Thursday, August 1, 2013

የኩዌቷ ፖለቲከኛ በጦርነት የተማረኩ ሞስሊም ያልሆኑ ሴቶች ለወሲብ ባርነት እንዲሸጡ መፈቀድ አለበት አለቸ



የዓመቱ አስቅኝና አስደናቂ ሴት!!! "ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም" ይላል ያገሬ ሰው
ሳልዋ አል ሙቴሪ ትባላልች።ለፓርላማ አባልነት ተወዳድራ ነበር፤ አልተሳካላትም እንጅ።በአሁኑ ጊዜ በኩዌት የፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ(political activist)ና የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢዋ ሳልዋ አል ሙቴሪ ከቤት ሰራተኞችና ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ለሚማግጡ የኩዌት ባለትዳሮች መፍትሔ የሆናል ብላ ያመነችውን ሓሳብ ይዛ ብቅ ብላልች።በወሲብ ስሜት የሚንቀለቀሉና ሞስሊም ሴቶችን ባሃብትና ስልጣናቸውን በመመካት እንደ ባርያ የሚቆጥሩ ወንዶች በጦርነት ከሚታመሱ ሃግሮች የወሲብ ባሮች እንዲገዙ ይፈቀድላቸው የሚል።


ምክንያትዋ ድግሞ በእስልምና እምነት አስምሮ መሰረት ሞስሊም ወንዶች በጦርንት ከማረኩዋቸው የወሲብ ባሮች ጋር ወሲብ ቢፈፅሙ እንደ ሃራም ሰለማይቆጠር ነው።የሳውዲ የሃይማኖት አባቶችን አማክሬ ችግር የለውም ብሎውኛልም ስትል ተናግራለች ሙቴሪ፤ በዩቲብ በለቀቀችው ቪድዮ


“የሚያሳፍር ነገር የለውም፤በሸሪዓ ሕግም ሃራም አይደለም” ስትል ትሞግታለች፤ሙቴሪ። ”ለሴቶቹም ይጠቅማቸዋል፤ እስር ቤት ውስጥ በርሃብ ማቅቀው ከሚሞቱ ይታደጋቸዋልና” በማለትም ትክራክራለች።  


ሙቴሪ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ኢራቅ፣ኢራንና ሶርያ ጠቅልሎ ያስተዳድር የነበረው ሃሩን አል ረሺድ የተባለ ሞስሊም መሪን እንደ ምሳሌ አቅርባለች።ሃሩን አል ረሺድ 2,000 እቁባቶች ነበሩት የሚባል አልቧልታ አለ ያባላል።


“የኩዌት ወንዶች በወሲብ ፍላጎት ተገፋፍተው የወሲብ ቅሌት በመፈፀም የሸሪዓ ሕግ ከሚተላለፉ የወሲብ ባሮች ይግዙ” ፤ ትላልች ሙቴሪ።ሙቴሪ  በዚህ አላበቃችም፤ ጦርነት የማያባራባት ችችንያ ለዚህኛው ዓይነቱ ንግድ ተመራጭ ንች ነው የምትለው።


በነፃነት የሚኖሩ ሞስሊም ሴቶች በትዳር ውል ነው የሚያገቡዋቸው እቁባቶቹ ግን በገንዘባቸው ይገዙዋቸዋልና እንዳሻቸው ሊያደርጉዋቸው ይችላሉ ነው የምትለው ሙቴሪ።እናም ትላለች ሙቴሪ ጭዋ የኩዌት ሞሲሊም ወንዶች የመርጥዋትን ለመግዛት የሚያስችላቸውን ገንዘብ ካላቸውና ሊቆጣጠሩት በማይችሉት የወሲብ ፍላጎት

 የሚፈተኑ ከሆነ ወጤታማው መፍትሔ የኸው ብቻ ነው ስትል ደምድማልች።

ሙቴሪ የኩዌት ሴቶች ጨምሮ ዓረቦችና ምዕራባውያን ቢኮንኑዋትም አወዛጋቢው አስተያየትዋን ግን አልገታችም።አሁን ደሞ ለኩዌት ሞስሊም ሴቶች ሌላ መፍትሔ አለኝ ብላለች። እሱም የወሊድ መጠን ለመጨመር እንዲቻል የኩዌት ሴቶች እንዳዘዙት የሚሆንላችው "መልከ ቀና" ንጭ ወንዶች መግዛት ይችላሉ ስትል መክራለች።


ዋቢ ድረ ገፆች

 


  1. Kuwait Concubines: What Century Are We in Again? DAVID ROBERTS: 'Concubines' are the solution to protecting Kuwaiti men from "..adultery and corruption," according to a female Kuwaiti political activist. Great idea, eh?...
  2. Goal to Improve Offspring Through "White-Skinned Husbands" 

    3.  2011′s Amazing Women of the Year SHELINA ZAHRA JANMOHAMMED: How could I possibly include all the women who filled our headlines over the past 12 months, for bravery and impact?.

 



No comments:

Post a Comment