
አንድ
ዶክተሩ ቀላል ሰው አይደሉም፡፡ሃይለኛ ኢህአፓ ነበሩ ይባላል፤ምናልባትም
የነጭ ሽብሩ ጠንሳሽ፡፡በከተሞች የተሰማሩ ኢህአፓዎች በቀይሽብር ተመትተውና እርሰበርሳቸው ተገዳድለው ድራሻቸው ሲጠፋ የአሲምባዎቹ
ኢህአሠዎች ደግሞ በተዋጉበት ግንባር ሁሉ አሳፋሪ ሽንፈቶች ሲከናነቡ ቆይተው የመጨረሻ ዕጣ ፈንታቸው መበታተን ሆነ፡፡የነደክተር
የስልጣን ጥማት ቅዠት ሁኖ ቀረ፡፡
ሁለት
ብሬ አሜሪካ ሄደው ደክትረው መጡና ከአሲምባ ያባረራቸው ኢህአዴግን በ97ቱ
ሃገራዊ ምርጫ ለማሸነፍ ከቅንጅቶች ጋር ያለ አቻ ጋብቻ ተጋቡ፡፡የ‹‹ወደነበሩበት እንመልሳቸዋለን›› ፉከራ ከሽፎ በክብር ቃልቲ
ወረዱ፡፡ኋላ በይቅርታም ይሁን በማስጠንቀቅያ ከእስርቤት ሲለቀቁ ወደ አሜሪካ አመለጡና ‹‹በተገኘው አጋጣሚና ስልት›› ተጠቅመው
ኢህአዴግን ከስልጣኑ ለማባረር ጉንበት ሰባት የሚባል አክራሪ ቡድን አደራጅተው በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሶስት
አሁን በምስሉ ላይ የሚታዩ ዶክተር ብርሃኑንን በደጋፊና ተቃዋሚ ምልከታ
እንቃኛቸው፡፡
ደጋፊዎቻቸው፤
ዶክተር ብርሃኑ ሊቅ ወይም ‹‹ጂኔስ›› ናቸው፡፡ኢህአዴግን ከበትረ ስልጣን አባርረው የአራት
ኪሎው ቤተ መንግስት ለመቆጣጠር እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳቦችን በመተንተን ላይ ናቸው፡፡በላፕቶፓቸው ላይ አፍጥጠው
በትኩረት እያነበቡና እስክርቢቶና ወረቅ ይዘው ማስታወሻ እየወሰዱ ነው፡፡የጭንቅላተቸው ሐሳቦችን የመተንተን ብቃት ከሮኬት ይፈጥናል፡፡
የማስታወስ ብቃታቸው ከ‹‹ሃረድ ዲስክ›› የሚበልጥ ሲሆን ‹‹በትሪልዬን ቴራ ባይቶች›› የሚለካ ነው፡፡አሁን ታድያ ይህን ሁሉ የመረጃ
ክምር በከፍተኛ የሒሳብ ቀመር(ሃየር ማትማቲክስ) ተጠቅመው በማስላት ላይ ናቸው፡፡የኢሳት ጋዜጠኞች ኢቲቪን በቅርቡ ይቆጣጠራሉ፡፡የፌስቡክ
ግንባር አዋጊዎችና ተዋጊዎች የወደፊትዋ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ይሆናሉ፡፡ያኔ ኢትዮጵያ ግሃንም መሆኗ ታሪክ ሁኖ ወደ ገነትነት
ትቀየራለች፡፡
ተቃዋሚዎቻቸው፤
ዶክተር ብርሃኑ ምን ያህል ቢበላና ቢጠጣ ነው ይህን ያከለው?አሁን እኮ
ለማያውቀው ተመልካች በላፕቶፑ የሚያነብ ይመስለዋል፤ጉረኛ፡፡እውነታው ግን ሌላ ነው፤ ዶክተሩ የወሲብ ፊልም በመመልከት ላይ ናቸው፡፡አራቱ
ብርጭቆዎች ለምን ደረደራቸው?ላሜ ቦራውን አታልሎ በሰበሰበው ዶላር የተለያዩ ዓይነት ውድ መጠጦች እየተጎነጨባቸው ይሆናል፡፡አናናሱ
በጥርሱ ሊቦጫጭቀው ነው እንዴ! ይህ ሰውየ ከመብላትና(ማባላት)
ከመጠጣት(ማስጠጣት)
ውጪ ሌላ አያውቅም ማለት ነው?ሆዳም! ሁለት መነፅሮች ምን ሊፈይዱለት
ሰበሰባቸው?አንዱ ፊልም ሊያይበት፤ሌላኛው ማንነቱን ሊሸፍንበት፡፡መላጣው ያብረቀርቃል፤እንደመስታውት ፊት ያሳያል፡፡መላጣው ሲያልበው
የሚያብስበት ጨርቅ ያኸውና፤ከማሃለኛው ብርጭቆ አጠገብ፡፡
ማስጠጣት
ማባላት
ዶክተር ብርሃኑ ከወሲብ ፊልም ሌላ ምን ሊመለከት ይችላል?የዓረቡ ፀደይ
በኢትዮጵያም ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ ያሰላስላል፡፡ኢትዮጵያውያንም ልክ እንደ ግብፃውያን ጎራ ለይተው ሲጨፋጨፉ የሚያሳይ ፊልም
የመላጣው ‹‹ስክሪን›› ከሳትላይቶች እየተቀበለ ያስተላልፍለታል፡፡ይህ አስደሳች ዜና በኢሳት ሲተላለፍ በቁሙ እየቃዠ ይመለከተዋል፡፡በዶክተሩ
አስተሳሰብ በአሁኑ ጊዜ እርሰ በርሳቸው በመገዳደል ላይ ያሉ ግብፃውያን ሳይሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
‹‹ግብፃውያን የኢትዮጵያውያን
መከፋፈል ተጠቅመው የገንዘብ ፈሰስ በማድረግ የጉንበት ሰባት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን እየለፉ ነው›› ብሎ ይቃዣል፤
ዶክተር ብርሃኑ፡፡
ዶክተሩ ይቀጥላል፤ከራሱ ጋር አታካራ ይገጥማል፡፡‹‹በቃ ኢህአዴግ በህዝባዊ
አመፅ ከስልጣን ተወግዶ ዶክተር ብርሃኑ
የሚኒሊክ ቤተ መንግስት ይቆጣጠር እንጂ የህዳሴው ግድብ ጥንቅር ብሎ ይቀራል፡፡መለስ ያስጀመረው ግድብና የዕድገት ጎዳና ቢቻል ወደኋላ መቀልበስ እንጂ ስንዝር እንኳን ወደፊት
ፈቀቅ ማለት የለበትም፡፡ይህ ከሆነማ የመለስ ስም ለዘልዓለም ሲወሳ ሊኖር ነው፡፡
ስለዚህ የህዳሴ ግድብና የኢትዮጵያ እድገት ግቡን
መምታት የለበትም፤በጭራሽ!›› እያለ በተመስጦ ይብሰለሰላል፡፡እውነታው እሱ በሚያስበው መንገድ እየሄደ አለመሆኑን ሲገነዘብ ፊቱ
የተጠበሰ ስጋ ይመስላል፡፡አንጀቱ እርር ኩምትር ይላል፤ለንዴቱ ማርከሻም ይጠጣል፤እየደጋገመ፡፡
ስለዚህ ጽኁፍ ምን ማለት ይቻላል ? ተራና ደካማ አስተሳሰብ ባለው ሰው የተጻፈ ተራ የመንደር አሉባለታ እንጂ ፐፐፐፐ ባን ቤት አዋርደህ ሞተሃል!
ReplyDelete