Tuesday, September 17, 2013

‹‹ለውጥ የምናመጣው ስልጣን ስንይዝ ነው›› አበርሃ ደስታ




በቅርቡ ነው የዓረና ትግራይ ፓርቲ የማእከላይ ኮምቴና የስራ አስፈፃሚ አባል ሆኖ የተሸመው፤ አብርሃ ደስታ፡፡ከሎሚ መፅሔት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰኑ ጥያቄዎች ቀርበውለት ወሳኝ የሆኑ ማብራርያዎችን ሰጥቷል፡፡ከነዝያ ጥያቄዎች አንዱ - አሁን የአረና አባል ሆነሃል፤ በፓርቲው ውስጥ ያለህ ተሳትፎ ምን ይመስላል? የአረና ጥንካሬና ድክመትስ ምንድነው? በትግራይ የምታካሂዱት እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
አብርሃ ደስታ የመጀመርያው ጥያቄ(በፓርቲው ውስጥ ያለህ ተሳትፎ ምን ይመስላል?) አልመለሰውም፡፡የሎሚው ጋዜጠኛ ሊያስታውሰው ይገባ ነበር፡፡የዓረና እንቅስቃሴዎችና ፈተናዎች ሲያብራራ ግን ‹‹ፓርቲያችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለውጥ ማምጣት ይፈልጋል። ለውጥ የምናመጣው ስልጣን ስንይዝ ነው።›› ብሏል፡፡ይህ አባባል አዲስ አይደለም፤ ሃገራችን ተቃዋሚዎች በእጅጉ  የሚተቹበትና ኢህአዴግም የህዝብ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚጠቀምበት አውራው ድክመታቸው ይመስለኛል፡፡ አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች የአማራጭ ፖሊሲያችሁ ምንድነው ሲባሉ ‹‹ስለ ፖሊሲው አሁን አንጨነቅበትም፤ ስልጣን ከያዝን በኋላ ከህዝቡ ጋር በመወያየት እናዘጋጀዋለን›› የሚል መልስ ይሰጣሉ፡፡ይህ ታድያ ‹‹ራስ ሳይጠና ጉተና›› አያስብልም? ህዝቡስ ምን አይቶ ነው ሃገርን የማስተዳደር ያህል ስልጣን ሊሰጣቸው የሚችለው?
የኢትዮጵያ ህዝብ ከፖለቲከኞች የሚጠብቀው ቃል መግባት ብቻ አይመስለኝም፡፡ቃል በመግባትማ ኢህአዴግን የሚያስከነዳ አይኖርም፡፡ ህወሓት ቃል በመግባት አንደኛ ነው፡፡የቀድሞ ጠቅላይ ምኒስትራችን 20 ዓመታት በፊት ነበር ‹‹ከ10 ዓመት በኋላ ሁላችሁም በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ›› ብለው ቃል የገቡልን፤ቃሉ ግን 10 ዓመት በኋላ ይቅርና ሁለት ዓስርት ዓመታት ጠብቀንም ቢሆን እውን አልሆነም፡፡ዛሬም ድረስ አብዛኛው ህዝባችን ከእርዳታ ጥገኝነት አልተላቀቀም፡፡
እውነቱን አንነጋገር ከተባለ ሃገርን ያክል ለማስተዳደር ብቁ ንኝ የሚል ፓርቲ ይቅርና ግለ ሰብም ቢሆን ‹‹ለውጥ የምናመጣው ስልጣን ስንይዝ ነው›› ብሎ ቃል መግባት በጣም ቀላል ነው፡፡ፖለቲከኞች ቃል ለመግባት ሲቸገሩ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም፡፡ዋናው ችግራቸው የገቡትን ቃል አክብረው መገኘቱ ላይ ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ ቃላቸው ባለመጠበቃቸውም ቢሆን በይፋ ይቅርታ ጠይቀው አለማወቃቸው ነው፤ ለማንኛውም ጉዳይ ተልካሻ ምክንያት አይጠፋምና ‹‹የናቴ ቀሚስ አስናከለኝ›› የመሳሰሉ አሰልቺ ሰበቦች ይደረድራሉ፡፡ከዓመታት በፊት የገቡት ቃል እየደጋገሙ ህዝቡን በተስፋ ቁንጣን ያሰቃዩታል፡፡
አብዛኞቹ የዓረና መስራቾችና አባላት ከህወሓት ጋር በነበሩበት ግዜ ትላልቅ ባለስልጣናት ነበሩ፡፡እንደ ፖለቲከኞችም ቃል ገብተውልን ነበር፤ ግን እነሱም ቃላቸውን አጥፈዋል፡፡ህወሓት እያሉ የህዝብ እምነት በልተዋል፡፡አሁን በዓረና ትግራይ ስም ቢመጡም ማንነታቸው በድምብ እናውቀዋለን፡፡እንዳውም እንሱ በስልጣን ላይ እያሉ የአሁኑ ያህል እድገት አልነበረም፡፡
ስለዚህ ከዓረና ትግራይ የምንጠብቀው ስልጣን ከያዙ በኋላ ለውጥ እንዲያመጡልን ሳይሆን ከወዲሁ የለውጥ ሃወርያት መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩን ነው፡፡ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ በማፅዳትና ነፃና ግልፅ የኖነ የስልጣን ተዋረድ መቅረፅ አለባቸው፡፡የህወሓቶች ፖሊሲ የሚያስከነዳ ፖሊሲ እንዳላቸውም በተግባር ሊያሳዩን ይገባል፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ የህዝብ ሮሮ ማዳመጥ የሚችል ጀሮ እንዲኖራቸው እንሻለን፡፡በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠሩ የትግራይ ክፍሎች በመዘዋወርም የህዝቡ የልብ ትርታ ተገንዝበው ለመፍትሔው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡


1 comment: