ሰላም ለናንተ ይሁን ለሰላም ወዳድ ወገኖች ሁሉ በያላቹበት!ኪሮስ አለማዮህ በሚስረቀረቅ ድምፁ “ሰላም!” እያለ በትግርኛ የዘፈናት ዘፈን ጋብዤችኃለሁ።የኪሮስ ዘፈን ይከፈትና “ኣቲ ሰላም አበለኺ?ፍቕሪ ሰላም ይውረድ እት ናይ ዓንተዎ...ሰላም ሆይ የትነሽ?የድሮው ፍቅርና ሰላም ይምጣልን” እያልን ስለ ሰላም ትንሽ እንጨዋወት።
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አውራ
ጎዳናዎች በሰላማዊ ሰልፈኞች
ተጨናንቋል።የታክሲ ሹፌሮች፣የዩኒቨርሲቲና የሁለተኛ
ደረጃ ተማሪዎች
በጋራ መሬት
ላራሹ የሚለው
መፈክር አንግበው በአንድ
ድምፅ ይጮኻሉ።
የ40 ዓመታት
የዕድሜ ባለፀጋው ዘውዳዊ
አገዛዝ ከስረ መሰረቱ
አናጉት።ቤተ መንግስታቸው አቅጣጫዋን
ስታ በማዕበል
እንደምትናወፅ መርከብ በዥዋዥዌ
ተናጠች።የአፄ ሃይለስላሴ ወንምበር
በርዕደ መሬት የተመታች
ያህል ተርገበገበች፤ተናወፀች።አፄ
ሃይለስላሴ መቀመጫቸው
ቆረቆራቸው፤አናታቸው ላይ የተደፋው
ዘውድ በድንጋይ
እንደተመታ ደወል አንቃጨለ።የጆሮ
ታምቡራችው ሊፈነዳ ትንሽ
ቀረው፤ሆዳቸው ተምበጫበጨ።የ80 ምናምን
ሽማግሌ ገላቸው ተንዶ
ቁልቁል እንደሚውርድ የካብ
ክምር ይንቋቋል፤ይንገራገጫል።
ይህን ሲከታተሉ የነበሩ
ድልብ ወታደሮች
የአፄ ሃይለስላሴ
ወንምበርን ተመኟት፤ክልክ በላይ
ቋመጧት።እናም መስከረም 2፣1967
ዓ.ም
ሽማግሌውን ከመቀመጫቸው ገፍትረው
አሽቀነጠሯቸውና እሳቸውን ከወንምበሩ
ስር ቀብረው
እወንምበሩ ላይ ዘጭ
አሉበት።ስዩመ እግዚአቢሄሩ አፄያችን
ከሚኒስትሮቻችው ጋር ወደ
መቃብር ወረዱ።የአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች በደም ጨቀዩ፤የእናቶችና የህፃናት ዓይኖች ደም አለቀሱ።ነፃ አውጭዎች እንደ አሸን
ፈሉና ሃገራችን ነፃነቷን አሳጧት፤ህዝባችን የሰላም አየር መተንፍስ ናፈቀው።
ሃገር ሰላም አጣች።ኢህአፓዎች በዘመቻ ነጭ ሽብር የተቀናቃኞቻቸውን ቀይ ደም
አፈሰሱ።ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ተመታ፤የህዝብ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሁሉ እሾህን በእሾህ ለመንቀል ተራወጡ።አልተቻለም።የወንድሙን
ደም ላፈሰሰው ሁሉ ደሙ እንዲፈስ ሲደረግ፤ሰው ሁሉ በደም ሽታ ሰከረ።ስካሩም በመላው ኢትዮጵያ ተዛመተ።ሃገር አኬልዳማ ሆነች።የሃገራችን
ከተሞች የደም ኩሬዎች ሆኑ፤የደም ኩሬዎቹ እየተገጣጠሙ የደም ሃይቅ ሰሩ።ከደም ሃይቁም ብዙ፣እጅግ በጣም ብዙ የአባይ ወንዞች ፈልቀው
ህዝባችን ከነንብረቱ ጠራርገው ወሰዱት።ሃገራችን ሰላሟን ብቻ ሳይሆን ስሟንም ጭምር አጣች።የክፋት መናገሻ ሆነች።የዓለማችን የድህነት፣የኋላቀርነት፣የመሃይምነት…በጠቅላላው
የመልካሙን ሁሉ ጭራ ሆነች።
የቻርለስ ዳርዊን የመኖር
ብቃት(survival of the fittest)
ተግባራዊ ሆነ።ትላልቅ ዓሳዎች
ትናንሾቹን ዋጥ አደረጓቸውና
“ሃገረ ገዢዎች
እኛው ነን!”
ብለው አወጁ።የኢትዮጵያ
ህዝብ ደም መፋሰሱን ሰልችቶታል፤የሰላም አየር መተንፈስ ናፍቆታልና ይሁን ብሎ ተቀበላችው።አቧራና ወበቅ የተቀላቀለበት ቢሆንም ህዝባችን
ትንሽ የሰላም አየር መተንፈስ ጀመረ።ቀስ በቀስ አቧራው በኖ ጠፋ፤ወበቁም ተስተካከለ፤የሰላም አየር በሽ በሽ ሆነ።እናቶች እፎይ
ማለት ጅመሩ።ህፃናት አድገው ወደ ትምህርት ቤት እንጅ ወደ ጦርነት መማገዳቸውን ቀረ፤ታሪክ ሆነ።ሃገር ተረጋጋች።
የሃገራችን ከተሞች፣የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ደም ሳይሆን አስፓልት ጠጡ።ሽገር
የሬሳ ክምር ሳይሆን የሰማይ ጠቀስ ፎቆች ስብስብ ሆነች።በየጎዳናው የሰላም ዘምባባ ሲያቆጠቁጥ ይታያል።ሃገራችን የቁልቁል ጉዞውን
ትታ ሽቅብ መንጠራራት ጀመረች።
እንሆ ዛሬ! ልማደኛው ጅኒ የሚተፋው የሰላም ጥንቅ ዶፍ የሽቅብ ጉዞዋን ቢያንቀራፍፈውም
ሊገታው ግን ከቶ አልተቻለውም።የዓለም መገናኛ ብዙሓን ስለሃገራችን ድህነት፣ጦርነት፣ረሃብና ጠኔ መዘገቡን ትተው እንደኮሶ እየመረራቸውም
ቢሆን ስለ እድገት፣ብልፅግና፣ስለ ታሪካዊ ገናናነታችን መዝገብ ጀመሩ።
ይህን የታዘቡ ዓረቦች
በቅናት ቆሽታችው አረረ፤ዓይናቸው
ደም ሰርቦ
እኛን ደም
ለማፋሰስ “ሳላፊስቶችን” አስልጥነው፤ሽብርተኝነት፣አክራሪነትና
ፅንፈኝነት አስታጥቀው ወደ
ሃገራችን ላኩብን።እኛ ኢትዮጵያውያን
ቀርቶ ራሳቸውም
ጭምር በተረጋጋ
መንፈስና በመክንያታዊነት ብያጤኑት
መስማት የማይፈልጉትን እኛ
እንድንሰማላቸው “ድምፃችን ይሰማ”
በማለት አስተጋቡ፤ጮኹ።
እናም ሰላማውያን ሞስሊም ወገኖቻችን በተሰባሰቡብት ሁሉ ሰርገው እየገቡ ሰላም
ይነሷችው ጅምሯል።እውነት እንነጋገር ከተባለ፤እነዚህ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፈኞች ሳይሆኑ ፀረ ሰላም ነውጠኞች ናቸው።ሃይማኖታዊ በዓል
በሚከበርበት ቀን ሁሉ ፅንፈኛ አመለካከት ማራመድ ምን ይሉታል።የዘንድሮው የዒድ በዓል ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚከናወንበት ሳይሆን
ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚራመድበት ነው የሚመስለው።ኢህአዴግ እንደዛ ስላል አይደለም! በዓይናችን ያየነው፤በጆራችን የሰማነው እውነት
ነው።የማይሆን ነገር(ብያንስ ባሁኑ ሰዓት)በጭኾት እንዲሆን መሞከር ያልታሰበ ደም መፋሰስ እንዲ ከተል መፀለይ ነው።ፆምና ፀሎት
ለሰማያዊ ፀጋዎች የሚደረጉ ልመናዎች እንጅ ሃይማኖታዊ አገዛዝ በሌሎች
ለመጫን የሚፈፀሙ ከሆነ ፖለቲካዊ አክራሪነት እንጅ ሌላ ስም ሊሰጣቸው አይችልም።
በዛሬው ቀን ዒድ ተከብሯል፤ ወደ ስተድየም የሚያስገቡ የአዲስ አበባ አውራ
ጎዳናዎች የቆሻሻ ክምር ሆኗል።ከፕያሳ እስከ ለገሃር ድረስ በእግሬ ነበር የሄድኩት።አስፓልቱ ሁሉ እንዳለ በካርቶን፣በወረቀት፣በተቀዳደደ
ማዳበርያ፣ በፕላስቲክ፣በሴቶች ጫማ፣በሽበጥ ተሽፍኗል።አዲስ አበባ የካርቶን፣የወረቀት፣የፕላስቲክ
ክምር ሆናለች…
“እንዴ! ይዘውት የመጡትን
ሰግደው ሲጨርሱ ይዘውት
አይመለሱም እንዴ?” ስል
ለአዷ መንገደኛ
ጠየኳቸው። “ራብሻ ተነስቶ ነበር፤ብዙ
ሰው ሳይጎድ
አልቀረም፤ኸረ እንደውም ጥይትም
ተተኩሷል።ዘመኑ ጥሩ አይደለም
ልጄ” አሉኝ።እዎ፤አብዛኛው
ወገናችን በዘመን ያላክካል።እውነታው ግን ሌላ ንው፤ሰው ሰውን ይባላል እንጅ ዘመን ሰው አይበላም።ዘመን ሁሌም ያው ነው፤ፀሃይ ትወጣለች
ትጠልቃልች፤አለቀ።
የሰው ልጅ ሲከፋ
ግን “ዘመኑ
ክፉ ሆነ”
ይባላል።ሰው ከእንስሳ የሚለየው
ማሰብ ሲችል
ብቻ ንው፤
ማሰብ የተሳነው
ጊዜ አውሬ
ይሆናል።ጉልበተኛው አውሬ ደካማውን
ይሰለቅጠዋል፤ያሻውን ያደርገዋል።በርሱ ሳምባ
እንዲተነፍስ፤በርሱ አእምሮ እንዲያስብ፤በርሱ
ህሊና እንዲያስተውል
ያስገድዷል።ያኔ እጣፈንታው እንደ
በግ መንጋ
ሰጥ ለጥ
ብሎ
መነዳት ብቻ ሲሆን
የፈለገውን ይሆንለታል።የኸውና ብዙ!
እጅግ በጣም
ብዙ! አውሬዎች
ተንስተውብናል። “እኛ
ያልናችሁ ሁኑ፤አልያም ከምድረ
ገፅ ጥፉ”
እያሉን ነው።የኸውና የንፁሃን ደም ያፈሱት ጀምሯል! ዓላማቸውም አንድና አንድ ነው፤እሱም እምዬ ኢትዮጵያን ዳግም የደም ሃይቅ ለማድረግ። እናት ሃገራችንን ዳግም አኬልዳማ ለማድረግ። ይሳካላቸው ይሆን?
ጊዜው ሲደርስ
ይታወቃል።
ለሰላም ወዳድ ሞስሊም
ወገኖቻችን ዒድ ሙባርክ! ፆመ ፍልሰታን በመፆም ላይ ያላችሁ ክርስትያኖችም
መልካም ፆም!
ለፀረ ሰላሞቹ
ግን አላውቅም፤ከፈለጉም
ገደል ይግቡ።ለአክራሪዎቹ፣
“ኢትዮጵያ በሸሪዓ ህግ ትመራ፤የእስልምና እምነት ከሚከተሉ በስተቀር ሌላው ይውደም! የክርስትና እምነት ከሚከተሉ በስተቀር ሌላው
ይጥፋ!” የሚል እርኩስና ዝቃጭ አስተሳሰብ እውን ለማድረግ የሚፍጨረጨሩትን ግን ከነዝቃጭ አስተሳሰባችሁ ገደል ግቡ እንጅ ሌላ ምን
ይባላል?

No comments:
Post a Comment