Sunday, August 11, 2013

ጥሩነሽ




‹‹ስም ይመርሆ ለምግባር›› ነው የሚባለው? ቀለል አድርገው ‹‹ጥሩነሽ›› ሲሉ ሰየሟት አይደል? በጣም የሚገርም ስያሜ ነው፡፡ለጥሩነሽ ግን ‹‹ጥሩነሽ›› ብቻ በቂ ነው ትላላችሁ? እጅግ!…እጅግ!…እጅግ!…በጣም!…በጣም!…በጣም!…ጥሩነሽ!
እንደውም ይህም ሲያንስባት ነው! እውነቴን ነው፤ በጣም ሲበዛ ያንሳታል! ነገር ግን የጥሩነሽ ዲባባ ቤተሰቦች ኩሩ ኢትዮጵያውያን ስለሆኑ ነው መሰለኝ ምንም ሳያካብዱ፣ቀልል አድርገው፤ ‹‹ጥሩነሽ›› የሚል ስያሜ ሰጧት፡፡የሚገርም ስም! የምትገርም ልጅ፡፡በነገራችን ላይ የወርቅ አባዜ ስለተጠናወተብኝ ነው እንጂ የበላይነሽ ኦልጂራ መዳብም ቢሆን ትንሽ የተቀደሱ ሃገራች ብቻ ናቸው የሚታደሉት፡፡ብርቅየዋ አትሌታችን በላይነሽም ልክ እንደ ስሟ የበላይነቷን አረጋግጣለች፡፡እውነትም በላይነሽ!!!

በሁለቱም ፆታዎች፣በጀግኖቹና በብርቅዬቹ አትሌቶቻችን አማካኝነት ወርቅ!... ወርቆች!... እንደልብ ማፈስ የለመደች ሃገራችን በዓለም በመሰሪነታቸው ለሚታወቁት እንግሊዛውያን በሚሮጠው ሞ ፋራሕ የወንዶቹ የአስር ሽህ ሜትር ወርቋን ለትንሽ ተነጠቀች፡፡ብርቅየው አትሌታችን ኢብራሂም ጄይላን የብር ሜዳልያው ቢያሸንፍልንም ወርቅ የለመደው ቆሌያችን ግን ሊረካልን አልቻለም፡፡ደስታችንም ሙሉ አልሆነልንም ነበር፡፡

ዛሬ ማታ ግን ጥሩዬ ካሰችን፡፡አዬ ጥሩነሽ! ጥሩውን ሁሉ ጨምሮ ጨማምሮ ላንችው ይስጥሽ! ግን ደግሞ ዛሬም የኢንግሊዞች መሰሪነት የሆድ ቁርጠቱ፣ራስ ምታቱ፣ፍልጠቱ… ኸረ ምኑ ቅጡ! ሊተወኝ አልቻለም፡፡ለምን መሰላችሁ? ትናንት ሞ ፋራሕ እንዳሸነፍ ነበር ቢቢሲ በድረ ገፁ ወድያው ‹‹Breaking news›› ብሎ በቀይ ቀለም የለጠፈው(ፖስት ያደረገው)፡፡አምስት ደቂቃ አልቆየም፡፡ዛሬ ግን እችን ፅሑፍ ፅፌ እስክጨርስ ድረስ ቢቢሲ ሰለ ጥሩነሽ ወይ ትንፍሽ አላለም፡፡አይገርምም? አያናድድም? ወይ ፍንክች! ዘም! ጭጭ!... 

በቀጣዩ ሳምንት፣ ኢብራሂም ጄይላንና ሞ ፋራሕ በአምስት ሽህ ሜትር ሩጫው ይገናኛሉ፡፡ ያኔ ኢብራሂም ልክ እንደ ዴጉን ሞ ፋራሕን ሲያሸንፍ እንግሊዞች ምን አባታቸው ይዘግቡ ይሆን? ብቻ ታላቁ ፈጣሪ የእንግሊዞች ሽንፈት እንዲያሳኝ ነው የምፀልየው፡፡ሞ ፋራሕ ብቃቱን አደንቅለታለሁ፤ ግን አለ አይደል? የሆነ ለጌቶቹ የሚሮጥ ባርያ መስሎ ነው የሚታየኝ፤ኤድያ! ክብረ ነክ ነገር፡፡

በጥሩነሽ ማሸነፍ በጣም ደስብሎኛል! በዚህ አጋጣሚ እናንተንም እንኳን ደስ አላችሁ ስል ‹‹ጥሩ ነሽ… ጥሩ ነሽ…ጥሩ ነሽ›› የሚለው ዘፈን በመጋበዝ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment