“የጋዜጠኛው ማስታወሻ”ን ከተወስኑ ዓመታት በፊት ነበር ያነበብኩት(ምናልባት ከሶስት
ዓመት በፊት ይሆናል)።ያኔ ለምን ዓላማ እንደፃፈው ባይገባኝም የስነ ፅሑፍ ውበቱ ገን በጣም ሳይመስጠኝ አልቀረም፡፡በገፅ 412 ላይ
‹‹ይህን(አማርኛ ማለቱን ነው) ቋንቋ ከኔ በላይ ማን ይራቀቅበታል?›› እንዳለው ለእንደኔ ዓይነቱ ጀማሪ አንባቢ ሳይራቀቅብን አልቀረም::የስነ
ፅሑፍ ችሎታው ለህፃናት የሚሰጥ ከረሜላ ነው፡፡ያ ከረሜላ ግን መርዝ የተቀባ ነውና ቢበላ ይገድላል።በተመስጦ ሳነበው ተመቸኝ፤ከረሜላነቱን ብቻ ስላየሁ፡፡አንብቤ
ስጨርስ ግን ‹‹ተስፋየ ይህን መፅሐፍ ለመፃፍ ምን አነሳሳው?›› ብየ ራሴን አልጠየቅኩም፤ የመርዙን መኖር
አልተገነዘብኩም ነበርና፡፡በድጋሚ ሳነበው ግን የስነ ፅሑፍ ችሎታው ብቻ አንድንቄ ለማለፍ አልቻልኩም፡፡የከረሜላው ሽፋንና መርዝ
መለየት ችያለሁ፡፡አንድ አንባቢ የሚያነበውን ፅሑፍ ይዘቱን በትክክል እንዲገነዘብ ብያንስ ፃሐፊው ማን ነው?ለምን ፃፈው?መቼ? የሚሉ
ጥያቄዎችን በመጠየቅ መልስ ሊያገኝ ይገባል፡፡
የጋዜጠኛው ማስታወሻ ለምን ተፃፈ?
የጥያቄው መልስ ያለው
በገፅ 413 ላይ ነው፡፡‹‹ለራሴው ህልውና ስል እታገላለሁ… በመሆኑም ይህ ጥራዝ ትግል ነው›› በማለት መልሱን በማያሻማ መልኩ
አስቀምጦልናል፤ተስፋየ፡፡የሚታገለው ታድያ ለኢትዮጵያ አይደለም ለራሱ ነው፤ለግሉ! ይህችን መፅሃፍ በመፃፉ እራሱን እንደ አርበኛ
ታጋይ ነው የሚቆጥረው፡፡ተስፋየ ታጋይ ነው፤በብዕሩ ይታገላል፡፡
ማንኛውም ፀሓፊ ሲፅፍ ዓላማ አለው አይደል፤ በተለይም የፕሮፖጋንዳ በለሙያ የሆኑ ሰዎች።የፕሮፖጋንዳ ሰዎች
‹‹ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል›› የሚል ፈሊጥ አላቸው።ጆሴፍ ጎብልስ የናዚ ጀርመን ስመጥር የፕሮፓጋንዳ ባለሙያ ነበር፡፡ ጀርመኖችን ከጫፍ እስከ ጫፍ አነሳስቶ አይሁዳውያንን በግፍ ጨፍጭፈው
እንዲያወድሙ ያደረገው እሱ መሆኑን ታሪክ ዘግቦታል።‹‹ከቻልክ›› ይላል ጆሴፍ ጎብልስ፣‹‹
ከቻልክ እጅግ በጣም ትልቅ ውሸት ዋሽ፤ ያ ውሸት ሁልጊዜ
እየደጋገምክ ተናገር፤ በመጨረሻም ህዝቡ እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል።…..If you tell a lie big enough and keep
repeating it, people will eventually come to believe it.››
ስመጥሩ ቻርለስ ዳሪዊንም እንደ አ.አ በ1871 በፃፈው ‹‹ The Descent of Man…የሰው ልጅ አመጣጥ ›› በሚለው መፅሐፉ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፤ ‹‹ገና በጨቅላ ዕድሜያችን፣አእሯችን አዳዲስ ነገሮችን ለመቀበል እንደ ነጭ ወረቀት
ንፁህ እያለ በቋሚነት የሚቀረፅብን እምነት ላይ ማትኮር አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ልክ ተፈጥሮ የምትቸረንን ያህል ደመነፍሳዊ ባህሪ
ይሆናልና፣የደመነፍሳዊነትን ጭብጥ ደግሞ ምክንያታዊነትን የማይከተል መሆኑን ነው….. It is worthy of remark that a belief
constantly inculcated during the early years of life, whilst the brain is
impressible, appears to acquire almost the nature of an instinct; and the very
essence of an instinct is that it is followed independently of reason.››
ከነዚህ የጥናት ግኝቶች ተነስተው ነው ታድያ የፕሮፓጋንዳ ባለሙያዎች የህዝቡ ስሜት እንዳሻቸው የሚያሽከረክሩት፡፡ይህ
ይቅጥፈት ግቡ እንዲመታ ውሸት ወይም እውነት
የሚመስል ውሸት መደጋገም አለበት፡፡እንደነ ተስፋየ ገብርአብ ያሉ የሙያቸውን ስነ ምግባርና ህግ በማይፈቅደው መልኩ በጠራራ ፀሐይ
ሸጠው የሚበሉ ‹‹ሸሌ ጋዜጠኞች›› ደግሞ ሁነኛ ተላላኪዎቻቸው ናቸው፡፡ይህ ሰው ‹‹የቡርቃ ዝምታ››ና ‹‹የጋዜጠኛው ማስታወሻ››
ሲፅፍ በደምብ አስቦበትና ‹‹የኢትዮጵያውያን
ደካማ ጎን ነው›› ብሎ ባመነበት ሊያጠቃን ስለፈለገ ነው፡፡ይኸውና
አንዴ በልበ ወለድ በሌላ ጊዜ ደግሞ በበሬ ወለደ መረጃዎቹን ሊያወናብደን ብቅ ጥልቅ ይላል፡፡
የአዶልፍ ሂትለር የቀኝ
እጅ ጆሴፍ ጎብልስ ነበር፡፡የጆሴፍ ጎብልስ የፕሮፖጋንዳ መልእክቶች በጀርመናውያን ሰርፀው ለጥፋት እንዲነሳሱ ደግሞ የጁሌስ ስትሬሸር
የጋዜጠኝነት ሙያ በጣም አስፈላጊ ነበር፡፡ስትሬሸር የDer Sturmer(The stormer) ጋዜጣ መስራችና ዋና ኤዲር የነበረ
ሲሆን የጋዜጣው ዋና ዓላማ ደግሞ አይሁዳውያንን ማጥላላት ነበር፡፡ሰውየው ታድያ ከናዚ ሽንፈት በኋላ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሶ
ጥፋቱ ስለተረጋገጠ በሞት ተቀጥተዋል፡፡
የተስፋየ ገብረአብም
ጀርመናዊው ጁሌስ ስትሬሸር ሲያከናውነው የነበረው ተልእኮ ነው እየፈፀመ ያለው፡፡ ኢሳያስ በኢትዮጵያውን ላይ ያለው ጥላቻ ሂትለር
በአይሁዳውያን ላይ ከነበረው ጥላቻ አያንስም፤እንደውም ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ እናም ጀርመናውያን በሂትለር መሪነት በአይሁዳውያን
ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ኢንዲፈፅሙ ጁሌስ ስትሬሸር በመገናኛ ብዙሐን ተጠቅሞ የተጫወተው ሚና ኢሳያስም ኤርትራውያን በኢትዮጵያውያን
ላይ እንዲነሱ የተስፋየ ገብርአብ እርዳታ አልተለየውም፡፡ ተስፋየ የጁሌስ ስትሬሸርነት ተጋባሩ ለመወጣት የሚፈልገው ወደጅ በመምሰል
እኛ ኢትዮጵያውያን እርሰ በርሳችን እንድንናቆርና ሃገራችንም ተከፋፍላ የቀድሞዋ ዩጎዝላቭያ እጣ እንዲደርስባት የሚያስችሉ መርዞች
በመርጨት ነው፡፡
ተስፋየ የኢሳያስ መልእክተኛ
መሆኑን የሚያረጋግጥልን ራሱ እንደፃፈው ‹‹10 ዓመታት የወያኔ ጋዜጠኛና በለስልጣን›› ሆኖ ሲሰራ ከኢሳያስ ጋር የነበረው ገጠመኝ
በመፅሃፉ ላይ አለማስፈሩን ነው፡፡እናስተውል! ተስፋየ ከትላልቅ የህወሓትና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር ለ10 ዓመታት ሲሰራ ከሻዕብያዎች
አንዴ እንኳን ሳይገናኝ ቀርቶ ነው አንዲት ቃል ያልፃፈው? እውነታው ይኸው ነው፤ የሻዕብያ ሰላይ፣የኢሳያስ አምላኪና ተላላኪ ስለነበረ
አሁንም ስለሆነ ነው፡፡ የህወሓት፣የበአዴንና የኦህዴድ ባለስልጣናት ገመና አንድም ሳይቀረው ያወቀ ‹‹ጋዜጠኛና ትልቅ ባለስልጣን››
ከሻዕብያ ባለስልጣናት አንድም ሳያው ይቀራል ብየ አላምንም፡፡የህወሓት ምሲጠሮች አብጠርጥሮ የሚያውቅ ባለስልጣን በትንሹም ቢሆን
የሻዕብያም ያውቃል፡፡
ሌላው የሻዕብያ ተላላኪ
መሆኑን የሚመሰክርልን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ከኢትዮጵያ በግፍ ሰለ ተባረሩ ኤርትራውያን ሲፅፍ ከኤርትራ በግፍ ታፍሰው ስለተባረሩ
ኢትዮጵያውያን አለመፃፉ ነው፡፡ኤርትራውያን ሲባረሩ የኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት እርምጃ ትክክል አለመኖሩን ሲገልፅ ‹‹ በዓደዋ
በኩል የሚያልፍ ኢትዮጵያዊ እትብቴ የተቀበረው እዚህ ነው ሲል እትብትህም ተፈልጎ ይላክልሃል›› ብለው መለሱለት ብሎ ከትቦታል፡፡ስለሻዕብያ
ገመና ግን ትንፍሽ አላለም፡፡
ለመሆኑ ተስፋየ ማነው?
ተስፋየ በጣልያናውያን የውሽት ፕሮፓጋንዳ ታውሮ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ታጥቆ የተነሳ ኤርትራዊ ነው፡፡ጣልያንና ዓረቦች
ኢትዮጵያውያን እርሰበርሳችን እየተባላን አንደነታችን በንፋሳ ላይ እንደተሰጣ ዱቄት በኖ እንዲጠፋ፣ ፍቅራችን ወደ ለየለት ጥላቻ
ተቀይሮ እንደ እስራኤላውንና ፍልስጤማውያን ታሪካዊ ጠላቶች ሁነን እርሰ በርስችን እየተገዳደልን እንድንኖር ይፈልጉ ነበር፤ አሁንም
ይፈልጋሉ፡፡ኢትዮጵያና ኤርትራም እንደ ሁለቱ ኮርያዎች እሳትና ጭድ ሁነው እንዲኖሩ ይፈልጉ ነበር፡፡በቡችላቸው በሻእብያ አማካኝነትም
ውጥናቸው ግቡን መታ፡፡
‹‹የብሾፍቱ ልጅ የሆነ አንደ ዜጋ ይህችን መፅሃፍ ሊፅፋት ሲጀምር ለራሱ
ታማኝ ለመሆን ከህሊናው ጋር ብርቱ ትግል አድርጎአል፡፡›› ብሎ ነው ማስታወሻውን የጀመረው፤ ጋዜጠኛ ነኝ ባይዩ ተስፋየ ገብርአብ፡፡ሰውየው
እውነተኛ ለመምሰል የሚያደርገው ጥረት በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ተስፋየ ‹‹በዚህች መፅሃፍ ውስጥ የሰፈሩት ትረካዎች ‹ግለ - ታሪክ› አይደሉም፡፡የአንድ ጋዜጠኛ እውነተኛ እለታዊ ገጠመኞች ብቻ ናቸው፡፡››፤
ይለንና ‹‹ያ ሰው እኔ ነኝ!›› በማለት ያስረግጥልናል(ገፅ 5)፡፡የተስፋየ የመግብያ ፅሑፍ ቀጥሏል፤ በተጠቀሰው ገፅ ላይ፣‹‹በትረካው
ውስጥ ያልተሟሉ መረጃዎች…ሊያጋጥማችሁ ይችላል፡፡ይህ
መፅሃፍ የታሪክ መፅሃፍ አይደለምና ከዚያ በላይ አትጠብቁ›› ይልና የጋዜጠኝነት ሙያውንና ስነ ምግባሩን ‹‹ሴተኛ/ወንድ አዳሪ››
ያደርጓል፡፡
ጋዜጠኛ ‹‹ሸሌ››
አይደለም፤ እንደመጣለት ‹‹የቃላት ዝሙት›› የሚፈፅም፡፡በጭፍን ጥላቻና በበቀል ተነሳስቶ ያሻውን እንዲፅፍ ወይም እንዲናገር ህግና
ስነ ምግባር አይፈቅዱለትም፤የፈለገው ስልጣንና ብቃት ይኑረው፡፡ገጠመኙ ‹‹እውነተኛ ገጠመኝ›› ሊሆን የሚችለው ደግሞ ጋዜጠኛው ስለተናገረው
ብቻ ሊሆን አይችልም፤ምንጭ ያስፈልጓለ፤እውነትነቱን የሚያረጋግጥለት ዋቢ መረጃ ማቅረብ አለበት፡፡የተሟላ መረጃና ታማኝ ምንጭ ሳይጠቅስ
የሚፅፍ ወይም የሚናገር ጋዜጠኛ ገዜጠኛ አይደለም፡፡የጋዜጠኝነት ስነ ምግባርና የመገናኛ ብዙሐን ሕግ የማያከብር ሰው ‹‹የኸውና፤ጋዜጠኛው
እኔ ነኝ!›› እያለ በጉልበት ጋዜጠኛ ሊሆን አይችልም፡፡
እነዚህ ሁለት ነገሮች
ናቸው የጋዜጠኝነት ስራ በጣም ከባድ፤አስቸጋሪና ከፍ ሲልም አደገኛ የሚያደርጉት፡፡ ተስፋየ ግን ‹‹ያልተሟሉ መረጃዎች›› ቢኖሩም
እኔ ከሰጠኋችሁ በላይ አትጠብቁ እያለን ነው፡፡ማንኛውም ጋዜጠኛ እንደዚህ ዓይነቱ አወዛጋቢ ፅሑፍ ወይም ንግግር ሲያድረግ የህግ
ሰዎች በቅድምያ የሚጠይቁት ‹‹ምንጭ ወይም መረጃ አለህ ወይ?›› ብለው ነው፡፡ካለው ነፃ ይወጣል፤ኬሌለው ግን ይታሰራል፤የዘለፈውን
ዘልፎ፣የዘረፈውን ዘርፎ ሃገር ጥሎ ካልሸፈተ በስተቀር፡፡ከባዱ ነገር ታድያ መታሰሩ ብቻ አይደለም፤ በትልቁ ‹‹ታማኝነት›› ያጣል፡፡ታማኝነት
አጣ ማለት ደግሞ ሙያውን አጣ ማለት ነው፡፡የጋዜጠኞች የመረጃ ምንጭ የሚኖርበት ቀየ(አከባቢ)ና እዛው የሚኖር ማሕበረሰብ ናቸው፡፡ማሕበረሰቡ
ለጋዜጠኞች መረጃ የሚሰጠው ደግሞ ‹‹ታማኞች›› ናቸው ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ስለዚህ አንድ ጋዜጠኛ ሊታመን የማይችል መሆኑን የተደረሰበት
ጊዜ አለቀለት! ክብሩ ይገፈፋል፤ሙያውን ያጣል፡፡ተስፋየ ገብርአብ ግን ያሻውን አድርጎ ሃገር ጥሎ ጠፍቷልና እነዚህ ነገሮች አላሳሰቡትም፡፡
በፈለገው ሃገር እየኖረም ቢሆን የአቶ ኢሳያስ ተልእኮ ሙሉ በሙሉ ከግቡ እስካደረሰ ድረስ ምንም ነገር አያስጨንቀውም፡፡
ተስፋየ አያፍርም፡፡
ዩልኝታም ሲያልፍ አይነካውም፤ ያ በስሜትና በጥላቻ ተነሳስቶ ምንም ዓይነት ምንጭ ሳይጠቅስ የፃፈው መፅሃፍ ‹‹የታሪክ ፀሓፊዎች
የወርቅ ክር መምዘዝና የወርቅ ጉድጓድ መቆፈር ይችላሉ›› ይለናል (ገፅ 6)፡፡እንዴ! ‹‹ያልተሟላና ያልተብራራ መረጃ›› እንዴት
ብሎ ነው ለታሪክ ፃሐፊዎች ‹‹ወርቅ›› የሚሆነው? ወይስ እሱ ያለውና የፃፈው ሁሉ እንደ መጽሓፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁርዓን አሜን ብለው
እንዲቀበሉለት ነው የሚፈልገው? ተስፋየ የመፅሓፍህ ምንጮች እኮ ‹‹እንትና አለኝ››፣‹‹ይባላል››፣‹‹ሲባል ሰምቻለሁ››፣‹‹እየተባለ
ይወራ ነበር›› ወዘተ በሚሉ ቃላት የተሸበቡ ናቸው፡፡በአጠቃላይ ቀልብህ የነገረህ ሁሉ እንደ እውነተኛ ምንጭ ቆጥረህ ነው ያሰፈርከው፡፡
የስነ ፅሑፍ ችሎታህ ለስም ማጥፋት ዘመቻህ ማዋልህ አሳማነትህን ቅልብጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ለሆድህ ያደርክ አሳማ! እውነተኛ ማስታወሻ
ቢሆን ንሮ ከሻዕብያ ጋር የነበረህ ገጠመኝም ባሰፈርከው ነበር፡፡
የተስፋየ ጥላቻ ከባለስልጣኖቻችን ቢሆን ንሮ ምንም ችግር አልነበረበትም፡፡እንሱ
የሚፈልጉትን ሁሉ በጉልበታቸው አሟልቷልና የራሳቸው ስብዕና መጠበቅና ማስጠበቅ አይሳናቸውም፡፡የሚያስዝነው ግን ባለስልጣናትን እያስታከከ
ከኦሮሞ ህዝብ የወገነ በማስመሰል የአማራና የትግራይ ህዝቦችን የወነጅላል፡፡ከትግራይ ህዝብ የወገነ በማስመሰልም የአማራ ህዝብን
ይኮንናል፡፡ብቻ ዓላማየን ይመትሉኛል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች ሁሉ እየመዘዘ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ በተለይም ያለፉት የታሪክ ቆርሾዎች
እንደ እንግሊዛውያን ተክኖ ተጠቅሞባቸዋል፡፡‹‹እንትና አማራ ነው፣እንትና
ትግሬ ነው፣እንትና ኦሮሞ ነው›› እያለ ጎሳና ብሔር የሚዘረዝረው ለምንድን ነው?እነዝያ በቁጥር ኢዚህ ግባ የማይባሉ ባለስልጣናትስ
እንዴት አድርገው ነው ብሔር ሊወክሉ የሚችሉት?ማንኛውም ባለስልጣን የሚወክለው ራሱና ራሱን ብቻ ነው፤ካተረፈም ለልጆቹ፡፡የህ እውነታ
ተስፋየም አልካደውም፡፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን አስመልክቶ በፃፋ ርእስ ላይ በደምብ ገልፆታል፡፡ የባለስልጣናት ልጆች በማንነታቸው እየተሸማቀቁ መሆንን የመንግስቱ ሃይለማርያም ልጆችን
በምሳሌ ጠቅሶ በመፅሃፉ አስፍሮታል፡፡
የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ተቆርቋሪ በመመሰል የጥላቻ መርዙን ይረጫል፤ተስፋየ፡፡ደካማ
ጎናችን ለይቶ በማጥናት ወዳጅ መስሎ የጥላቻ እሳት ያቀጣጥላል፤ በሚቀጣጠለው እሳትም ጋዝ ያርከፈክፋል፡፡ነገር ግን የተስፋይን መፅሐፍ
በጥንቃቄ ለሚያነብ ሰው እውነታው ሌላ መሆኑን አይሰወርበትም፡፡ተስፋየ ደፋርና ዩልኝታ ቢስ ነውና ‹‹ኢትዮጵያን አልወዳትም፤ምክንያቱም
አላቃትም›› በማለት ወጭት ሰባሪነቱን ራሱ መስክሯል፡፡ይህ እውነታ የተናገረው የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያለ እንደሆነ ነው ተስፋየ
ራሱ የሚነግረን፡፡
… የ11ኛ ክፍል አስተማሪው የነበረው መምህር አንለይ“እስኪ ሃገራችሁን የምትወዱ እጃችሁን አውጡ!” ብሎ ጠየቀን ሲል
ይመሰክራል ተስፋየ፡፡
እናም ‹‹ተማሪው በሙሉ እጁን አወጣ።ጥያቄውን በትክክል ሰምቻለሁ።ድፍረቱና አሳቡ ከየትና እንዴት እንደመጣልኝ በፍፁም ባላውቅም እጄን ሳላወጣ ቀረሁ።›› ይላል ጋዜጠኛ ነኝ
ባዩ መርዘኛ ኤርትራዊ፡፡
… ‹‹መምህር አንለይ አይኖቹን ማመን አልቻለም፤ በዝግታ ወድኔ ተራመድና ጠየቀኝ››
‹‹እጅህን ለምንድን ነው ያላወጣኸው?››
‹‹ሃገሬን አለወዳትም›› አልኩ።
‹‹ለምንድን ነው የማትወዳት?››
‹‹አላውቃትም››
‹‹ተነስ›› ሲል አዘዘኝ።( ገፅ 122-123)
የተስፋየ መርዝ መርከስ የሚችለው ይህንን እውነታ በማጤን ነው፡፡ተስፋየ
‹‹ኢትዮጵያን አያውቃትም፤አይወዳትም!!!››፤ስለሆነም በሄደበት ሁሉ የጥላቻ መርዝ ይረጫል፤አቅሙ በፈቀደው ይታገላል፡፡እንደ ጁሌስ
ስትሬሸር የእጁን እስኪቀበል ድረስ በመገኛ
ብዙሐን ለእይታ የሚያማልሉ መርዛም ቅንጥሻራዎችን እያደለ ይገኛል፡፡
እስኪ አስቡት! ተስፋየ ‹‹የብሾፍቱ ልጅ የሆነ አንደ ዜጋ›› ሲል ነበር ወደ
ማስታወሻው የተንደረደረው፡፡ኢትዮጵያ እንደማኛው ዜጋ በእውቀት ኮትኩታ አሳድጋዋለች፡፡እስስት ማንነቱን ሸሽጎም ቢሆን ‹‹በ23 ዓመቱ››
የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅትን እንዲመራ ዕድል
ገጥሞታል፡፡ኢትዮጵያ እንድትለወጥ ከልቡ የሚሻ ቢሆን ንሮ ታድያ እነዝያ ‹‹አጭበራሪ፣አምባገነን፣ፈላጭ ቆራጭ…›› እያለ የሚወቅሳቸው
ባለስልጣናት የሰጡት ስልጣን ተጠቅሞ ለህዝቡ የሚጠቅም ስራ መስራት በቻለ፡፡ነገር ግን ‹‹ኢትዮጵያምን ስለማያውቃት አይወዳትምና››
እንደሌሎቹ ባለስልጣናት የራሱ ጥቅም ሲያሳድድ ከርሞ ውጣ ሲባል ጊዜ ጣቱን በነሱ ላይ መቀሰር ጀመረ፡፡ይህ መፅሓፍ የፃፈው ታድያ
‹‹ኢትዮጵያን አውቆ የወደዳት››፣ወዶም ያዘነላት የመሆኑን ሊነግረን ነው? አይደለም! ተስፋየ ኢትዮጵያን አሁንም አይወዳትም፤አያውቃትም፡፡የሚያውቀውና
የሚወደው ነገር ካለ ‹‹የብሾፍቱ ቆሪጦችን›› ነው፡፡የብሾፍቱ ቆሪጦች ቆሪጥ አድርገውታል፡፡ ተስፋየ በስልጣን በነበረበት ግዜ የትራፊክ
ህግ እንኳን ማክበር አልቻለም፤ሁለት ጊዜ ቀይ መብራት ጥሶ ሲነዳ መገኘቱን ፅፏል፡፡እንደ ጊዜ ሰክሮ ሲነዳ መገልበጡንም ‹‹ሰክሬ
እየነዳሁ ሳለ ኮተቤ መንገድ ላይ ተገለበጥኩ፡፡››(ገፅ 280) በማለት አምኗል፡፡እና የተራፊክ ህግ አታክብር፤ጠጥተህ ንዳ ያለህ
ህወሓት ነው?
ከልክ ባላይ የተጋነነው
ውሸቱን እውነት ነው ብለን እንደንቀበልለት ሲፈልግ ‹‹እሳት ካለ፣ ጭስ ኣለ›› ይለናል፡፡እውነቱን ውሽት ነው ብለን እንድናምንለት ሲፈልግ ደግሞ ‹‹በማሪዋና፣ በቴክኖለጂ መስፋፋት›› ያሳብባል፡፡በሃገራችን
ተስፋ እንደንቆርጥ ለማሳመን‹‹ነገም ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ እንደሆነ አለ›› እያለ የነቢዪነት ደርሻውን ይጫወታል(ገፅ 396)፡፡የባለስልጣናት
በፈጣሪ አለማመንና ጭካኔ ሲፅፍ እንደል ነበር ደግሞ እንደቀልድ አስመስሎ‹‹እሱ የፈጠረን ሰይጣን ያውቃል?›› (ገፅ 399) እያለ
የወደፊቱን ለሰይጣን አሳልፎ ይሰጣል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን የሰይጣን ፍጡራን አይደለንምና ከንተው ሰይጣናዊነት ጋር ልትጨምረን አትችልም፡፡‹‹ኢትዮጵያውያን
አብረው መብላት እንጂ አብረው መስራት አይችሉም›› ብለህ የፃፍከውም
ውሸት መሆኑን በኢትዮጵያውያን የጥምረት ክንድ የሚገነባው የህዳሴ ግድብ ቋሚ ምስክር ነው፡፡
ተስፋየ ‹‹በፈረንጆቹ
የዘመን አቆጣጠር መስከረም 5፣2005 ዓ.ም ሙሉ ጌታ አሸናፊ የተባለ ሰው ethiomedia.com ላይ እኔን አስመልክቶ ሁለት
ውሾቶችን ፅፎ አገኘሁት፡፡የመጀመርያው ከኢትዮጵያ ስኮበልል ግማሽ ሚልዮን ብር መዝረፌ ነበር፡፡››(ገፅ 293)፡፡አዎ! እናውቃለን፤
እንተን የሚመለከቱ መረጃዎች ሲፃፉ ሁለም ውሸት ናቸው፡፡ውሸት ቢሆን ታድያ አንድ ነጭ ‹‹ዘመዶችህ በራሃብ እያለቁ አንተ እንዴት
ወፈርክ?›› (ገፅ 398) ብሎ የጠየቀህ ምን አይቶብህ ነው?እውነታው አንተ የምትወነጅላቸው ባለስልጣኖቻችን የሃገር ሃፍት ሲዘርፉ
አንተም የቻልከውን ያህል ዘርፈህ ሸመጠጥክ፤ ከልክ በላይ በላህ፤ጠጣህና አሳማ መስለህ ቆጭ አልክ፡፡የህን የታዘበ ነጭም ‹‹ዘመዶችህ
በራሃብ እያለቁ አንተ እንዴት ወፈርክ?›› ብሎ ጠየቀህ፡፡በገፅ 388 ላይ ‹‹በወያኔ ጊዜ ጋዜጠኛና ባለስልጣን ሆንኩ፡፡›› ‹‹እንደ
ግለ ሰብ ተጠቃሚ የሆንኩት በወያኔ ዘመን ነው…›› ብለህ የፃፍከው ተሳስተህ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ልትክደው ብትሞክርም
‹‹በወያኔ ዘመን›› ተጠቃሚ ሆነሃል፡፡ውሸቱ ምኑ ላይ ነው?
የጋዜጠኝነት ሙያህ ለሆድህ ስትል መሸጥህ የሚያሳየው የመለስ ገመና ያወጣህ
መስሎህ የፃፍከው እውነታ ይመሰክራል፡፡
…‹ …ለመለሰ ዜና ‘ሁሉንም
እናውቃለን!’ የሚል መልእክት ንገረው።እሱ ሴት ልጁን በእንገሊዘኛ ቋንቋ እያስተማረ መሆኑን ሰምተናል! ምነው ታድያ ብትግርኛ ሳያስተምራት
ቀረ? የታገለው በቋንቋችን ስላልተማርን ተበድለናል ብሎ አልነበረም? ምነው ታድያ ሴት ልጁን ከትግሉ ፍሬ ሳያስቀምሳት ቀረ? የማናቅ
አይምሰላችሁ! የባለስልጣናት ልጆች አፋቸውን በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየፈቱ አይደለም እንዴ? ‘እኛን ደግሞ በዶርዚኛ ቋንቋ በመማር
መብታችሁን አስከብሩ!’ ትሉናላችሁ።እኔ ልጆቼ በአማርኛ ቋንቋ እንዲማሩ ነው የምፈልገው።ቢቻል ደግሞ ብእንግሊዝኛ! ምክንያቱም ልጄ
አማርኛ ከቻለ በመላ ኢትዮጵያ ተዘዋውሮ የመስራት ዕድል ያገኛል።እንግሊዘኛ ከቻለ ደግሞ በመላ አለም! በዶርዚኛ ተማሩ የምትሉን
ልጆቻችን ሸማኔ ሆነው እንዲቀሩ ነው? በል እንግዲህ ጋዜጠኛ ነኝ ካልክ ይህን ሳትቀንስ ፅፈህ መለሰ ዜና እንዲያንባት አድርግ!
አትፍራ… ‘ማነው ይህን ያለው?’ ካሉህ ወንድሙ ጩበሮ ነው ብለህ ተናገር! ዶርዜ ከተማ፣የቤት ቁጥር ያውልህ፣ ፃፍ! ከፈራህ ደግሞ
አሁንኑ ንገረኝ።›(ገፅ 129)
ብለህ ፅፈህ ስታበቃ በገፅ 130 ላይ ደግሞ የራስህ ወራዳነት እንደሚከተለው
አስፍረኋል፡፡
አንተ
ለሆድህ ያደርክ የተሰጠህ አደራ ከመብላት ወደ ኋላ የማትል ከሃዲ ነህ፡፡ለዚሁ ክህደትህስ ይቅርታ ጠይቀህ ታውቃለህ?
‹…መለሰ ሴት ልጁን በእንገሊዘኛ ቋንቋ እያስተማረ መሆኑን
ሰምተናል! ምነው ታድያ ብትግርኛ ሳያስተምራት ቀረ? የታገለው በቋንቋችን ስላልተማርን ተበድለናል ብሎ አልነበረም? ምነው ታድያ
ሴት ልጁን ከትግሉ ፍሬ ሳያስቀምሳት ቀረ?› የሚለውን ቆርጬ ጣልኩት። ከሁለት ሳምንታት በኋላ የመለስን ስሞች በሙሉ ቆራርጬ በመጣል
ቀሪውን በእፎይታ መፅሄት አተምኩት።
ተስፋየ ‹‹በአለም ላይ ሶስት አይነት ጋዜጠኞች አሉ የሚል ነገር አንድ ቦታ አንብቤያለሁ።የመጀመርያዎቹ ‹እንዴት ልፃፍ› ብለው አለቆቻችውን ይጠይቃሉ።ሁለትኛዎቹ ‹እንዴት ላስብ› ብለው ጌቶቻቸውን ያስፈቅዳሉ።የመጨረሻዎቹ ሁለቱንም ጥያቄዎች የሚያቀርቡት ለራሳቸው ነው።እኔ ከሁለተኛው ምድብ አከባቢ እየተንገላታሁ ነበር…›› (ገፅ 138) ሲልፅፏል፡፡‹‹ነበር››
አይደለም ተስፋየ! አሁንም ድረስ ‹‹እንዴት ልፃፍ፣እንዴት ላስብ›› እያልክ አሳዳሪ ጌታህ ኢሳያስን እየተለማመጥክ እንደምትኖር
ፅሑፎችህ ምስክሮች ናቸው፡፡
በገፅ 145 ‹‹…የሙሉ ጌታ ሉሌን፣አጥፍቶ መጥፋት ትረካ ከኔው ገጠመኞች
ጋር እያዋሃድኩ፣አንዳንድ ጊዜ፣ለመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ የልጆች መጫወቻ የሆነች ሃገር በአለም ላይ ትኖር ይሆን እያልኩ አስብ ነበር።››ስትል
ስለማታውቃትና ስለማትወዳት ኢትዮጵያ የዘንክ በመምሰል ፅፈሃል፡፡አዎ! እምዬ ኢትዮጵያን ብዙ ከሃዲወች ተጫውተውባታል፤አሁንም እየተጫወቱባት
ነው፡፡ግን፣ነገር ግን ያንተን ያህል አይሆንም፡፡‹‹ኢትዮጵያውን አላውቃትምና አልወዳትም›› ብሎ የፃፈ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ከሃዲ አንተ ብቻ ሳትሆን አትቀርም፡፡እንደዚህ
ዓይነት የክህደት ቃል ካንተ መፅሐፍ ውጭ አንብቤ አላውቅም፡፡
መሪዎቻችን ራሳቸው
የሚያስቀድሙ ሆዳሞች፣በፍቅረ ስልጣን የታውሩ አምባገነኖች፣ በድህነት አለንጋ ከሚገረፈው የደሃው መንጋጋ ለመንጠቅ ወደ ኋላ የማይሉ
ስግብግቦች … መሆናቸውን አናውቃለን፡፡ግን አንተም ‹‹ጋዜጠኛና ባለስልጣን፣የዝርፍያውን፣የጥቅሙን ተካፋይ›› ነበርክና ከነሱ የማትሻል
ከሃዲ ነህ፡፡ያንተ ክህደት፣ ያንተ ስግብግብነት፣አንተ የዘረፍከው የኢትዮጵያ ሃብት ሌሎቹ ከዘረፉት ቢበልጥ እንጅ አያንስም፡፡እንደውም
ሃገር ወዳድ መስለህ ሃገርና ኅዝብ የሸጥክ ከሃዲ ነህ፡፡ተኩላ ነህ! የበግ ለምድ የለበስክ ተኩላ፡፡

No comments:
Post a Comment