የኢትዮጵያ ባህላዊ አለባበስ
የሚያሳፍራቸው ዓለም አቀፍ ተወካዮቻችን
እስኪ እንደው ቦሞቴ ከላይ ያለው ምስል እዩና ምን እንደሚሰማችሁ
አስተውሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች( አምባሳደሮች፣ የውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች እና ፕረዚደንቶች)ከኢትዮጵያኖቹን በስተቀር እንድ
በጣም የሚያስደስት ልምድ አላቸው… ሁሌም የአገራቸው በህላዊ አለባበስ ያዘወትራሉ፡፡የኛዎቹ በለስልጣናት ግን ስልጣኑን እንጂ የኢትዮጵያ
ምንነት ስል ማስተዋወቅ ደንታ የላቸውም፡፡ቆይ የኛው እንደ በረዶ የነጣው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚዘወተርው በህላዊ አለባበሳችን ለባለስልጣኖቻችን
እነደ ሰማ ይለበልባቿል ልበል?የደቡቦቹ ዠንጉርጉር
ልባበስስ በነሱ ላይ እንደማያምር ማን ነገራቸው?አፋቸው ሞልተው
ስለ ኢትዮጵያ ከኛ በላይ የሚቆረቆር የለም ብለው የሚጎርኑ ገዢዎቻችን ከዘመን አመጣሾቹ የአዲስ አበባ ‹ፍሪኮች› በምን ይለያሉ?
ሱሪያቸውን እስከ ጭናቸውን ድረስ አውርደው ስላልረገጡ?ሱፍ እንኛ ኢትዮጵያውያንን
ይወክላል ያለቸው ማን ነው?
እስኪ የአዲሱ የውጪ ጉዳይ ምኒስትራችን አለባበስና የናይጀርያው
አምባሳደር አለባበስ እዩልኝ፡፡ስል ውስጣዊ ማንነታቸው ለጊዜው ይቆይልንና ስለ አለባበሳቸው ብቻ ወስደን በንመለከት ብዙ ነገሮችን
መታዘብ እንችላለን፡፡የሰው ልጅ ማንነት የሚገለፀው በዜግነት ብቻ አይደለም፡፡ኢትዮጵያዊ ስንል ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ ስላደገ ወይም
ከኢትዮጵያውያን ስለተወለደ በቻ አይደለም፡፡ኢትዮጵያዊ ምስል(ገፅታ) ስለተላበሰ ብቻም አይደለም፡፡አነጋገሩ፣አለባበሱ፣አበላሉ፣በጠቃላይ
የአኗኗር ዘቤው ኢትዮጵያዊ መምሰል አለበት፡፡ይህ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያዊ
ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ማንኛውም ሰው ደግሞ የራሱ የሆነ ልዩ መለያ(identity) ከሌለው ማንም አይደለም፤ በፍቃደኝነት ሰብአዊ
ማንነቱን አጥቷል፡፡ኢነዲህ ከሆነ ታድያ እንደ እስስት ሌሎችን ለመምሰል ሲሞክር ራሱን ሳይሆን ይቀራል ማለት ነው፡፡ይህ ትልቅ ችግር ነው፤ የራስን ልዩ ማንነት የማጣት ችግር…ፈረንጆቹ
(identity crisis) ይሉታል፡፡
እንዲህ ዓይነቱ ችግር በብዙ የአገራችን ወጣቶች ጎልቶ
ይስተዋላል፡፡የራሳቸውን ማንነት ተፀይፈው ምዕራባውያን ወጣቶችን ለመምሰል ሲጣጣሩ እናያለን፡፡
ግን ደግሞ አይችሉትም፤ አይሆንላቸውም፡፡ይህ ታድያ ራሳቸውና ሃገራቸው ጠልተው የባዕድ ማንነት ናፋቂ ቢሆኑ ምኑን ይደንቃል?
ችግሩ ያለው ከኛ በላይ ላሳር በሚሉ መሪዎችችን ተብዎቹን ላይ አይደለም?የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስት፣ የኢትዮጵያ ፕረዚደንት፣የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስተር
ተብሎ ኢትዮጵያውያንን ከልመሰለ ነፃነታችን ያለው የቱ ጋ ነው?በምዕራባውያን አለባበስ ደምቀው እንዴት አድርገው እኛን ይወክላሉ?ምን ዓይነት ሰዎች መሆናቸው እኮ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡
በተግባርም ሆነ በአምሳል እኛን አይመስሉም፡፡
እነዚህ ዓለም አቀፍ ተወካዮቻችን ባህላዊ እሴቶቻችን
ትተው የምዕራባውያን የመስታወቅያ ታፔላ መምሰላቸው በጣም ያሳዝናል፡፡እነዚህ ሰዎች እኮ እኛን ረግጠው መግዛታቸው ሳያንስ የሃገራችን
ማንነትም ጭምር እየተረማመዱበት ነው ያሉት፡፡ቆይ መቼ ነው እኛን የሚመስሉት?አባባሌ ልክ እንደኛ የነተበ ልብስ ይልበሱ ሳይሆን ያ እንደ በረዶ የነጣው በህላዊ አለባበሳችን በልዩ
ትእዛዝ እያሰሩ ይመሩበት፤ ይድመቁበት ነው፡፡እንድያ ከሆነ ብያንስ ልዩ ማንነታችን በምዕራባውያን ባህላዊ ወረርሽኝ ተሽመድመዶ ድራሹን
አይጠፋም፡፡
በተለይ ይህ ምዕራባውያንን የመመሰል ችግር እጅግ ገኖ
የሚፀባረቀው በየእምነት ተቋማት መሪዎቻችን ነው፡፡እስኪ የጳጳሶች፣የፓስተሮች፣የሸኮች አለባበስ
ታዘቡት፡፡እንደው ተዳፈርክ አተበሉኝ እንጂ የማናቸውም ኢትዮጵያን
አይወክልም፡፡ እዩልኝማ በሞቴ፡፡

'Emanicipate yourself from mental slevery 'Bob didn't say it for the sake of saying it. Now days slavery is a mental one. We are in cultural colonialism. Well the byproduct of it is: losing ones culture. Like Bob aded 'none but ourself can free our mind ' we should start to apreciate our thing again.As our proverb teaches us 'yesew werk ayademek'.
ReplyDelete