዮተኣለም ቢያራምድም የኣብርሃን የተቃውሞ ኣካሄድ በመደገፍ ከብዙ ሰዎች ጋር ተከራከሬኣለሁ፡፡ እየቆየ ሲሄድ ግን ኣብርሃ እኔነት የሚያጠቃውና ለመዋሸት ቅንጣት የማያመነታ ፖለቲከኛ ሆኖ ቀረ፡፡እየቆየ ሲሄድ ግን ኣብርሃ እኔነት የሚያጠቃውና ለመዋሸት ቅንጣት የማያመነታ ፖለቲከኛ ሆኖ ቀረ፡፡
እኔ የአብራሃ ፅሑፎችን የምቃወመው ህወሓትን በመቃወሙ የሚመስላቸው ወገኖች አሉ፡፡ሊመስላቸው ይችላል፤እውነታው ግን እሱ አይደለም፡፡ለእኔ ህወሓትና ዓረና ያው ናቸው፤ ምንጫቸውና አሰራራቸው አንድ ዓይነት ነው፡፡የዓረና መስራቾች በሙሉ የህወሓት ከፍተኛ የአመራር ዓባላት የነበሩ ናቸው፡፡
ያኔ ህወሓት የፈፀማቸው ታሪካዊ ስህተቶች ሁሉ በመፈፀም እኩል ተሳትፏል፡፡ከሌሎች የህወሓት አመራሮች ጋር በስልጣን ባለመስማማታቸው መድርክ ረግጠው ወጥቷል፡፡እነሱ ያሉት ነገር ተቀባይነት ባለማግኘቱና የግል ጥቅማቸው ስለተነካባቸው ብቻ ነው ከህወሓት ጋር የተጣሉት እንጂ ለህዝብ ትግራይ ተቆርቁረው አልነበረም፡፡

የአሁኑ አካሄዳቸውም ቢሆን ህወሓት ከሚከተለው አካሄድ ጋር የተለዬ አይደለም፡፡ህወሓት ደርግን ለማሸነፍ ከሻዕብያ ሳይቀር ግንባር እንደፈጠረው ሁሉ ዓረናም ህወሓት ለማሸነፍ ከአንደነት ጋር ለመዋሃድ እየተማፀነ ይገኛል፡፡የዓረናና የአንድነት የፖለቲካ መርሆች ግን ለየቅል ናቸው፡፡እናም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎችን እንዴት መለያየት ይቻላል?

የዓረና አካሄድ ግን አብራሃ ደስታ ከፍተኛ አመራር ሁኖ ከተመረጠበት ወዲህ በይበልጥ አቅጣጫው እየሳተ ይገኛል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አብራሃ የሚያራምደው ፖለቲካ ዓረና ይዞት ከተነሳው ዓላማ ስለሚጣረስ ነው፡፡ዓረና ለወደፊት ስሙና ዓላማው እስካልቀየረ ድረስ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡በመሆኑም ደጋፊ ማፍራት ያለበት በትግራይ ውስጥ ነው፡፡ይህን ለማሳካትም የትግራይ ህዝብ በሚገባው ቋንቋ መፃፍና መናገር ይጠበቅበታል፡፡አብራሃ ግን በአማርኛ እንጂ በትግርኛ ፅፎ አያውቅም፡፡

ሌላው የአብራሃ ደስታ ችግር ጆሲ ሮማናት በፌስቡክ ገፁ እንደሚከተለው አውስፍሮት ይገኛል፡፡

የኣብርሃ ችግር ኣንዳንድ በጥቅምም በሌላም ምክንያት ኣኩርፈው ወይም  ከህወሃት የተባረሩ ሰዎች ስብስብ የሆነው "ዓረና" ፓርቲ ኣመራር ኣባል መሆኑ ኣይደለም፡፡ የኣብረሃ ችግር የሚያራምደው ፖለቲካ (ፕሮፓጋንዳ) ውሸት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ የኣብርሃ ችግር የሚያወራው ሁሉ ሌሎች ቡድኖችን ለማስደሰት ያለሙ መሆናቸው ነው፡፡ ይሄም ለራሱም ለፓርቲዉም ትልቅ ዋጋ አያስከፈላቸው ይገኛል፡፡ ኣብርሃና ኣረና የከፈሉት ዋጋ ምንድንነው ብትሉኝ እነሱ እንታገልለታለን በሚሉት ክልል ውስጥ ተቀባይነትን ማጣት ነው፡፡ ፌስቡክ ላይ ኣንድ ነገር ቢለጥፍ የሚያንቆለጳጵሱትና የሚያወድሱት ሰዎች ብታዩ ትግራይና ተጋሩ ላይ ጥላቻ ያላቸው ሰዎች እንጂ ስለ ትግራይ ህዝብ የሚያስቡ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ የኣብርሃ ፓርቲ የትግራይ ፓርቲ እስከሆነ ድረስ ደግሞ ደጋፊ መሻት ያለበት ትግራይ ውስጥ ነው፡፡
ወንድማችን አብራሃ ባለፈው ገዜ ‹‹ከትግራይ ሰዎች ባሰባሰብኩት መረጃ መሰረት አንዱአለም አራጌ ተወዳጅ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ሁኗል›› በማለት ፅፎ ነበር፡፡ከዛም ከደጋፊዎቹ ጭምር ጠንካራ ተቃውሞ ደረሰበትና ስህተቱን ከማመን ይልቅ ነገሬው የበሰውኑ ለማድበስበስ ይሞክራል፡፡ቀጥሎ ያለው የማስተካከያ(ማብራርያ) ፅሑፍ ራሱ የፃፈው ነው፡፡
እኔ የፃፍኩት "ከትግራይ ሰዎች" የሚል ነው። እኔ እንደሚገባኝ "ከትግራይ ሰዎች" ማለት ትግርኛ የሚናገሩ ግለሰቦች ማለት እንጂ ትግራይ ህዝብ ወይም የመቀሌ ወይ የሌላ አከባቢ ኗሪዎች ማለት አይደለም። አንድ ሰውም ትግርኛ ተናጋሪ ከሆነ የትግራይ ሰው ነው፤ የትግራይ ህዝብ ግን አይወክልም። ስለዚህ "ከትግራይ ሰዎች" ብዬ ስል ያናገርኳቸው ሰዎች የትግራይ (ትግርኛ ተናጋሪ) ናቸው ለማለት ነው።
ይህ አበባል ትልቅ የአስተሳስብ ህፀፅ አለበት፡፡‹‹አንድ ሰውም ትግርኛ ተናጋሪ ከሆነ የትግራይ ሰው ነው›› ማለት ትግርኛ ተናጋሪዎቹ የኤርትራ ተወላጆችም የትግራይ ሰዎች ናቸው ማለት ነው፡፡አንድ እንግሊዘኛ ተናጋሪም የእንግለዚ ሰው ነው ማለት ነው፡፡እናም አውስትራልያውያን፣ካናዳውያንና አሜሪካውያንም እንግሊዛውያን ሆኑ ማለት ነው፡፡

እናም ይህንኑ የአስተሳሰብ ህፀፅ ደጋፋዎቹን ይባስ አበሳጫቸውና የተቃውሞ ናዳቸው እንደዶፍ ሲያወረዱበት ‹‹ደጋፊ የለኝም፤አያስፈለገኝምም›› እያለ መቀባጠር ጀመረ፡፡አውነታው ግን የዓረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆነው ደጋፊዎች ለማፍራትና ብሎም የስልጣን ኮርቻው ላይ ለመቆናጠጥ ነው፡፡አንድ ህዝብ ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ፓርቲ ደጋፊ ከሌለው በምን መልኩ ነው ዓላማውን ማሳካት የሚችለው?

አብራሃ ህዳር 17 ቀን ‹‹ደጋፊ የለኝም፤አያስፈልገኝምም›› ብሎ ቢፅፍም ከሁለት ቀናት በኋላ ግን ከፌስቡክ እንደሚጠፋ አስታውቆ ለተወሰነ ጊዜ ተሰወረ፡፡የማገገምያ ጊዜው ጨርሶ እንደተመለሰ ግን ሌላ ጭፍን ፍረጃ ፅፏል፡፡ነገሩ እንዲህ ነው፡ ‹‹New World Wealth›› የተባለ ድረ ገፅ በ1999 ዓ.ም 1,300 የበረው የኢትዮጵያውያን ሚልዮነሮች ቁጥር (በዶላር) በለፈው መስከረም ወር ወደ 2,700 ማደጉን ይዘግባል፡፡እንደ ‹‹theguardian›› የመሳሰሉ የዓለም መገናኛ ብዙሓን ደግሞ ይህን ዜና በድረ ገፃቸው ይዘግቡታል፡፡
በዚህ ዜና የተበሳጨ የሚመስለው አብራሃ ደስታም ሁሉንም የኢትዮጵያ ባለሃብቶችን በአልማሚት እንደሚከተለው ፈርጇቿል፡፡
ብዙ ሚልዮነሮች እንዳሉን መነገሩ ሰምቻለሁ። እኔ ግን ቅሬታ አለኝ። 'ሚሊዮነሮች' የሚለውን 'ቢልዮነሮች' በሚል መቀየር አለበት። ምክንያቱም በኛ ሀገር ብዙ ሚልዮነሮች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ቢልዮነሮችም አሉ።እንዴት ሚሊዮነሮች ሆኑ? ሰርተው ነው? ተወዳድረው ነው? አምርተው ነው? ኢንተርፕሪነሮች ስለሆኑ ነው? አይደሉም። የሃብታቸው ምንጭ ሙስናና ኮንትሮባንድ እንደሚሆን ነው የምገምተው።አብዛኞቹ ቢልዮነሮች በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳድረው አሸንፈው ያሰባሰቡት ሃብት አይደለም። ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ከድሃው ሕብረተሰብ ያሰባሰቡት ነው።

ይህ አጉል ፍረጃ ከአንድ ድርጅት ከፍተኛ አመራር ይቅርና ከማንም ጤንኛ አእምሮ ያለው ተራ ሰውም የማይጠበቅ ነው፡፡ሁሉንም ነጋዴዎች (ሚሊዮነሮች) በሃቅ ሰርተው በልፅጓል ማለት

ሊከብደው ቢችልም

ሁሉንም ሚሊዮነሮች ሙሰኞችና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ናቸው ብሎ በጭፍን መፈረጅ ግን ትልቅ ስህተት ነው፡፡አባባሉ በራሱ በስም ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቅ የህግ መተላለፍ ነው፡፡በይንስ ብያንስ እንዚህ ሚሊዮነሮች ሰርተው ያልበለፀጉ መሆናቸው መረጃ ቢኖረውም እንኳ ሙሰኞችና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ናቸው ብሎ መፈረጀ የአብራሃ ደስታ ስራ ሳይሆን የፍርድ ቤት ብያኔ ነው፡፡




አብራሃ ደስታ የባለሃብቶቹ ሙስኝነትና የኮንትሮባንድ ነጋዴነት ማስረጃ ቢኖረውም እንኳ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 20 ንኡስ አንቀፅ 3 መሰረት በወንጀል ሊፈርጃቸው አይገባም፡፡ህጉ እንዲህ ይላል፤ ‹‹የተከሰሱ ሰዎች በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር፣በምስክርነት እንዲቀርቡም ያለመገደድ መብት አላቸው፡፡››አንቀጽ 24 ንኡስ አንቀፅ አንድም‹‹ ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡›› እናም ወንድማችን አብራሃ እንዚህ መብቶቻቸውን አውቆ ሊያከብራቸው ይገባል፡፡

የሚገርመው ነገር ግን እሱ ራሱ ከአሁን በፊት(ህዳር 15) ‹‹ሁሉንም ነጋዴዎች ራሽናል(rational) ናቸው›› የሚል አቋም ይዞ ይከራከር መኖሩን መርሳቱን ነው፡፡የመቐለ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ መንግስት ሰለሚያስገድዳቸው የንግድ ቤቶቻቸው እየዘጉ መሆናቸውን ለማሳወቅ በፃፈው ፅሑፍ ‹‹አንዲት ሃገር ብዙ ባለሃብቶች ከሌላት የምትሰበስበው ግብር ሰለማይኖር እንደሃገር መቀጠልዋ አጠራጣሪ ይሆናል›› የሚል መልእክ ያለው ፅፎ ነበር፡፡

አሁን ግን ተገልብጦ(የፖለቲካ አኩራባት ስርቶ) እንዝያ ነጋዴዎች እየኮነናቸው ይገኛል፡፡ባለፈው አሞገሳቸው አሁን ወንጀለኞች አደረጋቸው፡፡ይህ አካሄድ የፖለቲካ ታአማኒነቱን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል፡፡አንዴ የገባው ቃል ከወዲሁ ማክበር ካልቻለ የህዝብ አስተዳዳሪ ሁኖ ቃሉን ሊያከብር አይችልምና፡፡

No comments:

Post a Comment