የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመጠቃለያ(ፋይናል) ፈተና እየተፈተኑ ይገኛሉ፡፡አብዛኞቹ ተማሪዎች
ከፍተኛ የራስ መተማመን አላቸው፤ እነዲሁም በጣም ጎበዞች ናቸው፡፡ የጉረኛ አስተማሪዎች ፈተና ያለምንም ችግር መድፈን ይችላሉ፡፡
በተቃራኒውም ልክ እንደ ልፍስፍሶቹ አስተማሪዎች ልፍስፍስ ተማሪዎችም ነፍ ናቸው፡፡እናም በዚህ ሳምንት የኩረጃ ጥበባቸውን የሚያስመስክሩበት ይሆናል፡፡ መንግስት ኮርጆ ፖሊሲ ያወጣል፣አስተማሪ
ኮርጆ ይፈትናል ኩረጃም ያስተምራል(ለይስሙላ ብቻ የየራሳችሁ ስሩ በሎ ይፎክራል… ፈተናው እስኪያልቅ!)፣ አርቲስቶች ይኮራረጃሉ፣ደራስያን
ይኮራረጃሉ፣ ነጋዴዎች በፎርጅድ እቃ ‹‹በአቋራጭ ለመበልፀግ›› ይሯሯጣሉ፡፡ የኩረጃው ትውልድ የኩረጃ ሃገር ለመመስረት እየተብከነከነ
ነው …‹‹ ጅግራ እንደመሪው››፡፡
ሃገራችን ኢትዮጵያ የብዙ አስደናቂ ቅርሶች ባለቤት የመሆኗን ጉዳይ ዓለም የመሰከረው እወነታ ነው፡፡
የተወሰኑትን እንኳ እንጥቀስ ከተባለ የአክሱም ሐወልቶች፣ላሊበላን ጨምሮ በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ውቅር አብያተ ክርሰትያናት፣ባህላዊ
አልባሳትና አሰራራቸው፣ባህላዊ የቤትና የእርሻ መሳርያዎች፣ባህላዊ የሙዚቃ መሰራያዎች፣ የተለያዩ ዓይነት አትክልቶች፣ፍራፍሬዎች፣ጥራጥሬዎች
ወዘተ እያለን መዘርዘር እንችላለን፡፡እንደ ነዚህ ዓይነት ቅርሶች ቁሳዊ ተብለው እንደሚጠሩ የነገረን የአንደኛ ደረጃ የታሪክ መመርያ
መፅሐፍ ነው፡፡መንፈሳዊ ተብለው የሚጠሩ ቅርሶችም አሉን፡፡ለምሳሌም የራሳችን የዜማ ዓይነቶች፣ ቋንቋ፣ፊደላት፣ቁጥሮች፣ስነ ቃላት፣በዓላት፣የጊዜ
መቁጠርያ፣ባህላዊ ስርዓቶች(የጋዳ ስርዓት፣የሃገር ሽማግሌዎች፣ ዕድር፣ዕቁብ)ወዘተ መጥቅሰ እንችላለን፡፡ እንዚህ ቁሳዊና መንፈሳዊ
ቅርሶች ከብዙ ዓመታት በፊት የተገኙ የአባቶቻችን እፁብ ድንቅ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው፡፡ሲወርድ ሲዋረድም እኛ ጋር ደርሷል፡፡
ወላጆቻችን ምንም ዓይነት ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ጥንት ዘመን ይህን የሚያህሉ የፈጠራ ውጤቶች ተመራመረው
ማግኘት ችሏል፡፡ንገር ገን በቂ ናቸው ለማለት አይቻልም፡፡በአሁኑ ጊዜ ዓለም በየቀኑ በአዳዲሰ ግኝቶች እየተጥለቀለቀች ትገኛለች፡፡ይቅርና
ይህቺ የምንኖርባት ዓለም/ፕላኔት ያደጉ ሃገሮች ብዙ ገንዘብና ዕውቀት በመመደብ ሌሎች ፕላኔቶችን በማሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡ለምን ቢባል?
ሁሌም የተሻለ ነገር ማግኘት እንደሚቻል ስለሚያምኑ ነው፡፡ምነጊዜም ቢሆን የበልጥ ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል አሰራር አለ፤ ‹‹እልፍ
ሲሉ እልፍ ይገኛል›› እንደሚባለው ማለት ነው፡፡እናም ዓለም በእውቀትና
በቴክኖሎጂ እንደሮኬት እየተመነጠቀች ትገኛለች፡፡ዓለም ሰው መተካት የሚችሉ ሮበቶችና የሰው አካልን መገጠጣጠምና መፍታት የሚችሉ
የሕክምና ውጤትችን ለማግኘት እየተፍጨረጨረች ትገኛለች… የሰው ልጅን ፈትተው የሚገጣጥሙ እጅግ ዘመናዊ ጋራጆች፡፡ አዎ ሌላው ዓለም
ድህነት ይቅርና ሞት ጭምርም ለማሸነፍ ሌት ተቀን እየተጣደፈ ነው፡፡
በኛ ሃገርስ? በኛ ሃገርማ ‹‹ተከድኖ ይብስል›› ነው ነገሩ፡፡ ቀንና ሌሊ እየቃዠን ነው የምናሳልፈው…
የትም የማያደርስ የቁም ቅዠት፡፡ በኛ ሃገር አዲስ ነገር መፍጠር ቀርቶ አስመስሎ(ኮርጆ) መስራተም አልተቻለም፡፡አብዛኛው ጊዜያችን
በከንቱ እያባከንን ያለን ይመስለኛል፡፡ትልቁ ሃብታችን ጊዜ ቢሆንም ፋይዳ በሌለው ነገር ላይ እያባከነው ነው፡፡ተመራመረን አዲስ
ውጤት መግኘት ይቅርና በሌሎች ልፋት የተገኘውንም በአግባቡ ለመጠቀም ደንታ የለንም፡፡ለመንደርደራያ ያሕል የህን
ካለኩኝ ዘንዳ ወደ ዋናው መንሻ ሐሳቤ ልግባ፡፡
ባአሁኑ ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግማሽ ዓመቱን የመጠቃለያ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ፈተና
በደረሰ ቁጥር ሌሎች ተደራራቢ ፈተናዎች ይከተላሉ፡፡ተማሪዎች ከመጠን በላይ ይጨነቃሉ… በተለይ ጀማሪ(ፈረሽ)ተማሪዎች፡፡ፈተና ስያሜውና
አፈፃፀሙ ከሚገባው በላይ ያከበዱት ይመስለኛል፡፡በስያሜው ላይ የእንግሊዘኛው ‹‹exam/test›› ቀጥተኛ ትርጉሙ ከአማርኛው ወይም
ከትግርኛው ‹‹ፈተና›› ጋር የሚራራቅ ትርጉም በጣም ይራራቃል፡፡ለምሳሌ
“Exam means: A set of questions or exercises evaluating
skill or knowledge and test means 1. A trial of something to see if or how it
works or 2.Any standardized procedure for measuring sensitivity,
memory, intelligence, aptitude or personality etc.”
በሁለቱም ተምሳሳይ ቃላት (exam/test) ያሉ ጠቋሚ ወይም አስረጂ
ትርጓሜዎች ብንወስድ(evaluating/
measuring) ሲሆኑ ትርጉማቸውም መመዘን እና መለካት የሚል ይሆናል፡፡በእንግሊዘኛው ትርጉም መሰረት ተመሪ
ምን ያህል እንደወቀና እንደተረዳ የመዘናል ወይም ይለካል… በተማረው መሰረት፡፡ ‹‹ፈተና››ግን ተማሪ ለማሸበር የሚደረግ ይመስላል…
‹‹ወደ ፈተና አታግባኝ›› በፆሎት ላይ?በዛ ላይ ደግሞ አብዛኞቹ አስተማሪዎች ተማሪን ለመጣል ከባድ በሚባሉ ጥያቄዎችን
ያቶክራሉ፡፡ይህን ያነሳሁት ለምሳሌ ያክል ለመጥቀስ እንጂ የስነ ቋንቋ መሁራን ስራ መሆኑን ስለዘነጋሁት አይደለም፡፡
እንደ ዋናው ችግር ሊነሳ ይሚገባው ነገር ግን የአፈፃፀሙ ጉዳይ ነው፡፡ይህ ችግር የሚመነጨው ከስርዓተ ትምህረቱ አቀራረፅና ወይም አወጣጥና የመማር ማስተማር ሂደቱ ያጠቃልላ፡፡ሲጀምር
የስርዓተ ትምህርቱ ካሪከለም ከሌሎች ሃገሮች የተኮረጀ ነው እንጂ ሃገራዊ መመዘኛ የለውም፡፡
1.
ስርዓተ ትምህረቱ ከሌሎች ሃገሮች የተወሰደ(በጥሬ ቃሉ የተኮረጀ) በመሆኑ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ጭብጡን(ፈሬ ሐሳቡን) በቀላሉ ለመለዋወጥ ሲቸገሩ
ይስተዋላል፡፡ አብዛኞቹ አስተማሪዎች ብቃትና ፍላጎት የጎድልባቸዋል፡፡ እነድም የሚናገሩትና የሚያስተምሩት የትምህረት ዓይነት በደምብ
አያውቁትም አልያም ፍላጎታቸው ከመጠን በላይ የወረደ ነው፡፡ እንዳነዶቹ በሰሚስትር ሁለቴ ወይም ሶስቴ ክፍል ገብተው የባጥ የቆጡን
አውርተው ይወጡና ፈተና ሲደርስ የጥያቄ መዓት ተማሪው ላይ ይጫናሉ… ጎበዝ ለመባል፤ ‹‹የእንትና ፈተና ማንም አይመልሰውም ››ተብሎ
እንዲወራላቸው፡፡ ለሌሎቹ አስተማሪዎች ደግሞ ክፍል ማለት የግል ችግሮቻቸውን የሚዘረዙሩበት መድርክ ነው የሚመስለው… የረሮና የአቤቱታ
መድርክ፡፡የሌሎቹም የሂይወት ታሪካቸውን እንደ ውዳሴ ማርያም የሚደጋግሙበት፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች
የመጠቃለያ ፈተና ሲደርስ የቡድን ስራ ይጭናሉ፤ ለፈተና በድምብ እንዳይዘጋጁ እንቅፋት ለመፍጠር፡፡
2.
በቂ የሪፈረንስ መፃሕፍት ማግኘት አይቻልም፡፡ ቢገኝም አንድም አስተማሪው ወስዶ
ይደብቀዋል አልያም ጊዜ ያለፈበትና ከኛ ሃገር ንባራዊ ሁኔታ ጋር የማይገናኝ ነው፡፡ የኢንተርነት አግልግሎት አሁንም ድረስ ለተመራቂዎች
እንጂ ለሌላው ተማሪ አይታሰብም፡፡
3.
የተማሪዎች ምግብ ቤት ንፅህናና የሚቀርበው ምግብ በዓይነትም
ሆነ በይዘት የወረደ መሆን ተማሪዎች በተለያዩ የጤና ችግሮች እንዲያዙ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡ ተማሪዎች የወጪ መጋራት መፈረማቸው
ግዴታ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ለተማሪዎች ተብሎ የሚመደበው በጀት በጣም ትንሽ ከመሆኑ ባሻገር ያለውም በሙሰኞች ሰሚዘረፍ
የምግቡ ዓይነት፣ ይዘትና ንፅህና በጣም የወረደ ሰለሚሆን ለጤና ጠንቅ ነው፡፡ወጪ ወጥቶ መብላት እንኳን ለተማሪ ለምንግስት ሰራተኛም
እጅግ ፈታኝ መሆኑን ለማንም ግልፅ ይመስለኛል፡፡ይህ ደግሞ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ እንቅፋት ይፈጥርባቸዋል፡፡
እናም በተማሪው ላይ እነዚህና ሌሎች ችግሮች ሲደራረቡበት ተመርቆ ስለመውጣት እንጂ ስለማወቅና አለማወቅ
ደንታ አይነረውም፡፡ ለእውቀት ከመመራመር ይልቅ እንዴት አድርጎ በፈተና ላይ ከሌሎች ኮርጆ የመመረቅያ ነጥብ ማግኘት እንዳለበት
ሲያወጠነጥንና ላይ ታች ሲል ይታያል፡፡ በተላይ አሁን አሁን መኮረጅ ወንጀለኝነቱን ቀርቶ እንደ ጀብድ እየተቆጠረ ነው… መኮረጅ
ብልጥነት ሁኗል፡፡በቃ ዋናው ነገር በፈታኙ ዓይን ላይ አለመግባትና ሳይታዩ መንትፎ ማምለጥ ብቻ፤ ካልሆነም ፈተና የመጣሉ ተብለው
የሚገመቱ ፍሬ ሃሳቦች በጥስጣስ ወረቀቶች(አጤሬራ)፣በመዳፍ ላይ፣ በክንድ ላይ፣ በልብስ ወዘተ ፅፎ መግባት ከዛም መገልበጥ፡፡አኮራረጁን
ለማይችሉት ግን ውርዴትን ማከናነቡ መች ይቀራል፡፡አንዳንድ ተማሪዎች ተሳስተው የሌላ ሰው ስምና የመታወቅያ ጭምርም የኮርጃሉ ይባላል…
አጥፍቶ መጥፋት ይሉሃል እነዲህ ነው፡፡
ይህ የኩረጃ ወንጀል ግን ለሃገራችን የማሕበራዊና ኢኮነሚያዊ እድገት እጅግ ፈታኝ መሆኑን እያየነው
ነው፡፡ መንግስት ከሌሎች ሃገሮች ፖሊሲዎችና ሰትራተጂዎችን እየተንደፋደፈ የኮርጃል(በነሱ አባባል ‹‹ቃል በቃል›› ይወስዳል)የወረቀት
ማድመቅያ ሁኖ ይቀራል፡፡ ካዛም በተደጋጋሚ‹‹የአፈፃፀም ችግር እንጂ ፖሊሲው እንከን አይወጣለትም›› ይባላል፡፡ እንዴ ሊሆን
ይችላል?
ይህ
ነገር ሊከሰት የሚችለው በሁለት ነገሮች ብቻ ነው፡፡ ወይ ፖሊሲው ትክክል አይደለም ወይም ደግሞ ፖሊሲ አስፈፃሚዎቹ በደንብ አልገባቸውም፡፡መፍተሔው
ታድያ አንዳቸውን መቀየር ነው… ፖሊሲ አስፈፃሚው ወይም ፖሊሲው፡፡ካልሆነ ግን አሁን እደሚታየው ሃገር በኩረጃ ስትተዳደር ትኖራለች፡፡ኩረጃ
ፀረ ልማት፣ፀረ እድገት ነው በማንኛውም መስክ፡፡
በሙዚቃ ስለጎንደር አንዴ ከተዘፈነ ሌሎችም እየተከተሉ ጎንደርን መከራዋን ያበሏታል፡፡ድሬ ከተባለም
ዘፈኑ ሁሉ ድሬ ድሬ ድሬ ይሆናል… የገደል ማሚቶ!
አንዱ የመፅሐፍ ተርጓሚ የስለፍልስፍና
መፅሐፍ ተርጉሞ ካሳተመ ሌሎችም በተደጋጋሚ እየተረጎሙ ማሳተም ይጀምራሉ… በየመፃሕፍት መደብሮች ሌላ መፅሐፍ አይገኝም፡፡ዴርቶጋዳ
ከተፃፈ አፍሮጋዳ ይከተላል፡፡አንዱ ማሕሙድ ጋር ጠብቂኝ ካለ ሌላውም ቦታ ቀይሮ ቦሌ ፒኮክ ጋር ካልጠበክኝ ብሎ የሙጢኝ ሲል ይስተዋላል…
ልጠብቅሽ ቢል ምን ይጎድልበታል?አንዱ ለስደት ከተሰለፈ ሌለውም ይከተለዋል፡፡አንዱ ሐሺሽ ቤት ከከፈተ ሌላውም እንዲሁ
ተሸቀዳደሞ ብዙ ሐሺሽ ቤቶችን ይከፍታል፡፡ሰልፍ ይኮረጃል(የዳቦ፣የታክሲ፣የባስ ወዘተ)፣ የጎዳና ላይ ነውጥ ይኮረጃል፣ ሽብርተኝነትና
የፀረ አሸባሪ ሕግ ይኮረጃል… ምን የማይ ኮረጅ ነገር አለ? የኩረጃ ሃገር!
እናም የሃገር መሪዎች መኮረጃቸውን በአደበባይ ካመኑ፣አስተማሪዎች ከሌሎች አስተማሪዎች ኮርጀው ፈተና
ከፈተኑ፣የዘፋኞች ብቃት እንደ ገደል ማሚቶ ማስተጋባት ከሆነ፣ የመፅሐፍ ደራሲዎች ስም ቀይሮ ማሳተም ከሆነ ስራቸው፣ ተማሪዎች ከማን
ተምረው የራሳቸው ይስሩ?እየኮረጁ አትኮረጅ ማለት እየገደሉ አትግል ብሎ የመስበክ ያህል ይቆጠራል፡፡ከተቻለ ኢትዮጵያዊ መቦቀል
ያለው አሰራርና ፍለስፍና እናራምድ መኮረጅ የግድ ከሆነብን ግን ካስተሳሰባችንና ንቃተህሊናችን ጋር የሚስማማ ይሁን፡፡
አካሄዳችን አያምርም፡፡‹‹አየነ ስወር አይነ ስውርን ቢከተል ተያይዞ…(እኔ ያስፈራኛል! ከፈለጋችሁ
እናንተ ጨርሱት)››እንዳንሆን ራሳችን እንሁን፣ የራሳችን እንስራ፡፡
I really want to admire your view, i can say 'KUREJA' is killing us, i remember what happened two/three years ago, back then i was giving a training in one of the regional states of Ethiopia, Gambella, and i became very close to one of the trainees,he is a teacher in a TVET college, we used to talk on so many issues about our country and life in general. And one day i asked him if there is one thing he can do for his region, Gambella, amazingly i was shocked by his answer. He said he was having a visit in Mekelle and he was so impressed by what he saw there in Mekelle. He told me that there is a high school called "KELAMINO" where only outstanding students join and attend a class, and he also visited an institute called MIT (Mekelle Institute of Technology, and he wanted to copy what he saw there in Mekelle, just because was having a chance to join Gambella education bureau and would be appointed as a deputy of the bureau. I know you might wonder what was the shocking point. In Gambella the problem back then was, most parents are not willing to send their children to school, and there is only one/two , if i am not mistaken, high school/s, and there is only one TVET college, so the solution for this problem was to create awareness about education and to facilitate ways to build as many high schools/colleges as possible but rather he wanted to copy what he saw in Mekelle, this is what we inherited from the government. Every system or policy is either China's or from some other country's experience, we should have a system or policy which best suits our own environment, unless and otherwise we can not progress like the way we need. And i want to thank you again for raising a good point, Keep up the good work my friend
ReplyDelete