እኛን የሚጠብቀን ድህነታችን እንጂ ድህንነት አይደለም!
እኛ በሰላም ወጥተን በሰላም የምንገባው ‹‹የህዝብ ድህንነቶች›› ስለጠበቁን ሳይሆን ድህነታችን
ሰለሚጠብቀን ነው፡፡እናስተውል ጎበዝ! ድ-ህ-ን-ነ-ት እና ድ-ህ-ነ-ት ለየቀል ናቸው፡፡‹‹ካአሸባሪዎችና›› ማጅራት መቺዎች የሚያስጥለን
ድህነታችን ብቻ ነው፡፡ እንዴት ብሎ የሚጠይቅ ካለ ወደ መልሱ አብረን ትንሽ የሐሳብ ጉዞ እናደርግ ዘንድ በትሕትና እጠይቃሎሁ ፡፡
ለድህነታችን(ይቅርታ ድህንነት አላልኩም)ምስጋና ይድረሰውና የግላችን ቤትና ንብረት የለንም፡፡የተከራየነው
ቤት እንጂ የለበስነው ልብስ እንቀይርም፡፡ ኪሳችን(ምናልባት የለበስነው ልብስ ኪስ ካለው)ባዶ ነው፡፡ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂዎች
ደግሞ ስለኪስ ባዶነትና ሙላት ከኛ በበለጠ ያውቃሉ… ልምድ አላቸዋ፡፡ በአጠቃላይ አኗኗራችን የነሱ ቀልብ የሚስብ አይደለምና ንቀው
ይተውናል፡፡መኪና የለንም፣ልብስ አንቀይርም፣ቤት የለንም፣ኪሳችን ባዶ ነው፤ ስለዚህ በነሱ አመለካከት መጅራት የለንም ማለት ነው፡፡
ድህነት ደብቆታል፡፡ምን አይተው ምናችን ላይ ይመቱናል? ለዚህ ነው ድህነታችን ለድህንነታችን መከታ ነው ያልኩት፡፡
ድህነታችን ከማጅራት መቺዎች ብቻ አይደለም እየጠበቅን ያለው፡፡ ቅድም እንዳልኩት ‹‹ካአሸባሪዎችም››
ጭምር ያድነናል፡፡ አሁንም እንዴት ብሎ መጠየቅ አይከፋም፡፡ምክንያቱም ‹‹አሸባሪዎች›› አንድ እንደኔ ዓይነቱ ምስኪን ድሃ ገድለው
የሚያገኙት የፖለቲካ ጥቅም የለማ፡፡‹‹አሸባሪዎች›› ስያሸብሩ ዓላማቸውን ለማሳካት ነው፡፡‹‹ሃገርና ህዝቦችዋን ለማሸበር?››አይደለም!
ባለስልጣናትን ለማሸበር ነው፡፡ባለስልጣኖችና ግብረ አበሮቻቸውን ለማሸበር ብቻ ነው፡፡እናስተውል!በጠብመንጃና በሳንጃ አስፈራርቶና
አስገድዶ በስልጣን የወጣ ማንኛውም በለስልጣን ስልጣን ከመያዙ በፊት በሌሎች ባለስልጣኖች ‹‹አሸባሪ›› የሚል የዳቦ ስም ተሰጥቶት
ነበር፡፡እናም የዘመኑ አሸባሪዎችም ‹‹በግብረሽብራ›› ድርጅት ላይ የተሰማሩት ባለስልጣኑን ገድለው ስልጣን ለመያዝ ብቻ ነው፡፡ድሃን
ገድለው የድህነት ስልጣን ስለፈለጉ አይደለም!
ድሆችንማ ድህነት እየገደላቸው አይደለም እንዴ?በኮንቴነር ታፍነው፣ በውሃ ጥም፣በረሃብና በድካም
ያለቀባሪና ያለወሬ ነጋሪ በየበረሃው ወድቀው እየቀሩ ያሉት እኮ ድሆችና የድሃ ልጆች ናቸው፡፡ በዓረብ አገሮች በቡድን ተደፍረውና
ከፎቅ ተውርውረው የሚሞቱት የባለስልጣናትና የባለሃብቶች ልጆች ናቸው እንዴ? የነሱ ልጆችማ በመረጡት የዓለማችን ምርጥ ዩኒቨርሲቲ
ተንደላቅቀው እየተማሩ ነው፡፡የነሱ ልጆችማ በሃገራችን በሉት የመከራ የትምህርት ተቋሞች አይማሩም፡፡ሁሉ በእጃቸው ሁሉ በደጃቸው
ነው፡፡
ስለሆነም አሸባሪዎች እንድ ሺህ ድሆችን ከመግደል ይልቅ እንድ ቦርጫምና ራሰመላጣ ባለስልጣን
መግደል ይመርጣሉ፡፡ምክንያቱም ያ ቦርጫም ራስ መላጣ ባለስልጣን ቢገደል የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ስለሚያገኝ የነሱ ስምና ዝና የገናል፡፡ይህ
ነገር የፖለቲካ ተንታኞችና ፕሮፓጋንዲስቶች‹‹እውቅና›› ብለው ይጠሩታል ፡፡አሸባሪዎች የአንድ ባለስልጣን ሂይወት ካጠፉ እውቅና
ያገኛሉ፤ በዛውም የማሸነፍ እድላቸው የሰፋል፡፡ የህ እንዳይሆን ነው ታድያ ‹‹የህዝብ ድህንነት›› ተብየዎቹ በገፍ የተሰማሩት፡፡
የህዝብ ደህንነትና ሰላም ለመከላከልና ለማዳን ሳይሆን ባለስልጣኖችን ለመከላከል ነው፡፡በሌላ አባባል ‹‹የህዝብ ድህንነት›› ማለት
የባለስልጣን አጃቢ ማለት ነው፡፡
በአጃቢዎች የሚንቀሳቀሰው ግን በለስልጣን ብቻ አይደለም… በለሃብትም ጭምር ነው፡፡ከእያንዳንዱ ትልቅ ሃብት
በስተጀርባ ብያንስ አንድ ትልቅ ወንጀል መኖሩን አንዘንጋ፡፡የህ እውነታ ነው ባለሃብቶችም በአጃቢዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚያስገድዳቸው፡፡የቤታቸው
ግቢ ራሱ ከሌሎች በእጅጉ ይለያል፡፡ በስፋቱ፣በተለያዩ ዓይነት አትክልቶች በመሸፈኑና በአሰራሩ ዲዛይንም አይደለም፡፡በአጥሩ ብቻ
ነው፡፡ የባለሃብቶች የአጥር ግንቢ በኤሌትሪክ ሽቦ የታጠረ ነው፡፡ የሌቦችና የማጅራት መቺዎች በህሪ በዛው ስራ ላይ ተሰማርተው
እያሉ የውቁታላ፡፡ማ ማንን ይሸውዳል?
No comments:
Post a Comment