Sunday, January 6, 2013

የኢትዮጵያ የገና በዓል አከባበር




የክርስትያን እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያውያን(በተለይም ኦርቶዶክሳውያን) የገና በዓልን እጅግ በጣም በደመቀና ባሸበረቀ ነው የሚያከብሩት፡፡ልክ እንደ ትንሳኤ በዓል በልደት በዓል ዋዜማም ነጭ በነጭ ለብሰው በየአብያተ ክርስትያኑ የጌታችንና መድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያወድሱና ሲቀድሱ ያድራሉ፡፡ አሁን የህን ፅሑፍ በምፅፍበት ሰዓትም በየአብያተ ክነርስትናቱ በማይክራፎን የሚደረግ የቀዳሴ ስነ ስርዓት ከአድማስ አድማስ እያስተጋበ ይገኛል፡፡ ይህ ስነ ስርዓት እስከ የለሊቱ ዘጠኝና አስር ሰዓት ድረስ ይቀጥላል፡፡ከዛም የቀዳሴው ስነ ስርዓት ይጠናቀቅና ምእመናን ወደየቤታቸው በማምራት የ44 የፆም ቀናት ቤት በፈራው ይፈታል፡፡ በነጋታውም ከምሳ ሰዓት በኋላ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የገና ጨዋታ ይካሄዳል፤ በተለይም በገጠር አከባቢዎች የሩርና የፈረስ ግልብያ በድምቀት ይከናወናል፡፡

የህ በዓል በአገራችን በድምቀት ከሚከበሩ ብሔራዊና ሃይማኖታዊ በዓላተ አንዱ ቢሆንም አሁን አሁን ግን በመጤ ባህሎች እየተበረዘ ይገኛል፡፡በተለይ በከተሞች ወርየው ሁሉ ስለ የገና ዛፍ ማማርና አለማማር እንዲሁም ስለ የበሕር ማዶው የገና አባት ተረት ተረት ነው፡፡ይህ ነገር በኤፍኤም ራድዮዎችም ሳይቀር ሙሉ ሽፋን ተሰጥቶት እንደ ‹‹አቡነ ዘበሰማያት›› ሲደጋገም የሰማል፡፡ከአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦች ቀጥሎ እንደ ትልቅ የመነጋገርያ አጀንዳ ይቆጠራል፡፡ ግን ስለ የገና ዘፍና የገና አባት ጉንጭ አልፋ ዲስኩር ምንፋቱ ለሃገራችን ምን ይፈይዳል?
ለማንኛውም መልካም የገና በዓል የሁንላችሁ!



No comments:

Post a Comment