Monday, January 14, 2013



‹‹ከያንዳንዱ ትልቅ ሐብት በስተጀርባ ብያንስ አንድ ትልቅ ወንጀል አለ!››






ታጥረው በተቀመጡ የሼክ አል አሙዲ ኩባንያዎች ይዞታዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ



የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በአንቀጽ 25 ስል የእኩልነት መብት  እንደሚከተለው ይላል፤

ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘር፣በብሔር፣ ብሔረሰብ፣በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡
ህገ መንግስታችን እንዲህ ቢልም በተግባር የምናየው ግን በግልባጩ ነው፡፡ እነዚህ በሽህ አሊ አል አሙዲን  ስም የተመዘገቡት ቦታዎች ታጥረው ከተቀመጡ አስራ አምስት ዓመት አልፏቸዋል፡፡‹‹በኢንቨስትመንት ሕጉ መሠረት ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ግንባታ ይካሄድባቸዋል የሚል ውል ቢኖርምም›› የዚህ ባለሐብት ግን ውሉ ካአስራ አምስት ዓመታት በኋላም ከአንድ ወር በፊት ‹‹ማስተንቀቂያ ሊሰጥ ነው››የሚል ዜና በሪፖርተር ተዘግቦ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹ምርመራ ሊካሄድ ነው›› እየተባለ ነው፡፡ የምን ምርመራ ነው? ህግ የተላለፈ ውል የለ ቅድመ ሁኔታ ፈርሶ መሬቱ ወደ ሚመለከተው አካል መመለስ ሲገባው መለማመጡ ምን አመጣው? ትክክለኛው መልስ ትላልቅ ባለሃብቶች የትላልቅ ዱላ ባለ ቤት ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡በሃገራችን ሰብአዊ መብት የሚከበረው በህግ ሳይሆን በጉልበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ጉልበት ያለው የፈለገው ዓይነት ወንጀል ቢፈፅምም በጉልበቱ ይከበራል፡፡ጉልበት የሌለው ግን ወንጀል ፈፅሞ ይቅርና ንፁህ እያለም ቁም ስቅሉን እያየ ነው፡፡

‹‹በአገር አቀፍ ደረጃ የሼክ አል አሙዲ ኩባንያዎች የያዟቸው በርካታ ይዞታዎች በተገባው ውል መሠረት ግንባታ እየተካሄደባቸው ባለመሆኑ፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ተነስተዋል፡፡››ቆይ ህዝብ ፈርቶ ዝም ቢልስ ንሮ መንግስ ስራውን አይሰራም ድንዴ?ዜጎች ግብር የሚከፍሉት እኮ ገንዘብ ስለበዛባቸው አይደልም፡፡ ህግ እንዲ ከበርላቸው ነው፡፡
‹‹ሁኔታው ያሳሰበው ኢሕአዴግና ኢሕአዴግ የሚመራው መንግሥት ለባለሀብቱ የተሰጡት ቦታዎች እስካሁን ለምን ግንባታዎች እንዳልተካሄደባቸው ምክንያቱን ለማወቅና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምርመራ ጀምሯል፡፡›› ምንም ዓይነት ምርመራ አያስፈልገውም! ባለሐብቱ ግዴታቸውን አልተወጡም፤ ስለዚህ እንደማንኛውም ዜጋ(ሕጋዊ ዜግነታቸው ሳዑዲ ዓረብያ ቢሆንም) እርምጃ ሊወሰድባቸው የገባል፡፡መሬቱ ወደሚመለከተው አካል መመለስ አለበት፡፡


ካልሆነ ግን ይህ መንግስት በራሱ ፍላጎት የውርዴት ካባ እየለበሰ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
አለበት፡፡ህግ ይከበር!መንግስት እኩልነታችን በወረቀት ብቻ ሳይሆን በተግባር ልያሳየን ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment