በመፅሐፍ ቅዱስ ትርክት መሰረት አዳምና ሄዋን ከገነት የተባረሩት የፈጣሪ ትእዛዝ በመተላለፋቸው ነው፡፡ትእዛዙ ምን
ነበር? ‹‹በገነት ካሉ ዛፎች ሁሉ መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ክፉና ደጉን ከምታሳውቀው ዕፀ በለስ ከበላችሁ የሞት ሞት ትሞታላችሁ››
ይላል ትእዛዙ፡፡አዳምና ሄዋን ይህ ትእዛዝ አክብረው ለዘመናት በሰላም ይኖሩ ነበር፡፡
ኋላ ግን በእባብ አሳሳችነት ዕፀ በለሷን በሉና ክፉና ደጉን አወቁ፤ ከገነትም ተባረሩ፡፡ እዚህ ጋ አንድ ጥያቄ እንጠይቅ፤
አዳምና ሄዋን በእባብ ተንኮል ለምን ተታለሉ? መልሱ ቀላል ነው፤ አዳምና ሄዋን ክፉና ደጉን አላወቁም ነበር፡፡ክፉና ደጉን ባለማወቃቸውም
ከገነት ስለመባረርና የሞት ሞት ስለመሞት አላስጨነቃቸውም፡፡ እንዳውም እባቡ‹‹የሞት ሞት አትሞቱም፤ ይልቅ ዕፀ በለሱን በበላችሁ
ጊዜ ዓይናችሁ ይበራል፤ ክፉና ደጉም ታውቃላችሁ››ብሎ ሲመክራቸው በደስታ ነበር የተቀበሉት፡፡
ያየመፅሐፍ ቅዱስ ፈጣሪ ግን ልክ እንደዛሬው ህግ አውጪዎች ስለነበር‹‹ ህግን አለማወቅ ከተጠያቄነት አያድንም››
በሚለው መሰረተ ሃሳብ አማካኝነት ቅጣቱን አወረደባቸው፡፡ስህተት ምን እንደሆነ ባያውቁም ‹‹እባብ አሳሳተኝና ዕፀ በለሱን በላሁ››
ብሎ ነገር ከገነት ከመባረርና የሞት ሞት ከመሞት አላዳናቸውም፡፡የመፅሐፍ ቅዱሱ የዓለም ፈጣሪ ሁሉም ቻይ ስለሆነ አዳምና ሄዋን
ዕፀ በለሱን በልተው ክፉና ደጉን ማወቅ ቢችሉም ከማወቅ ወደ አለማወቅ መመለስ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን በጣም ቀላሉና የማያዳግም
ውሳኔ ነበር የወሰነው፤ ዕፀ በለሷን ድጋሚ ወደማያገኙበት ማባረር፡፡
ክብረ ነገስትና መፅሓፍ ቅዱስ ‹‹የነገስታት ሽዋሚና ሻሪ አንደየ ነው›› ይላሉ፡፡ስለሆነም ገዢዎቻችን ከአንዴ በቀሰሙት
ልምድ መሰረት ህዝባቸውን ይገዛሉ፡፡ብዙ ዕፀ በለሶችን ከተገዢው ህዝባቸው እይታ ውጪ ያደርጋሉ፡፡አያስፈልጉም ያሉዋቸውን ጋዜጦች፣
መፂሔቶችና ድረ ገፆችን ይዘጋሉ፤ይደብቃሉ፡፡ምክንያቱም ገዢዎቻችን ክፉና ደጉን እንድናውቅና ዓይናችን እንዲበራ አይፈልጉም፡፡የእኛ
ንሮ በገነትም ይሁን በገሃንም በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አይፈልጉም፤ እንደ እንስሳት በደመንፍስ እንድንመራ ነው የሚፈልጉን፡፡
በሃገራችን ኢትዮጵያም ከዚህ የተለየ አስተዳደር የለም፡፡ብዙ መፂሔቶች፣ጋዜጦችና ድረ ገፆች እየተዘጉ ነው፡፡ከነዚህ
አንዱ የዓረና ትግራይ ድረ ገፅ(http://www.arena-tigray.org/) ይገኝበትል፡፡አብርሃ ደስታ
የዓረና ድረ ገፅ ትግራይ ውስጥ መዘጋቱን እየተናገረ ነው፡፡ነገር ግን ትግራይ ብቻ አይደለም የማይሰራው፤ እዚሁ አዲስ አበባም መክፈት
አይቻልም፡፡
ዓረና ፓርቲ የህግ እውቅና ተሰጥቶት ህገ መንግስቱን ሳይጋፋ ለዴሞክራሲ ግንባት የቻለውን ያህል አሰራ ያለ ፖለቲካዊ ድርጅ ነው፡፡የፓርቲው አቋም የምናውቀው ደግሞ የርሱ ልሳን በሆነው ድረ ገፁ ነው፡፡መንግስታችን ግን እንደ ዕፀ በለስ ቆጥሮት ከእኛ እይታ ውጪ አድርጎታል፡፡ይህ እርምጃ ግን ፍላጎታችን ከቁጥጥራችን ውጪ እንዲሆን በማድረግ ያንኑ ፍለጋ እንድንሰማራ ይገፋፋናል እንጂ ጥቅሙና ጉዳቱን አውቀን እንድንተወው ወይም እንጠቀምበት አያስችለንም፡፡
መንግስት የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ድረ ገፆች ብቻ አይደለም ‹‹እነዚህ ዕፀ በለሶችን ካያችሁ አይታችሁም ከበላችሁ
የሞት ሞት ትሞታላችሁ›› እያለን ያለው፡፡በቀጥታ የሚያስጠኑ ድረ ገፆች(online tutorials)፣የተለያዩ ዓይነት መፃሕፍትና
ኦድዮቪዥዋሎች ወዘተ በነፃ የምናወርድባቸውና ራሳችን እንድናሳድግ የምንጠቀምባቸው ድረ ገፆችም ተዘግተዋል፡፡
ህገ መንግስቱ ግን በአንቀፅ 29/2 ላይ ማንኛውም ዜጋ የሎሎች መብት እስካልተጋፋ
ድረስ መረጃ የማግኘት፣የመያዝና የማሰራጨት መብት እንዳለው በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ዓረና ፓርቲ የህግ እውቅና ተሰጥቶት ህገ መንግስቱን ሳይጋፋ ለዴሞክራሲ ግንባት የቻለውን ያህል አሰራ ያለ ፖለቲካዊ ድርጅ ነው፡፡የፓርቲው አቋም የምናውቀው ደግሞ የርሱ ልሳን በሆነው ድረ ገፁ ነው፡፡መንግስታችን ግን እንደ ዕፀ በለስ ቆጥሮት ከእኛ እይታ ውጪ አድርጎታል፡፡ይህ እርምጃ ግን ፍላጎታችን ከቁጥጥራችን ውጪ እንዲሆን በማድረግ ያንኑ ፍለጋ እንድንሰማራ ይገፋፋናል እንጂ ጥቅሙና ጉዳቱን አውቀን እንድንተወው ወይም እንጠቀምበት አያስችለንም፡፡
ስለዚህ የዓረና ትግራይ ድረ ገፅ እንደ ዕፀ በለስ ተቆጥሮ መዘጋት የለበትም፡፡መንግስታችንስ ስንት ዕፀ በለሶችን
ደብቆ ይወጠዋል?
A statement from ESAT or EthiopianReview
ReplyDelete——————————————————–
A lion believed to be a well trained, anti-Ethiopian TPLF cadre, has deliberately killed an innocent Ethiopian in Addis Ababa. The lion is believed to have killed the man mainly because the man was not Tigrian. In fact, our source strongly believes the lion was motivated to kill the victim because he is a patriotic Amhara. Our source added that the TPLF hoodlum lion has committed the crime as part of a long term plan by the TPLF regime to cleanse Amhara guards from the historical zoo founded by His Highness the late Emperor Haileselassie.