| fanabc |
በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ አከባቢ በተለምዶ
ጆንያ ተራ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር የደረሰው የእሳት አደጋ
32 ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል፤40 ሱቆች ሙሉ
በሙሉ በእሳት ወድሟል እንዲሁም አምስት መጋዝኖችም የእሳቱ ሰለባ ሆኗል፡፡
የእሳት ቃጠሎው የጀመረው 8፡30 ቢሆንም የእሳት
አደጋ ድርጅት ግን መረጃው የደረሰኝ 9፡30 ነው ብለዋል፡፡እሳቱን ለማጥፋት የአዲስ አበባ የአሳት አደጋ ድርጅት፣የኢትዮጵያ አየር መንገድና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በመተባበር
የተሳተፉ ሲሆን ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ውሏል፡፡
በጆንያ ተራ የእሳት አደጋ ሲደርስ ለአምስተኛ ጊዜው ቢሆንም ትናንት የደረሰውን ይህል ግን በመርካቶ ይቅርና በአዲስ አበባ ታሪክም
ተከስቶ እንደማያውቅ ነው ኗሪዎች የተናገሩት፡፡
የእሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ ግን በውል አልታወቀም፡፡
ምንጭ ፡ሬድዮ ፋና
No comments:
Post a Comment