Thursday, January 3, 2013




በጣም ካስገረሙኝ ነገሮች!

ድሮ ነው፣ ድሮ… ድሮ… ድሮ እጅግ በጣም ድሮ፣ ህፃን እያሎህ!አንድ የሃገር መሪ ከእገዚሔር ፍቃድ ውጪ ስልጣን መያዝ እንደማይችል ሲነገር እሰማ ነብር፡፡ ‹‹ንጉስ አይከሰስ ሰመይ አይታረስ›› የሚለው አባባልም ዚህን እውነታ የሚያረጋግጥ ነበር የሚመስለኝ፡፡ለምሳሌ አፄ ሃለስላሴ የቅርቡና ምናልባትም የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩ ሲሆን ሙሉ ስማቸውም…ሞአ አንበሳ ዘ እምነገደ ይሁዳ፣ ግርማዊ ቀደማዊ አፄ  ኃይለ ስላሴ፣ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ነበር፡፡እዚ ላይ‹‹ ስዩመ እግዚአቢሔር››የሚል ተጨማሪም አላቸው…በእግዚሔር የተሾሙ መሆናቸውን ለማሳየት፡፡ ፡፡ጳጳሶችና ሼኮችም እገዚሔር ነበር የሚሾማቸው፡፡ አሁን ግን የኦርቶዶክስና የእስለምና እምነት ተከታዮች መንግስትን እየወቀሱ ይገኛሉ፤ ‹‹በሃይማኖታችን ጣልቃ ገባብን›› እያሉ፡፡ ታድያ ያ የሃገር መሪዎችን ይሾምና ይሽር የነበረው እገዚሔር የት ሂዶ ነው አሁን መንግስት የሃይማኖት መሪዎችን መሾምና መሻሩን የተያያዘው? እረፍት ላይ ነው ልበል?ወይስ የኢህአዴግ‹‹መተካካት››ፖሊሲ እዚህም ላይ ይሰራል?

ለነገሩ መንግስት በሃይማኖት ላይ ጣልቃ ምግባት የጀመረው ከሰሎሞን ሰርወ ንግስነት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ዘውዳዊ ስርዓት በደርግ ተገረሰሰ ወዲህ ነው፡፡ ደርግ በእግዚሔር የተሾመ መንግስት አልነበረም፤ ራሱን በራሱ የሾመ ነበር፡፡ኢህአዴግም ደርግን ከጨዋታ ውጪ አድርጎ ስልጣን በክንዱ የተቆነጣጠ ስለሆነ በሃይማኖት ላይ ጣልቃ መግባቱ የቀጠለበት ይመስላል፡፡ የህ ጣልቃ ገብነት ግን ለወደፊትም የሚቀር አይመስለኝም፤ የሃይማኖት ተቋማት እንደ ቫቲካን ካልተገነጠሉ በስተቀር፡፡

ሃይማኖትስ በመንግስት ስራዎች ላይ ጣልቃ ገብቶ አያውቅም ማለት ነው?በደምብ አርጎ ነው እነጂ!ድሮ እግዚሔር ጳጳስ ወይም ሸክ ይሾምና እነዚህ ደግሞ በተራቸው ነገስታትን ይሾማሉ፡፡ ሃይለኛ ንጉስ እነዲሆንም ዝፏናቸው ይባረክ ነበር፤ በጳጳሳት ወይም በሾኮች፡፡ ታድያ አሁን የተገላቢጦሽ ኁኗል፡፡ የሃይማኖት ቶቋማት ደሮ የዘሩትን በማጨድ ላይ ናቸው መሰለኝ፡፡

No comments:

Post a Comment