Monday, January 21, 2013

ትኩስ ወሬ ስለ ካውያ፤ ‹‹ካውያ ባለሃብት እያደረገ ነው››




አንዳንድ ሰዎች ተንግሮት የማይሰማ፣ እየሰማም ቢሆ ሆን ብሎ ሰዎችን ለማናደድ እዳንልሰማ በማስመሰል ‹‹ምን አልከኝ/ሺኝ? እ፣ እ… እ…እ›› እያለ የሚያታክት ሰውን ‹‹ካውያ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ እንደ ካውያ ቀስ እያለ ልብን የሚያቃጥል፣ አንጀት እርር ድብን የሚያደርግ ዓይነት ሰው ማለት ነው፡፡

አሁን ግን ወሬው የተቀየረ ይመስላል፡፡ በአዲስ አበባ የሚናፈስው ወሬ ወሬውን የሰማ ሰው ሁሉ ፀጉሩና ልቡ እንዲቆም የሚያደርግ ሁኗል፡፡ ሰው ሁሉ ግራና ቀኝ እየተሯሯጠ፣ ልቡ በድካም ቀጥ እስክትል ድረስ በሐሳብም ሆነ በእውን እየከነፈ ይገኛል፡፡በቃ ምን ልበላችሁ? ክንፍ አውጥቶ መብረር ያሰኟል፡፡ አንድ ካውያ እስከ ስድስት ሚሊዮን ብር ድረስ እየተቸበቸበ እንደ ሆነ እየተነገረ ነው፡፡እስኪ አስቡት፤ በአንድ ካውያ ባንዴ ሚሊየነር መሆን፣ ከዛም ‹‹ድህነት ደና ሁኚ›› እያሉ መዝፈን… እንኳን በእውን ሽሮ እየበሉ እንዲህ ዓይነት ህልም ማለም ራሱ መታደል ነው፡፡ስለሆነም ይህ አለቧልታ (እስካሁን ድረስ አላመንኩም)እውነት ከሆነ ‹‹ካውያ›› ስድብ መሆኑን ቀርቶ የሙገሳና የመቆለማመጫ ቃል ሊሆን ነው፡፡ከባሕር እንቅና ከዲያሜንድ የከበረ በአቋራጭ የማብልፀግያ መንግድ ሊሆነ ነው፡፡

ካውያ ካላችሁና የሚከተሉትን መስፈርቶ የሚያሟላ ከሆነ ያካውያ ልብስ መተኮሻ ብቻ ሳይሆን ዲያሜንደም ጭምር ነው… ሚልየኖችን የሚያስታቅፍ፡፡
1.ወደ ካውያው እስክርቢቶ ስታስጠጉለት ካገነፈለው ወይም ቀለሙን ከቀየረው
2. ሞባይል ስታስጠጉለት ኔትወርኩን ካጠፋውና
3.ፎቶ ልታነሱት ስተሞክሩ የማይነሳ ከሆነ(ጥቁር ብቻ ከሆነ)
እጅግ የተከበሩ ባላሃብት መሆነዎን ያረጋግጡ፤ እናም እንኳን ደስያሎት እላለሁ፡፡ እንድ ነግር ግን እስካሁን ድረስ ግልፅ አይደለም፤ ለምን ጥቅም እንደሚውል፡፡

አንድ ወሬ ልመርቅሎት(ምናልባት እስካሁን ካልደረሱበት)፡፡ የድሮው ትልቁ ፋኖስም ከካውያ በበለጠ የናጠጠ ትጃር ያደርጋል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው፡፡እናም ከአያቶችዎ የወረሱት የጠቀረሸ ፋኖስ ካልዎትም አሁንኑ ያፈላልጉት፡፡

እናንተስ ምን ትላለችሁ?በናንተ አከባቢ ምን ይወራል? መቸስ ‹‹ ውሸት፣ አልቧልታና ሐሜት ከእውነት በበለጠ በፍጥነት ቀየውን ሁል ያካልላሉ›› ይባላል፡፡
መልካም ዕድል(እውነት ከሆነ ማለት ነው)፡፡

No comments:

Post a Comment