Monday, January 21, 2013

ገጠመኝ




በአንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ በየ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያና በታንዛንያ የሚካሄደው የኳስ ጨዋት እየተመለከትኩ ነው፡፡ ሳላዲን ሰይድ ቅጣት ምት ስተዋል! ወይኔ! ወይኔ! ወይኔ! በቁጭት እርር ድብን በያለሁ… አንጀቴ ተቃጥሎ ቋንጣ ሁኗል፡፡ ጨዋታው አሁንም እየቀጠለ ነው፡፡ የፈጣሪ ያለህ! ጀማል ጣሰው ተጎድቶ ወጥቷል… በስትሬችርና በቀይ ካርድ፡፡ሙዴ ተሰርቋል፤ ተስፋችን እንደ ክር መንመኗል፡፡ኦይ! ኦይ! ኦይ ዛምብያ ጎል አስቆጥሮብናል፡፡
ከራሴ ጋር እየተነጫነጭኩ ጫወታውን መመልከት ቀጥያሎህ፡፡ የመጀመርያውን የጫወታው ክፈለ ጊዜ አልቋል… ዛምቢያ አንድ – ኢትዮጵያ ባዶ! ወይነዶ! ወይነዶ! ወይነዶ! መቼ ይሆን የምንላቀቀው ከጎል መዓት መስተንግዶ?

ከዕረፍት በኋላ የኢትዮጵያ ብዱን ጠንክሮ በመጫወት ላይ ነው፡፡ እኔ አላምንም! አስር ለአስራ አንድ ያጣድፏቿል… ደስ ሲሉ! አዲስ ህንፃ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ገብቷል፡፡ የጨዋታው ሚዛን ኢትዮጵያውን ወስደውታል፡፡ አያጠቁ ነው፤ በጣም ተመስጫሎሁ፡፡ ልቤ ተንጠልጥሏል… እፍ! ወደ አናቴ ሊወጣ ነው፡፡ ሳላዲን ሰይድ ለአዳነ ግርማ፣ አዳነ ግርማ! አዳነ ግርማ!አ…ዳ…ነ!!! !ጎጎጎጎል!በደስታ ሰክሬ እምሆነውን አጥቻሎሁ፡፡ በእጆቼ እያጨበጨበኩ በአፌን አፏጫሎሁ፡፡ 

ድንገት አስተናጋጇ መጥታ ‹‹ምን ልታዘዝ!>> አትለኝም፡፡ ጎል! ጎል! ጎል! ጎሽ የኔ እናት!ጭማሪ ጎል ይዘሽ ነይ፡፡
በሳቅ ፈዳች፡፡ እየሳቀች ሄደች፤ ያዘዝኩት ጎልም አልመጣም ለጀቷም አልተመለሰችም፡፡ በቃ ጨዋታው በዛው አለቀ፡ ኢትዮጵያ  አንድ–ታንዛንያ አንድ፡፡ኢትዮጵያውን በጋራ! ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ታሪክ ሰርቷል፡፡ ያለ አምበላቸው ደጉ ደበበና ቋሚ በረኛው ጀማል ጣሰው፡፡

 መልካም ዕድል ለምርጥ ብሔራዊ ብዱናችን!

No comments:

Post a Comment