Wednesday, December 18, 2013

ማናቸውን እንመን???


/ አረጋሽ አዳነ ህወሓት ደርግን ለመጣል በካሄደው የ17 ዓመታት ትግል በጋራ ታግሏል፡፡ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከልም አንዷ የነበሩ ሲሆን 1993 . ህወሓት በነአለምሰገድና በነመለስ መካከል ሲከፋፈል ፓርቲው ጥለው ከተሰናበቱ አባላት አንዷ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከህወሓት ከተገነጠሉ ሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ሁነው ዓረና ፓርቲን በመመስረት ህወሓትን በመቃወም ላይ ይገኛሉ፡፡

አብራሃ ደስታም በጳጉሜ ውስጥ በተካሄደው የዓረና ድርጅታዊ ስብሰባ ከፍተኛ አመራር ሁኖ ተመርጧል( በራሱ አበባል ዓረናን በገፀ በረከት መልክ ተስጥቶታል)፡፡ይሁን እንጂ አብራሃ ከዓረናዎች ጋር የማይስማሙ መረጃዎችን እያናፈሰ ይገኛል፡፡ለምሳሌም ህወሓት በአባይ ወልዱ (መቐለ)ና በደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶክተር)(አዲስ አበባ) ቡድኖች ስለመከፋፈሉ ተቃራኒ የሆኑ ሐሳቦች እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
አብራሃ ደስታ ‹‹ህወሓት ለሁለት ተከፈሏል፤በአባይ ወልዱ የሚመራው የመቐለ ቡድንና በደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶክተር) የሚመራው የአዲስ አበባ ቡድን መካከል፡፡››እያለ ይለፍፍ ነበር፤በፌስቡክ አድራሻው፡፡ይህን ማለቱን ሳያበቃም እንደ ‹‹የእንግሊዝ ፕሪመርሊግ ኮመንታተሮች›› አሁን የአባይ ቡድን እያጠቃ ነው፤የህወሓት ስልጣን ሙሉ ለሙሉ ሊቆጣጠረው ትንሽ ቀርቶታል፡፡

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ጣልቃ ገብተው ካልሸመገሏቸው በስተቀር ሽጉጥ ከመማዘዝም ወደኋላ አይሉም፤ ይጨራረሳሉ፡፡ በለው! በለው! በለው… አሁን ደግሞ የደብረፅዮን ቡድን እያጠቃ ነው፡፡የአባይ ቡድን መልሶ ማጥቃቱን መቋቋም አልቻለም፤የስልጣን ሽኩቻው በደብረፅዮን ቡድን አሸናፊነት ሳይጠናቀቅ አይቀርም… ሌላም ሌላም እያለ የፈጠራ ድርሰቱን ሲኮመኩም ነበር፡፡አብራሃ ስለ ህወሓት መከፋፈልና መዳከም ብዙ ነገር ፅፏል፤ ሰብኳል፡፡

አረጋሽ አዳነ ደግሞ ‹‹ ‹ተከፋፍለዋልየሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡›› እያለች ነው፤ ሰሙኑን ከሎሚ መፂሔት ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ፡፡የሎሚና የአረጋሽ ቃለ መጠይቅ ቀርንጭበን እንይ፡፡ሙሉውን ቃለመጠይቅ ይኸውና ያንብቡት

ሎሚ፡- ህወሓትየአዲስ አበባ እና የመቀሌበሚል ቡድን ለሁለት መከፈሉ ይነገራል፤ የኢህአዴግአስኳልነው የሚባለው ህወሓት ውስጥ መከፋፈል መከሰቱ የሚፈጥረው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት ይኖራል?
 
አረጋሽ፡- በህወሓት ውስጥ ክፍፍል አለ፤ ለሁለት ተከፍሏል የሚባለውን ነገር ላውቀው አልቻልኩም፡፡ ክፍፍል አለ ብዬ ለመውሰድ ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡ተከፋፍለዋልየሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ተከፋፍለው አንድ ሆነውም ለመዝለቅ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው የሚለው ጥያቄ ቢነሣ ነው የሚሻለው፡፡
በአጠቃላይ ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፡፡…

የኸው እንግዲህ፤ አብራሃና አረጋሽ የዓረና ቁልፍ ሰዎች ቢሆኑም በዚች ውሳኔም  አልተስማሙም፤ ተቃራኒ ናቸው፡፡ ህወሓት ለሁለት ይከፈል አይከፈል፣ በ10 ቡድኖች ይበጣጠስ ወይም የአንድ ቤተ ሰብ ድርጅት ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም፤ እስካሁን ድረሰ፡፡ታድያ ማናቸውን እንመን???ማን ነው ውሸታም??

1 comment:

  1. It is not uncommon to see people of the same political party with minor differences on some aspects. This is not a big deal for me.

    ReplyDelete