ተማሪዎቹ የትምህርት ፍላጎት እንደሚያንሳቸውና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መስርታዊ እውቀት እንደሌላቸው አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር ተናግረዋል።
የላይበርያ ትምህርት ሚኒስተርዋ ወይዘሮ ዴቪድ ታርፓ አንድ ተፈታኝ እንኳን የዩኒቨርሲቲ መግበያ ፈተናውን ማለፍ አለመቻሉን ለማመን መቸገራቸውን አስታውቀዋል። << የተምህርት ተቋሞች ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ፈተናውን የወሰዱ ሁሉም ተማሪዎች ወድቀዋል ሲባል ግን ያጠራጥራል።ዘር ለማጥፋት ይሚደረግ ጅምላ ጭፍጨፋ ሊባል ይችላል>> በማለት ነው ሁኔታውን የገለፀት።ስለሆነም የተማሪዎቹ የፈተና ውጤት ማየት እንደሚፈልጉም አስታውቀዋል፤ወይዘሮ ዴቪድ።
ሞሞዱ ጌትዋህ የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ቃለ አቀባይ በቦኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በውሳኔው እንደሚፀናና ስሜታዊነት ውሳንያችው እንደማያስቀይራችው ተናግረዋል።
**************************************************************************************
<<ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም>> አሉ አበው።አሁን ጉዱን ሰምተናል፤መስከረም ሆይ ተሎ ነይ።
No comments:
Post a Comment