Sunday, September 15, 2013

ርእዮት አለሙ ሞልቃቃዋ የህግ ታራሚ



የፌስቡክ ወረኞች ነውጠኛዋ የህግ ታራሚ ርእዮት አለሙ ‹‹ምግብ ለምኔ›› እያለች መሞላቀቅ ከጀመረች አምስት ቀን ሆኗታል እያሉ ነው፡፡እኔ ምለው፤ ልጅቷ ምን ያህል ሞለቃቃ ብትሆን ነው ወንጀለኛ መሆኗን በፍርድ ቤት ተረጋግጦባት እስር ቤት ከገባች በኋላም ይህን ያህል ይምትበሻቀጠው? እሺ፤ ሞልቃቃዋ ልጅ በእስር ቤት ይህን ያህል ከተሞላቀቀች ከመታሰሯ በፊትስ ምን ያህል ሞልቃቃ ነበረች ማለት ነው? ለካ ጋዜጠኛ ተብየዋ ርእዮት ‹‹እምቦቆቅላ ሚጣ›› ነበረች፡፡የሚጣ ነገር! ለዛም ነበር ለካ ሃገርን በማሽሸበር መንግስትን ‹‹በቃ!›› እንበለው ብለው ቢመክሯት ግራ ቀኝ ሳትል እሳቱ ውስጥ ዝው ብላ የገባችው? ምስኪን ሚጣ፡፡
የርእዮት ሚጣነት ግልፅ የሚሆንልን ለምን እንደታሰረች ስናውቅ ነው፡፡መሃመድ ቡዓዚዝ የሚባል ቱንዚያዊ ወጣት ፖሊሶች አላሰራ ብለውኛል በሚል ሰበብ በራሱ ላይ ጋዝ ከርከፈከፈ በኋላ ክርቢት ጭሮ ራሱን በእሳት አጋየ፡፡ በዚህ የተቆጡ ቱንዝያውያንም ወደ አደባባይ ግልብጥ ብላ ወጡና የቤን ዓሊ አገዛዝን አፉ አሉት፡፡ የቱንዝያውያኑ ‹‹ህዝባዊ ዓመፅ›› ግብፃውያን ተቀብለው አስተጋቡት፤ታሕሪር አደባባይ የዓመፅ ምሽግ አደረጉት፤በመጨረሻም የሙባረክ አገዛዝ እጁን ሰጠ፡፡የኸው ዓመፅ የርዳኖስ፣ሊባኖስ፣ሳውዲ ዓረብያ፣ሊብያ እያለ ሲቀጥል ‹‹የዓረብ ፀደይ›› የሚባል የደቦ ስም የሰጡ ፡፡
ህፃናት በተፈጥሯቸው ሌሎች የሚያደርጉትን ለማድረግና የያዙትም ለመያዝ ያምራቿል፡፡ነገርየው በቀላሉ ከተገኘ እሰየው ነው፤ ካልሆነ ግን እሪ ብለው ያለቅሳሉ፤ የቻሉትን ያህል ያምፃሉ፡፡ህፃናት የፈለጉትን ካላገኙ አልያም ካልተቆነጠጡ በቀር አመፁን ይቀጥሉበታል፡፡የጋዜጠኞች ተብየዎቹ እነ ውብሸት ታየ፣ርእዮት አለሙ፣እስክንድር ነጋና ሌሎች ጮርቃዎች ዓመፅ ታድያ ዓረቦች ያደረጉትን በኢትዮጵያ መድረግ አለብን ከሚል ሚጣነት የመነጨ ነበር፡፡መንግስት ‹‹ተው›› ሲላቸው አሻፈረኝ በማለት ገፉበት፤ ‹‹የተሌኮሚኬሽንና የመብራት ገመዶች›› እየበጣጠስን የኢትዮጵያውያን ‹‹ህዝባዊ ዓመፅ›› ካላነሳሳን ሞተን እንገኛለን ሆነ አቋማቸው፡፡ግብፃውያን በታሕሪር አደባባይ መሽገው ሙባረክን ‹‹በቃህ!›› ብለው መሸኘት ከቻሉ ‹‹እኛስ መስቀል አደባባይ በመመሸግ ኢህአዴግን በቃ! ለማለት በምን እናንሳለን?›› ተባብለው እርሰ በርስ ተጠያየቁ፤እናም ‹‹እንችላለን›› ሆነ ውሳኔቸው፡፡
የጋራ ውሳኔቸው ከግቡ ለማድረስም በፌስቡክና በትዊተር ‹‹በቃ!›› እያሉ ማላዘን ጀመሩ፤ ዘመቻ ‹‹በቃ!›› ተጧጧፈ፡፡ ዘመቻው ግን ከማህበራዊ ድረ ገፆች ወደ መስቀል አደባባይ በመንደርደር ላይ እያለ በድህንነት ሃይሎች ‹‹በቃ!›› ተባለ፡፡ የእነ ርእዮት የ‹‹እቃ እቃ›› ጫወታም ማዳረሻው ቃልቲ ሆነ፡፡እነዚህ ልጆች ቃልቲ ከወረዱ በኋላ ግራ ሳይጋቡ አልቀሩም፡፡ ምክንያቱም ፍርድ ቤት ህግ ጥሳችኋል፤ ወንጀለኞች ናችሁና መታሰር አለባችሁ ብሎ ሲወስን ‹‹የጋዜጠኞች ተቆርቋሪዎች ነን›› ባዮቹ ‹‹ዓለም አቀፍ ተቋሞች›› ደግሞ ‹‹ጀግኖች ናችሁ፤ ለሰራችሁት ጀብድም የኸውና ሸለምናችሁ›› አሏቸው፡፡እናም እነ ሚጣም እውነት መስሎቸው በማረምያ ቤት ሆነውም መሞላቀቁን ገፉበት፡፡የቃልቲ ማረምያ አሁንም የነሚጣ ‹‹የዓመፅ አደባባይ›› መሆኑን ቀጥለዋል፤ ከወራት በፊት የማርምያ ቤት ጥበቃዎችን ያስፈራሩ እንደነበር ሰምተናል፡፡አሁን ደግሞ ‹‹ከኮለኔል ሃይማኖት ጋር አልታሰርም፤ልትገድለኝ እየዘተች ነው›› ስትል ከመክሰሷም በላይ ‹‹ምግብ ብበላ ሞቸ እገኛለሁ›› እያለች ነው ይባላል፡፡ግን እኮ ያበዛችው አይመስላችሁም?‹‹ለልጅ ከሳቁለት፣ ለውሻ ከሮጡለት መልስ የለውም›› አሉ አበው፡፡
ቆይ ግን፤ ተቃዋሚዎች (የኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ጠላቶች ብላቸው ይሻላል)‹‹ኢህአዴግ ከደርግ የባሰ አምባገነን ነው›› በማለት በተደጋጋሚ ይከሳሉ፤በደርግ እስር ቤትም የምግብ ማቆም አድማ ነበር ማለት ነው? የደርግ ዳኞች እነማን ነበሩ? እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አልነበሩም? እነዚህ ሰዎች ‹‹ኢህአዴግ ከኛ ይሻላል›› ብለው ለመናገር ድፍረት እንደማይኖራቸው ይተወቃል፡፡ የነዝያ ነፍሰ በሎች ተማሪዎችስ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ያለ የሌለውን እየለቃቀሙ ታርጋ ከመለጠፍ ውጪ ምንም፡፡ እስኪ በሞቴ ፎቶውን ተመልከቱልኝ! ጋዜጠኛ ተብየዋ ርእዮት አለሙ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር እንዴት እንደተጣበቀች አያችሁልኝ? በርሳቸው ሳምባ የምትተነፍስ እኮ ነው የሚመስለው፡፡ቀኝ እጇን ተመልከቱት! የልብ ትርታቸውን እየለካች ነው? ‹‹ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ተምራመጣች›› አለ ያገሬ ሰው፡፡ከዚሁ እድሜ ልኩን ሃገር ሲያፋጅ የኖረው ሽማግሌ ጋር እንዲሁ የተጣበቀች ሚጣ ለጊዜው ምግብ አልበላም ብትል ምኑን ይደንቃል?
የተቃዋሚዎች ፍርደ ገምድል ውሳኔዎች
የሃገራችን ተቃዋሚዎችን ሳስብ ሁሌም ግርም ይለኛል፡፡አንዱ የሆነ ነገር ካለ ሁሉም እንደ በቀቀን ያስተጋቡታል፡፡ልክ እንደ ውሻ አንዱ ማላዘን በጀመረ ቁጥር ሁሉንም እየተቀባበሉ ያላዝናሉ፡፡የሚገርመው ደግሞ ፍርደ ገምድልነታቸው! ስንት በርባኖች እንዲፈቱላቸው ነው የሚፈልጉት? ‹‹ብርቱካን ትፈታ! ትፈታ!...ትፈታ!...ትፈታ!››፤ ‹‹ርእዮት ትፈታ! ትፈታ!ትፈታ!ትፈታ!››፤‹‹እስክንድር የፈታ! የፈታ! የፈታ!የፈታ! የፈታ!››፤ ‹‹የአወልያ ኮምቴዎች ይፈቱ! ይፈቱ!ይፈቱ!ይፈቱ!›› ወዘተ፡፡ብቻ አንዱ ማለዘን ይጀምር ማስተጋባት ነው፤ማሰብ ማሰላሰል የለም!  እነዚህ ናቸው የበቀቀኖቹ ጭሆቶች፤ ማን ምን እያለ ነው የሚለው ጥያቄ ግዳቸው አይደለም፡፡ብቻ ሁሉንም በርባኖች መፈታት አለባቸውን የነሱ ማላዘን፡፡ቆይ ግን፤ በበርባኖች ምትክ ማን እንዲ ሰቀልላቸው ነው የሚፈልጉት? እነዚህ በርባኖች እኮ የህዝብ ድህንነት አደጋ ውስጥ ለመክተት ሲዶልቱ ተደርሶባቸው ነው የታሰሩት፡፡ታድያ እነሱ ተፈትተው ህዝቡ እንዲ ሰቀልላቸው ነው ይህ ሁሉ ጭሆት? አሁን ማ በጣም አበዙት፤ ከልክ በላይ ቀበጡ፡፡ ስለዚህ ‹‹በቃ!›› ማለት ያለባቸው እነሱ ናቸው፡፡ ካልሆነ ግን በፊልሞች የተመለከቷቸውንና በውጭ ሃገራት የታዘቧቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ወደ ሃገራችን ካለስገባን፤አስገብተንም ካልሞከርን እያሉ አሻፈረኝ ማለታቸውን ማቆምያ የሚኖረው አይመስለኝም፡፡
ምክንያቱም አያያዛቸው አያምርም፡፡ የእነሱ ሃሳብ የተቃወመ ሁሉ እንደ ጠላት ይቆጥሩታል፤ ፍርዳቸውም አንድና አንድ ነው፤‹‹ይሰቀል! ይሰቀል!ይሰቀል!ይሰቀል!›› በቃ! ልክ እንደ ቁራ በጋራ መጮህ፡፡በእነሱ ሳምባ የማይተነፍስ ሁሉ ጠላት ነው፡፡አይሁዶች ‹‹በርባንን ፍታልን፤ እየሱስን ስቀልልን›› በማለት ጲላጦስን እንደ ጮሁበት ሁሉም በርባኖች እንዲፈቱላቸው የፈልጋሉ፡፡አዎ! የኢትዮጵያ ጲላጦስም እየሱሶችን ሰቅሎ በርባኖችን ነፃ ካላወጣ በስተቀር አምባገነን ነው፡፡እንሱ ያሉት ካላደረገ ‹‹የቄሳር ወዳጅ›› አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ ከአይሁዶችና ከጲላጦሶች ነፃ የምትወጣው መቸ ይሆን? የኢትዮጵያ ህግስ መቸ ይሆን ኢየሱሶችን በፃ አሰናብቶ በርባኖችን የሚሰቅለው?



No comments:

Post a Comment