Friday, September 20, 2013

‹‹እኛ (እኔና ጓደኞቼ) ወደ ዓረና አልገባንም፤ ዓረና ለኛ ተሰጠ እንጂ!›› አበርሃ ደስታ



የሚከተለው አጭር ፅሑፍ ከማንበብህ በፊት ግን የዓረና ከፍተኛ ባለስልጣን የአብርሃ ደስታ ‹‹እኔና ዓረና ፓርቲ›› የሚባል አርእስት ሰጥቶ በፌስቡክ ገፁ ላይ ፅሑፍ አንብብ፤‹ሊንኩ› ላይ በመጫን፡፡




ስማ! ይህ ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሃል? አብርሃ ደስታን ታውቀዋለህ፤ በጣም ታውቀዋለህ፡፡ግን የት ነው የምታውቀው? ‹‹በሃገረ ፌስቡክ››  ብለህ እንደምትመልስልኝ አልጠራጠርም፡፡አንተ ከተጠራጠርክ ግን አብርሃ ደስታ ከሌላው ዓለም በላይ በጣም የሚታወቀው በፌስቡክ መሆኑን ልንገርህ፡፡
ይህ የፌስቡክ ታዋቂነቱም ዓረና የሚያክል ፓርቲ አሰጥቶታል፤ ከዛሬ ጀምሮ ዓረና ፓርቲ የአብርሃና ጓደኞቹ ስጦታ ነች፡፡‹‹ዓረና ለራሳችን ሰጡን›› የሚለውን መስመር ደግመህ አንብበው፡፡ልብ በል፤ አብርሃ የዓረና ከፍተኛ አመራር ሁኖ አልተመረጠም(ካላመንከኝ ለራሱ ጠይቀው)፡፡እስከዛው ድረስ ግን ‹‹ እኔ ወደ ዓረና አልገባሁም፡፡ዓረና ነው የተሰጠኝ›› የአብርሃ ፅሑፍ መሆኑን ላስታውስህ፡፡

አዎ፤ ‹‹የዓረና መሪዎች ለውጥ ፈለጉ፣ ዴሞክራሲ ፈለጉ፣ ወጣቶችን ተክተው ማለፍ ፈለጉ፣ ከህወሓት የተሻለ ለህዝብ ጥቅም የሚቆም ወጣት ሙሁራን የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅት መመስረት ፈለጉ።›› እናም አብርሃና ጓደኞቹ ‹‹ተደራጅተው›› ህዝብ ለመምራት ‹‹ዓረናን ለራሳቸው ለማድረግ ተቀበሉት›› እንዲህ ነው ለውጥ ማለት፡፡የዴሞክራሲ ለውጥ ካስፈለገ ስልጣን በምርጫ ሳይሆን በገፀ በረከት መልክ ‹‹ለተደራጁ ወጣት ምሁራን›› መሰጠት አለበት፡፡የዓረና መስራቾች ይህን ያህል ቸር ናቸው፤ ፓርቲ በሚያህል ስጦታ ያምበሸብሹኋል፡፡

አብርሃ ‹‹ከኛ ጋር በመሆን የህዝብ አጀንዳ ማስያዝ ይችላል።›› ብሎ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? እያልክ አትብሰልሰል፡፡ የዚህ ዓረፍተ ነገር ስም፡‹‹የህዝብ አጀንዳ ማስያዝ›› ሲሆን ወርቁ ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያን ለመግዛት ቁማር ስንጫወት የህዝብ ጥያቄ እናስያዛለን›› የሚለውን ነው፡፡በሌላ አባባል እነ አብርሃ ቁማር የሚጫወቱት በህዝቡ ህይወትና ንብረት ነው፡፡ ስለሆነም በቁማሩ ቢበሉም ቢበሉም(አንዱን ቃል መርጠህ ‹በሉ›ን አጥብቀህ አንብበው) አይከስሩም ማለት ነው፡፡

ለመሆኑ የአብርሃ ደስታ ‹‹ጓደኞች››(ካስፈለገህ Friends ማለት ትችላለህ) እነማን ናቸው? የፌስቡክ ጓደኞቹን ማለቱን ከሆነ ‹‹ሼም›› ነው፡፡እንዴ! ዓረና የፌስቡከሮች(እንዲህ ከሆነ እኔም የፌስቡክ ጓደኛው ነኝና ዓረና የኔም ጭምር ነች ማለት ነው) ፓርቲ አደረጋት ማለት እኮ ነው!ሰለዚህ ዓረና የአብርሃ ደስታና የፌስቡክ ጓደኞቹ መሆኗን እወቅ፡፡
 እናም ኢትዮጵያን የታክል ሃገር ፌስቡክ ሁነን ልናስተዳድር? አብርሃ ደስታ አታደርገውም!እባክህ አታድርገው፡፡አንተ ‹‹IT IS SO›› ብለህ  በመጨረሻ ላይ ሶስት የቃለ አጋኖ(!!!) ምልክቶች በማስቀመጥ ከወሰንክ ‹‹ቃሌ ከሚጠፋ ይህ ዓለም ይጥፋ›› ማለትህ አይቀርም፡፡እቺ የድርቅና መፈክርህ ‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም››ን ነው የምታስታውሰኝ፡፡

በመጨረሻም የሚከተሉት ጥያቄዎች እንዲመለሱልኝ እፈልጋለሁ፡፡

አብርሃ ደስታ አንተና ጓደኞችህ(ወጣት ምሁራን?) ወደ ዓረና አልገባችሁም፤ አረናግን ወደ እናንተ ገባች(ለእናንተ ተሰጠች፤ የዘመኑ ምርጥ ስጦታ!)፡፡ከጓደኞችህ ጋር ‹‹ተደራጅታችሁ›› ዓረናን ተረከባችሁ፡፡ቆይ ግን፣ ዓረና ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ነች እንዴ? ከሌሎች ፓርቲዎች የመቀላቀል ዕድል ብያጋጥማችሁ የዓረና ስም ሊቀየር እንደሚችልም ተናግረሃል፤ ከዛስ ምን ይዘህ ልትቀር ነው? በዓረናዎች ወጣት የሚባለው ከስንት ዓመት በታች ነው(ለኔም ከዓረና ትንሽ ቆርሳችሁ እንደትሰጡኝ ስለምፈልግ ነው፤ ወጣት ምሁር አይደለህም ካላላችሁኝ በስተቀር)? አዲስ ትውልድ የማትለው ‹‹አዲስ ትውልድ ብሎ ነገር የለም፤ቋንቋ ነው›› ብለህ ስለምታምን ነው?

No comments:

Post a Comment