ሕዳር 8፣ 2003 ዓ.ም፣ የ26 ዓመቱ ቱንዚያዊ ወጣት ሞሃመድ ቧዓዚዝ በራሱ ላይ
ጋዝ በማርከፍከፍና ክርቢት በመለኮስ ራሱን አቃጠለ፡፡ለምን?ታሪኩ ብዙና አሳዛኝም ነው፡፡በአጭሩ ግን አንድ ቱንዚያዊት የፖሊስ አዛዥ
ሽንኩርትና ሌሎች ፍራፍሬዎችን እየመዘነ የሚሸጥበት ሚዛንና ነግዶ ለማትረፍ 200 ዶላር ከሰው ተበድሮ የገዛው እቃ ስለዘረፈችው፤
አንጀቱ ተቃጠለ፤ ‹‹ ምንግስት ስራ ሊሰጠኝ አልቻለም፤ ራሴ የፈጠርኩት ስራም አላሰራ አለኝ፤ ታድያ እንዴት መኖር እችላለሁ?››
አለና ዓለም ጉድ ባሰኘ መንገድ ራሱን አሰቃይቶ ገደለ፡፡ከ18 ቀናት ቡኋላ ቧዓዚዝ ማረፉን ተሰማ፡፡የቱንዚ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ለዓመፅ
ተነሳ፤እሳት ጎርሶ እሳት እየተፋ የቤን ዓሊ የ23 ዓመታት አገዛዝ ገረሰሰው፡፡
ህዝባዊ ዓመፁ ግን በቱንዚያ አልተገታም፡፡ማዕበሉ ወደ ግብፅ ተሸጋገረና የሁሰኒ
ሙባረክ አገዛዝም ጠራርጎ ወሰደው፡፡የሙዓመር ጋዳፊ ከብረት የጠነከረ ስልጣን ለመጀመርያ ግዜ በዓማፂዎች ተፈተነ፡፡ጋዳፊ ግን
‹‹ትናንሽ አይጦች ሆይ አርፋችሁ ተቀመጡ፤እግርና እጃችሁ እንዳትቆረጡ›› ሲሉ ዛቱባቸው፡፡አሜሪካ፣ኢንግሊዝና ፈረንሳይ ይህንኑ አጋጣሚ
ሲጠብቁ ነበረና ‹‹በሰበቡ መምሬ ተሳቡ›› ሆኖ ጋዳፊን በተደበቁበት ቱቦ ውስጥ ተኩሰው አቆሰሏቸው፡፡ታላቁ ጋዳፊ፣ማንአህሎኝ ባዩ
ጋዳፊ፣የአፍሪካ ንጉስ ለመሆን ሌት ተቀን ሲያልሙና ሲለፉ የኖሩ ጋዳፊ ‹‹ማሩኝ! አትተኩሱብኝ! አትተኩሱብኝ›› እያሉ ቢማፀኑም
‹‹ብንምርህ አይማረን›› አሉና ገደሏቸው፡፡ሬሳቸውም በአደባባይ ዘርግተው ለህዝብ እይታ ክፍት አደረጉት፡፡
ምዕራባውያን ‹‹የዓረብ ፀደይ›› ብለው የሰየሙት ህዝባዊ ዓመፅ እንደስያሜው ህዝባዊ
አልነበረም፤የለየለት የእርሰበር መጨፋጨፍ እንጂ፡፡የብዙ ንፁኃን ዓረቦች ደም እንደ ጅረት የፈሰሰበት ብጥብጥ አሮጌ ስርዓቶችን ቢያስወግድም
የታለመው ሰላምና ዲሞክራሲ ግን እንደጉም በነነ፡፡ቱንዚያውያን ዛሬም ሰላም አላገኙም፤ ስልጣናቸው በአክራሪ ሃይሎች ተነጥቀዋል፤አሁንም
እርሰ በርስ በመገዳደል ላይ ይገኛሉ፡፡በልብያ ሰላም የለም፡፡የግብፂ ነገርም መላቅጡ የጠፋበት ልቃቂት ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሊቶች ነን ባዮች የዓረቡ ፀደይ በመኮረጅ መስቀል አደባባይን እንደ
ታሕሪር አደባባ በህዝባዊ አመፀኞች ለማጥለቅለቅ ዛቱ፡፡ዝተውም አልቀሩም፤ በፌስቡክ፣በትዊተርና ሌሎች ማህበራዊ ድረ ገፆች የ‹‹በቃ!››
ዘመቻ አዘጋጁ፡፡ በቃ! በድህንነት ሃይሎች በቃ ተባሉና ከያሉበት ተለቃቅመው ቃልቲ ታጎሩ፡፡መሪዎቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ የበቃ ዘማቾች
አንድም ሃገር ጥለው ኮበለሉ አልያም ከያሉበት ተሰባስበው ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የሚባል ሌላ ዘመቻ ከፈቱ፡፡ነገር ግን የግብፆች ዓመፅ
በእስላማዊ አክራሪዎቹ ሞስሊም ወንድማማቾች እንደተጠለፈው የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ዘመቻም በዋህቢስቶችና ሳላፊስቶች ተጠምዝዞ ከፌስቡክ
ወደ መስጊዶች ተዛመተ፡፡
የሄኛው ዘመቻ ግን ልክ እንደ ‹‹በቃ!›› ስሩ ኢትዮጵያ ስላልሆነ ከማስፈራራት
ወደ ማጥቃት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡በደሴ አንድ ታላቅ ሃይማኖታዊ መሪ በጥይት ተደብድበው ተገድሏል፤ ሼህ ኑር
ሁሴን፡፡የኢቲቪ ዜና አንባቢው ተመስገን
ዘገየም ኩፍኛ ተደብድቦ፤ ትቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኝተዋል፡፡እኔን ጨምሮ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ዘመቻን የተቃወመና ለመቃወም ያሰበ
ሁሉ ብዙ ማስፈራርያዎችና ዛቻዎች እየደረስባቸው ነው፡፡ ጦማሪው ዳኒኤል ብርሃነ ከአንድ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወዶ ዘማች ‹‹እገድልሃለሁ!
ወላሂ አልምርህም›› የሚል ዛቻ ደርሶበታል፡፡
የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ዘማቾች ቁጥር የሚናቅ አይደለም፤ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ከፌስቡክ
በፍለጋ ካሰባስብኳቸው ብዱኖች
ስምንቱ እያንዳንዳቸው ከ7ሺህ በላይ ሰዎች ወዷቸዋል፡፡
1.
- ድምፃችን ይሰማ :ይህ ብዱን መረጃው በተጠናቀረበት ወቅት 58, 772 ሰዎች ወደውታል(like አድርገውታል)፡፡
- ድምፃችን ይሰማ- Dimtsachin Yisema: ይህኛው ብዱን
የመጠባበቅያ ሲሆን 26, 392 ሰዎች ወደውታል፡፡ - ድምፃችን ይሰማ (Demtsachen yesema):
ይህኛው ብዱን ዝግ(closed group) ነው፡፡ 10, 713 አባላት ያሉት ሲሆን 4 ዋና
ዋና ዓላማዎች ዘርዝረዋል፡፡ከነዚህ አንዱ ‹‹ በጦርነት ሳይሆን በተማረ አስተሳሰብ ሃገራችንን የኢስላም ደሴት እናደርጋታለን››ይላል፡፡የድምፃችን
ይሰማ ዓላማ በግልፅ ያስቀመጠና ‹‹ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ናት›› የሚሉትን የሚፎካከር መሆኑን ነው፡፡ ግን ‹‹ በጦርነት ሳይሆን በተማረ አስተሳሰብ››ማለት ምን ማለት ነው?የተለያዩ እምነቶች የሚከተል ህዝብ ለዘመናት የኖረባት ሃገር ‹‹የኢስላም ደሴት›› ለማድረግ ያለመው ‹‹የተማረ አስተሳሰብ›› ምን ዓይነቱ ነው? እኔ እስከማውቀው ድረስ የተማረ አስተሳሰብ የሚባለው ሰዎች የፈለጉት እምነትና አስተሳሰብ በነፃነት እንዲያራምዱ የሚፈቅድ ነው እንጂ ሃገር ሙሉ ‹‹የኢስላም ደሴት›› ወይም ‹‹የክርስትና ደሴት›› ለማድረግማ የተማረ አስተሳሰብ አያስፈልግም፡፡ወይስ ሌሎች እንዳይማሩና የፖለቲካና የኢኮነሚ ጥገኞች እንዲሆኑ በማድረግ በህይወት ለመቆየት ሲሉ እምነታቸው እንዲቀይሩ ነው ‹‹የተማረ አስተሳሰብ›› ያስፈለገው?አዎ! አሁን ያለው እውነታ የሄው ነው፡፡ አንደኛው የሃገሪትዋ የልማት ግንባት በማኮላሸትና እንዳትበለፅግ ማድረግ፡፡ከዛም የዓረብ ሃገሮች ምድራዊ ገነትነት በመስበክ የሃገሪትዋ ወጣቶች ሃገራቸውን ጥለው ወደ ዓረቦች እንዲሰደዱ ለማሳመን ህገወጥ ደላሎች ማሰማራት፡፡ከዛም እነዛ ሰርተን ያልፍልናል በሚል ተስፋ ወደ ዓረብ ሃገሮች በገፍ የሚጉዋዙ ዜጎች እንምነታቸው እንዲቀይሩ ማስገደድ፤ ካልሆነም በኤሌትሪክ እያቃጠሉና እየደበደቡ ማሰቃየት ብሎም ከፎቆች ቁልቁል በመወርወር መግደል፡፡ይሄው ነው ‹‹የተማረው አስተሳስብ›› ወይስ ሌላ?ሁለተኛው ደግሞ በማንኛውም መንገድ የሃገሪትዋ ኢኮነሚያዊና ፖለቲካዊ ስልጣን መቆጣጠር፤ ከዛም በሸሪዓ ህግ የሚመራ እስላማዊ መንግስት ማቋቋም፡፡የእስላማዊ መንግስት ዓለማ ደግሞ ለማንም ግልፅ ነው፤ሳይንሳዊ አስተሳሰቦችና እውነቶች በመደፍጠጥ እስላማዊ ርእዮተ ዓለሞች ብቻ ማራመድ፡፡የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳቦች እንዳገደው የታሊባን የትምህርት ፖሊሲ ማለት ነው፡፡
- ድምፃችን ይሰማ ከሳዑዲ አረቢያ: መነሻው ሳውዲ ዓረብያ ሲሆን 10, 563 ሰዎች ወደውታል፡፡
- ድምፃችን ይሰማ - Let Our Voice be Heard : 8, 131 ሰዎች ወደውታል፡፡
- ድምፃችን ይሰማ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ: መነሻው ከደቡብ አፍሪካ ሲሆን 7, 669 ሰዎች ወደውታል፡፡
- ድምፃችን ይሰማ !Ethiopian Muslim University students: ይህ ብዱን ልዩ የሚያደርገው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚገኙበት በመሆኑ
ሲሆን 7 385 ሰዎች ወደውታል፡፡
8 . ድምፃችን ይሰማ በአዳማ:
መነሻው ናዘሬት ወይም አዳማ ሲሆን 7 323 ሰዎች ወደውታል፡፡
ዋቢ ድረ ገፆች
No comments:
Post a Comment