Saturday, August 31, 2013

‹‹ለምን ተለያየን? ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ተከተልን›› አብርሃ ደስታ



እወይ ፖለቲከኛ !!! እወይ ክህደታችሁ!!! እወይ አሌነታችሁ!!! ‹‹ኢትዮጵያ ወይም ሞት!››፣‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም››፣ ‹‹ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም›› ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ግን እንድንስማማ አስችለውናል፤ አይደል?‹‹የግል መብት እንጂ የብዱን መብት አያስፈልግም›› እያልከን ነው ወንድማችን? እሺ በናንተ(ኢትዮጵያ ግለሰቦች በውድም በግድም የሚታጨቁባት ትልቅ ጎተራ ነች ለምትሉ) አስተሳሰብ (አክራሪ አመለካከት) ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊትና ‹‹ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ›› ከማቋቋሙ በፊት በኢትዮጵያ አለመግባባ ተፈጥሮም ተሰምቶም አያውቅም አይደል? ‹‹ነጭ ሽብር››ና ‹‹ቀይ ሽብር›› ኢትዮጵያችን የምሁራንና የወጣቶች ደሃ ያደረግዋት መቸ ነበር ወዳጄ?
ኢትዮጵያችን የጠርነት አውድማ፣ የደም ጅረት፣ የእርሰበርስ መጠላለፍና መጠፋፋት የነበረችው በኢህአዴግ ጊዜ ነው ያለህ ማን ነው?መስፍን ነጋሽ?ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም?ፕሮፌስር አል ማርያም?ዶክተር መራራ ጉዲና?እነዚህ ሰዎች መኢሶንና ኢህአፓ በሚገዳደሉበት ጊዜ፣ መኢሶኖች የደርግ ሰላዮች ሆነው ኢህአፓዎችን ሲያስጨፈጭፉ ምን ይሰሩ ነበር? ስለሰላም፣ስለአንድነት፣ ስለ  የአስተሳሰብ ብዙኋነት ይሰብኩ ነበር እንዳትለኝ፡፡ወንድም አብርሃ ስላሞካሹህና የፃፍከውን ሁሉ ስላስተጋቡልህ(share ስላደረጉልህ) ብቻ እውነትን አትስቀላት፡፡እነዚህ ሰዎች እነሱን ደግፈህ ሌሎችን በጭፍን ነቅፈህ ስትፅፍ ብቻ እንጂ ህሊናህን ያዘዘህ ስታደርግ ፊታቸው እንደሚያዞሩብህ የኢቲቪ ዜና አንባቢው ተመስገን ዘገየ መደብደቡ ትክክል አለመሆኑን ስትፅፍ ምን አሉህ? ስንቶቹ ይህን የግል አስተያየትህ ተቀበሉት፤ ለሌሎች አካፈሉልህ?ለምን?


ለመሆኑ በአፍ መፍቻ ቋንቋህ የማትፅፈው ለምንድንው?‹‹የናት ቋንቋህ ለመሰዳደብ ብቻ የሚጠቅም የወፍ ቋንቋ ነው›› ብለው የሰበኩህን አምነህ ስለተቀበልከው ነው፡፡በነሱ ባህልና ቋንቋ ተፈብርከህ ከላደክ በስተቀር ያንተ ማንነት እንደማይቀበሉት ታውቃለህና የፈለጉትን ለማድረግ ትገደዳለህ፡፡እነሱ እኮ በባህልህና በቋንቋህ እንድትኮራ አይፈልጉም፡፡እንዳውም በእነሱ የአፍ መፍቻ ቋንቋ መናገር ብቻ አይደለም የሚጠበቅብህ፤ ዘዬውና ለዛው ከበላሸኅባቸው መቀለጃና መሳለቂያ አሻንጉሊት እንደሚያደርጉህም በደምብ ታውቃለህ፡፡ያደክበት ማንነት እርግፍ አድርገህ በመተው እነሱን ለመምሰል የምትፍጨረጨረውም ለዛው ነው፡፡እስኪ በአፍ መፍቻ ቋንቋህን ፅፈህ ፌስቡክ ላይ የለጠፍካቸው ፅሑፎች መለስ ብለህ ተመልከታቸው፡፡የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳንተው ካልሆነ በስተቀር ማንም አያይልህም፡፡

‹‹ቋንቋ መግባብያ ነው፤ስለዚህ እኔና እነርሱ በምንግባባበት ቋንቋ ብፅፍ ምን ችግር አለው?››ለትል ትችላለህ፡፡መግባባት ወይም መረዳዳት ሊኖር የሚችለው አንተም እነሱም ለመግባባት ፍቃደኞች ስትሆኑ ብቻ ነው፡፡ይህ የሚሆነው ደግሞ አንተ የነሱ ቋንቋ ማወቅ ስትችል ብቻ ነው፡፡እናም ግዴታው ባንተ ጫንቃ ብቻ እንዲኖር ነው የሚፈለገው፡፡ለምን?በዓል አሸንዳ በድምቀት በመከበሩ ሲያለቃቅሱ የከረሙት ለምን ይመስልሃል?ያንተ ባህል፣ቋንቋና እሴት ቀጣይነት እንዲኖረው ሰለማይፈልጉ ነው፡፡ለዚህም ነው ቋንቋን መሰረት ያደረገ የብዱን መብት እንዲሻር መቃወማቸውን እየገፉበት ያለው፡፡አንተም የነሱ ተቆርቋሪ ሁነህ አረፍከውና ‹‹ለምን ተለያየን?ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ስለተከተልን›› የሚለው ጭሆታቸውን እንደ ገደል ማሚቶ ታስተጋባለህ፡፡

ኢትዮጵያ ያለ ብሄር ብሄረሰቦችዋ ምንድነች?የትኞቹ ብሄሮች ጠፍተው በየትኛው ብሄር መጠራት አለባት ነው ይምትለው አብርሃ ደስታ?የትኞቹ ቋንቋዎች ጠፍተው በየትኛው ቋንቋ እንድንግባባ ነው የምትፈልገው? ተው እንጂ ወንድማችን፤ወዳጅ መስለህ ጠላት አትሁንብን፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ከአስር በላይ መፂሔቶች እየታተሙ ለንባብ ይቀርባሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ አንድ ብቻ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተም ሲሆን ሌሎቹ እንዳለ በአማርኛ ቋንቋ የሚታተሙ ናቸው፡፡ጋዜጦቹም ቢሆን ከእንግሊዘኛና አማርኛ ቋንቋዎች ውጪ እንዳይታተሙ የተከለከለ ይመስላል፡፡በአፋን ኦሮሞ ዜሮ፤በትግርኛ ዜሮ፤በሱማልኛ ዜሮ፤በአፋርኛ ዜሮ… በሌሎቹም ምንም!!!ለምን?‹‹የአንዲት ሃይማኖት፣አንዲት ቋንቋና አንዲት ኢትዮጵያ›› ውጤት ነው፡፡ብሄር ወይም ቋንቋ መሰርት ያደረገ ፖለቲካ እንዳኖር መቃወምህ ታድያ ከላይ የተጠቀሰው ነገር ለማስቀጠል መታገልህ መሆኑን እመን፡፡ደግሞ አታፍርም ‹‹I am not for sale›› ትላለህ፤ ከዚህ በላይ ምን ልትሆን ፈልገህ ነው አብርሽ?ባህልና ቋንቋውን ተገፎ ራቆቱን የቀረ ሰው ማንነት አለኝ ማለት አይችልም፡፡
 
አየህ ወንድም አብረሃ፤ኢህአዴግ ፍፁም ህዝባዊ ስለሆነ ሊነቀፍ አይገባውም እያልኩኝ አይደለም፤ የህዝቡን አደራ የበላ ከሃዲ ነው፡፡ ቃል መግባት እንጂ የተናገረውን ተግባራዊ የሚያደርግ መንግስት አለመሆኑን አውቃለሁ፡፡ እቅዶቹና መርሃ ግብሮቹ ወረቀት ከማድመቅ የዘለሉት ቢኖር ኢምንት ነው፡፡ባጭሩ ኢህአዴግን ከንተ በላይ ልሰድበውና ልቃወመው አልችልም፤አንተም ታውቃለህ፡፡የኢህአዴግ ችግሮች ከማንም በላይ እናንተ ታውቃላችሁ፡፡
ነገር ግን ኢህአዴግ ‹‹የብሄር ብሄረ ሰቦች መብት(እስከ መገንጠል) የከበር›› ማለቱ ነው እርሰበር እንዳንግባባ ያደረገን፤ ተለያይተን እንድናድግ ያስገደደን፤የተለያዩ ቋንቋዎች እንደንናገርና የተለያዩ ግን ተመሳሳይ አስተሳሰቦች እንድናራምድ ምክንያት የሆነን መለትህ አልቀበለውም፡፡‹‹በአንዲት ኢትዮጵያ ከአንድ ሃይማኖትና ከአንድ ቋንቋ በላይ አይፈቀድም›› ማለት እኮ አክራሪነት ነው፡፡ እኔ የምናገረው ቋንቋ ካልተናገርክ፤በኔ አምላክ ካላመንክና የኔ ትእዛዝ ካላከበር በስተቀር ኢትዮጵያዊ አይደለህም ማለት ምን ማለት ነው?
አንተም ‹‹የያ ትውልድ ነውጠኝነት›› ተጋባብህ ልበል? በጎውን ሁሉ አጥቁረህ፤ እውነታውን ሁሉ ሽምጥጥ አድርገህ መካዱን ካስተማሩህ በላይ የተካንክ ትመስላለህ፡፡አካፋን አካፋ ማለቱን ብትደፍር ምን አለበት? ተቃዋሚዎች ገዢ ፓርቲውን ሽምጥጥ አድርጋችሁ ስትክዱትና በጭፍን ስትቃወሙት እናንተን ለማጥፋት ከመትጋት ውጭ ምን ይሰራል ብላችሁ ታስባላችሁ? ‹‹ የሚያድርጉት አያውቁምና ይቅር በላቸው›› ብሎ እንዲፀልይላችሁ ነው ይምትፈልጉት?



3 comments:

  1. perfect reply ! but what i am asking to you is how can we make EPRDF either to respect the peoples right or if needed remove it

    ReplyDelete
  2. you can "make " nothing, just OBEY the rule of the land, and stop pointing fingeres-do your job! you don know what to do?,get out of here, choma ras!

    ReplyDelete
  3. you can "make " nothing, just OBEY the rule of the land, and stop pointing fingeres-do your job! you don know what to do?,get out of here, choma ras!

    ReplyDelete