ከፕያሳ ወደ ጳውሎስ፣መድሃኒአለም በሚወስደው መንገድ፣ ራስደስታ ሆስፒታል አጠገብ ዮሃንስ ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት
አንድ አዲስ የተገነባ ሕንፃ አለ፡፡የሕንፃው ስም ‹‹ፍቃዱ ዘለቀ ሕንፃ›› ይባላል፡፡ነገር ግን ማታ ማታ የሚያበራው የኤሌትሪክ
ፅሑፍ ግን ‹‹ሕ›› ስለጠፋች ‹‹ፍቃዱ ዘለቀ ንፃ›› ብቻ ሆኖ ነው የሚነበበው፡፡ይህ የፊደል ግድፈት ያለበት ስም ሳነብ ትዝ ያለኝ
‹‹ከእያንዳንዱ ትልቅ ሃብት በስተጀርባ አንድ ትልቅ ወንጀል አለ›› የሚለው የፈረንሳዊው ደራሲ ኦነሪ ባዛልክ ጥቅስ ነው፡፡የሕንፃው
ባለቤት ‹‹ፍቃዱ ዘለቀ ንፃ›› የሚል ፅሑፍ ሲያነብ ምን ይሰማው ይሆን? የስኬታማነት ስሜት ወይስ የመሸማቅቅ?
No comments:
Post a Comment