Tuesday, September 17, 2013

ኤልያስ ክፈሌ አሸባሪነቱን አመነ




መስከረም 6 ቀን 2000 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ እንደመጣሁ የሚከራይ ቤት እስከማፈላልግ ድረስ በጥገኝነት ከዘመዶች ጋር እኖር ነበር፡፡ያስጠጉኝ ዘመዶች ባልና ሚስት ሲሆኑ በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ወታደሮች የነበሩ ናቸው፡፡2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ስለነበር ወሬው ሁሉ ስለህዳሴ፣ ስለ እርቀሰላም፣ስለ ኢትዮጵያውያን አንድነት የሚሰብክ ነበር፡፡ብዙ በውጭ ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባዓሉን ለማክበር ይተማሉ፡፡ዘፈኖቹ ሁሉ ሚሊኒየም ሚሊኒየም ይላሉ፡፡
እኔ በነበርኩበት ቤት ግን የ97ቱ ግርግር ያለፈ አይመስልም ነበር፡፡ሰዎቹ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከገዢው ፓርቲ ጋር ያላቸው ቅሬታ ያንፀባርቃሉ፡፡የእኔ ትግራዋይነት እያወቁም ቢሆን በተጋሩ ላይ ያላቸው የከረረ ጥላቻ ከመናገር አያቅማሙም ነበር፡፡አንዳንዴም በህወሓት ላይ የነበረኝ አመለካከትና ግንኙነት እየጠየቁ ለውይይት ይጋቡዙኛል፡፡ነገር ግን ለጊዜውም ቢሆን የነሱ ጥገኛ ነበርኩና ከነሱ ጋር ለመከራከር ድፍረት አልነበረኝም፡፡ያሉትን ቢሉ በዝምታ አልፈው ነበር፤የውስጤ እንዳለ ሆኖ፡፡ነገርየው ሲከርም ወደ መፃደጃ ቤት የምሄድ እያስመሰልኩ ከቤት እወጣ ነበር፡፡
አንድ ቀን ግን ያ ስሸሸው የነበረው ነገር ገፍቶ መጣና ከርክሩ ተጀመረ፡፡ሰዎቹ ታላቅ ወንድሜ መሞቱን በስልክ ተነግሯቿል፤እናም ባልና ሚስት በጋራ ሆነው ከነሱ ጋር የምንነጋገር በት ጉዳይ መኖሩንና ከቤት መውጣት እንደሌለብኝ ነገሩኝ፡፡ምናልባት ቤት ፈልግ ይሉኝ ይሆናል እያልኩ ሳስብ ነበር፤ ነገር ግን ከፖለቲካ ጋር የተገናኘ ውይይት ተጀመረና እኔም ቀስ በቀስ ወደ ውይይቱ ገባሁ፡፡ውይይቱ እየተጋጋለ ሄዶ ክርክር ሆነ፡፡የ97ቱ የህዝብ ዓመፅ ተነሳና ክርክሩ አሟሟቅነው፡፡
እኔ ዓመፁ ትክክል አልነበረም፡፡በተለይም የህዝብ ንብረት የሆኑ የከተማ አውቶብሶች ማቃጠልና መስባበር፣ የህንፃዎች መስታወት መስባበር፣ ሱቆችና ስፐር ማርኬቶች መዝረፍ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ዘመቻ ማካሄድ ስህህተት ነበር እያልኩ ተከራከርኩ፡፡በተለይም የበድሩ አደምና የታድዮስ ታንቱ ንግግሮች እያነሳሁ እሞግታለሁ፡፡
የቤቱ አባወራ ግን አትሳሳት፤ዓመፁ ትክክል ነበር ብለው ሞጎቱኝ፡፡ስህተት መሆኔን ለማሳመንም ህወሓት በረሃ እያለ ድልዮችን ያፈርስ፣ የህዝብ ባንኮች ይዘርፍ፣ መኪኖች(የህዝብ አውቶብሶችም ጭምር) ሲያቃጥል፣ በአጠቃላይ የሃገሪቱ መሰረተ ልማቶች ያወድም እንደነበርና አመፅ ባለበት ሁሉ ይህ ነገር ልሙድ መሆኑን ተረክሉኝ፡፡
የኔ መልስ ደግሞ ማንኛውም አውዳሚ ተግባር ማውገዝ አለብን እንጂ እንደ አርአያ ወስደን ልንደግመው አይገባም ብየ ተከራከርኩ፡፡‹‹ሁለቴ መሳሳት ስህተቱን ያባብሰው እንደሆነ እንጂ አያስተካክለውም›› ስለሆነም ማንኛውም የተሳሳተ አካሄድ በማንም ይፈፀም አበክረን ማውገዝ አለብን፡፡‹‹ብልሆች ከሌሎች ስህተቶች ይማራሉ፤ ሞኞች ግን ከራሳቸው ስህተት ነው የሚማሩት›› ብየ ለማስረዳት ሞከርኩ፡፡አልተግባባንም፤ ባለመግባባት ተግባብተንም ተለያየን፡፡
የሃገራችን ችግሮች የማይፈቱት ካለፉት ስህተቶቻችን ተምረን አካሄዳችን ስለማንቀይር ነው፡፡የዘመነ መሳፍንት ስህተቶች በተከታታዮቹ ነገስታት ተደጋግሟል፡፡የአፄ ቴወድሮስ ስህተቶች በአፄ ዮሃንስ 4ኛ ተደግመዋል፤የአፄ ዮሃንስ 4ኛም በአፄ ምንሊክ ቀጥሏል፤ከዛም በአፄ ኃይለስላሴ፤ከዛም በደርግ አሁን ደግሞ በኢህአዴግ እያሉ ከላይ ከላይ እየተደራረቡ እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል፡፡ለምሳሌ አፄ ምኒሊክ ኤርትራን ለጣልያን ፈርመው አስረከቧት፡፡አፄ ኃይለስላሴ በፌደሬሽን አማካኝነት ቢመለሷትም ዳሩ ፌዴረሽኑን ሰረዙትና ነገርየው ተበላሸ፡፡
የባሰው አይን አውጣ ስህተት የተፈፀመው ግን በዘመነ ኢህአዴግ ነው፡፡ህወሓቶች(በተለይም ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ) የኤርትራ መገንጠልን ምንም ሳያቅማሙ ነበር የተቀበሉት፤ ለተግባራዊነቱም ብዙ ሰርቷል፤አንዳንዴም ከሻዕብያ በላይ፡፡እናም ሃገራችን የወደብ ደሃ አደረጓት፡፡ ከሻዕብያ አብረውም ደርግን ጥለዋል፤ ‹‹የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው›› በሚባለው አቋም እየተመሩ፡፡ይህ አካሄድ ግን የህወሓቶች እርኩስ ተግባር ሆኖ አልቀረም፡፡ዛሬም እነ ጉንበት 7፣ኦነግ፣ኦብነግ ወዘተ እንደ ፍቱን የስልጣን መወጣጫ ርካብ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡በሰላማዊዎቹ ተቃዋሚዎችም ቢሆን ይህ ‹‹የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው›› መሳይ አከሄድ ሲተገበር ይታያል፡፡
የግንቦት ሰባቱ ደጋፊና የኢትዮጵያ ሪቪው ድረ ገፅ(የብዙ በሬ ወለደ ዘገባዎች ምንጭ) ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ ከኢሳት ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ በፌስቡክ ሲንሸራሸር አገኘሁትና ተመለከትኩት፡፡ሰውየው የሼህ አላሙዲ ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሶ በእንግሊዝ ሃገር ሁለቴ የገንዘብ ቅጣት ተፈርዶበታል (በድምር $355,000).በሶስት የተለያዩ የሽብርተኝነት ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱም በሌለበት በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የሃገራችን ፍርድ ቤት እንደወሰነበት የሚታወስ ነው፡፡እናም ጥያቄው ከዚህ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡
ኤልያስ ምንም ሳያቅማማ እንዲህ አለ፡-
እርግጥ እኔ እንደዚያ ባደርግ ደስ ይለኛል፡፡ አሁን የኤርትራ መንግስት ገንዘብ ቢሰጠኝና ሀገር ውስጥ ያሉትን ኢትዮጵያውያንን እያስተባበርኩኝ የወያኔ ፋብሪካ ባቃጥል፤ የኤሌክትሪክ መስመር ብበጣጥስ ምናምን ብል ደስ የሚለኝ ነገር ነው፡፡ በዛም ከተከሰስኩኝ ደግ አደረግሁኝ የሚል መልስ ነው እንጅ የምሰጠው እኔ አላረግኩም አልልም፡፡ ግን በእኔ አመለካከት እነዚህ ነገሮች መደረግ ለባቸው፡፡ ወያኔን በኢኮኖሚው ማዳከም አለብን፤ የወያኔን ፋብሪካዎች ሳቦታጅ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ወያኔ የሚጠቀምባቸውን መዋቅሮች ሁሉ ማዳከም ያስፈልጋል፡፡
የኸው ነው የሃገራችን መድሃኒት ያልተገኘለት ተላላፊው በሽታ፡፡ከትናንት በስትያ መኖሩን ታሪክ ይነግረናል፤ ትናንት ሃገራችን ሲያወድም በዓይናችን አይተነዋል፤ዛሬም የኸው አለ፡፡ኢህአዴግ ወይም ኤልያሳውያን አጠራር ‹‹ወያኔ›› የፋብሪካዎች፣የመብራት፣የቴሌኮምኒኬሽንና የውሃ ፍሳሽ መተላለፍያ መስመሮች ባለቤት አይደለም፡፡‹‹ወያኔ›› የሃገራችን ኢኮነሚ ባለቤት አይደለም፡፡ህገ መንግስቱም አይፈቅድለትም፡፡እነዚህ ተቋማት የኢትዮጵያ ህዝብ ናቸው፤ ህዝብ በሚከፍለው ግብር(ታክስ) የተቋቋሙ ናቸው፤ብህዝብ ላብ ነው የተገነቡት፡፡አገክግሎታቸውም ቢሆን ለ‹‹ለወያኔ›› ከሚሰጡት ይልቅ ለህዝቡ የሚሰጡትን ይበልጣል፡፡ጉዳት ቢደርስባቸው ይበልጥ የሚጎዳው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ‹‹ወያኔ›› አይደለም፡፡የህዝብ ተቋሞችን የሚያወድሙና ለማውደም የሚያስቡ ግሰቦች ደግሞ ህዝቡ ያገላቸዋል፤ ይተፋቸዋል እንጂ የተም አይደርሱም፡፡ይህ ዓይነት አካሄድ ጊዜው አልፎበታል፡፡
እነዚህ ቶቋሞች በማውደምም(ሳቦታዥ በማድረግ) የ‹‹ወያኔ›› ኢኮኖሚ አይዳከምም፡፡የሚዳከመው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብቻ ነው፤የሃገራችን ኢኮኖሚ እማ አሁንስ ደካማ አይደለም እንዴ?
መብራት ለሳምንታት እየጠፋ እየተቸገርን አይደለም ያለነው?በውሃ እጦት ያልተቸገ ኢትዮጵያዊስ የት ይገኛል(ከድያስፖራዎች በስተቀር)? የቴሌ አገልግሎት የሞተ ነው፡፡ታድያ እኛ በመብራት፣በውሃና በቴሌ መቆራረጥ ስንማረር ኢህአዴጎች መቸ ሲቸገሩ አየን? ብዙ ፋብሪካዎች ስለሌሉ አይደለም የስራ አጡ ብዛት እንደአሸን የፈላው? እንዚህ ሁሉ ተደማምረው የሃገራችን ኢኮኖሚ አዳከሙት እንጂ ‹‹ወያኔ›› ግን አልተዳከመም፤ በሃገራችን ድህነት እየተገረፈ ያለው ህዝቡ ነው እንጂ ኢህአዴግ አይደለም፤ የህዝብ ልጆች እንጂ የኢህአዴግ ባለስልጣናትና ልጆቻቸው እማ በውጭ ሃገሮች እየተዝናኑ በመማር ላይ ናቸው፡፡ሃገራችንን ከዚህ በታች ለማዳከም የሚደረገው የአክራሪዎች ጥረት አሳፋሪ ነው፡፡ኢትዮጵያ ማዕቀብ እንዲጣልባት በየኤምባሲዎቹ እየዞሩ የሚወተውቱ የድያስፖራ መርዛም አክራሪዎች የበሽታ እንጂ የጤንነት አይደለም፡፡
ኢህአዴግ የሚዳከመው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማሽመድመድ ሳይሆን ከህዝብ በመነጠል ብቻ ነው፡፡ይህ እውን የሚሆነው ደግሞ ድህነት በማጥፋት(በመቀነስ)ና ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ተምሮ መብቱና ግዴታው ጠንቅቆ በማወቅ መብቱን እንዳይነኩበት ዘብ መቆም ሲችል ነው፡፡ድህነትና ኋላ ቀርነት የምናባብስ ከሆነ ግን ህዝቡ ስለመብትና ግዴታ ያለው እውቀት ውሱን ስለሚሆን የጨቋኞች ሲሳይ ሆኖ ነው የሚቀጥለው፡፡ስለዚህ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መጉዳት ብሎም ማዳክም ማለት የህዝቡን ንቁ ተሳተፎ ማቀጨጭ ማለት ነው፡፡ህዝቡ በንቃት ካልተሳተፈ ደግሞ የራሱ ስልጣን ባለቤት መሆን አይችልም፤ስልጣኑ በሃይለኛ በወሮ በሎች ይነጠቃል፡፡
እነ ኤልያስ ግን ይህ ነገር አይገባቸውም፤‹‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›› ነውና የጠነባው ማንነታቸው ከድጡ ወደማጡ ይጨምሩታል፡፡እነዚህ ሰዎች በበለፀጉ ሃገሮች መኖር ከጀመሩ ብዙ ዓመታት አስቆጥረዋል፤ ነገር ግን ‹‹‹ወንዝ ውስጥ የሚኖር ድንጋይ መቼም ቢሆን ዋና አይለምድም››እንደሚባለው አስተሳሰባቸው ምን ጊዜም ጭቃ ነው፡፡

ምንጮች፡

  1.   http://blog.indexoncensorship.org/2013/02/25/london-libel-ruling-against-ethiopian-dissident-shows-urgent-need-for-reform/
  2.   http://www.5rb.com/case/Al-Amoudi-v-Kifle-and-Another 
  3.   http://www.theguardian.com/law/2013/mar/05/defamation-bill-leveson-clause
  4.   http://www.onebrickcourt.com/files/cases/amoudi_92547.pdf 
  5.  http://www.ethiotube.net/video/17206/Elias-Kifles-Plea-with-Eritrean-Govt-For-Funds-To-Blow-up-Factories--Infrastructures-in-Ethiopia 

3 comments:

  1. እኔም የሚገርመኝ ለኢትዮጵያ አሳቢ እንደሆኑ ኢትዮጵያ በመጥፎ የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እየወደቀች መሆኑን ይናገራሉ ታዲያ ወደ ተለያዩ አገራት ኢምባሲ እየሄዱ ማዕቀብ እንዲጣልና የአገሪቱ ዜጎች በረሃብ እንድንሞት የሚራራጡት ለምን እንደሆነ አልገባኝም፡፡
    ለነገሩ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስለራሳቸው ብቻ ተቃዋሚ ነን ባዮችም ያው ለውጥ የላቸውም ቀጣይ ስለሚፈልጉት ሥልጣን ብቻ ነው ሐሳባቸው ሆዳሞች

    ReplyDelete
  2. እኔም የሚገርመኝ ለኢትዮጵያ አሳቢ እንደሆኑ ኢትዮጵያ በመጥፎ የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እየወደቀች መሆኑን ይናገራሉ ታዲያ ወደ ተለያዩ አገራት ኢምባሲ እየሄዱ ማዕቀብ እንዲጣልና የአገሪቱ ዜጎች በረሃብ እንድንሞት የሚራራጡት ለምን እንደሆነ አልገባኝም፡፡
    ለነገሩ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስለራሳቸው ብቻ ተቃዋሚ ነን ባዮችም ያው ለውጥ የላቸውም ቀጣይ ስለሚፈልጉት ሥልጣን ብቻ ነው ሐሳባቸው ሆዳሞች

    ReplyDelete
  3. I like your logical and coherent argument. Keep the good job Asfaw arkey.

    ReplyDelete