Monday, September 16, 2013

ዳኒኤል ብርሃነ ውፍረቱ አሳስቦታል

Daniel Berhane: Ok, I admit I am overweight. Tell me what to do. I will do anything. I mean, anything except sport & diet.
(እሺ፤ ከልክ በላይ መወፈሬን አምኛለሁ፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሩኝ፡፡ስፖርት ስራ፤ አመጋገብህን ቀይር አትበሉኝ እንጂ ማንኛውም ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡፡)

መልስ፡



እኔ የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ስራም አልልህም የአመጋገብ ለውጥም ማድረግ ያለብህ አይመስለኝም፡፡ ችግርህ ከልክህ በላይ መወጣጠርህ ነው፡፡ ‹‹የምጡቅ አእምሮ ባለቤት ንኝ›› አልክ፤ ይሁንልህ ብለን ዝም አልን፡፡ምክንያቱም ከቅርብ ጊዜዲህ የኢቲቪ የዜና ደምሳሽ(ዳሳሽ አላክኩም)ና በታኝ(አሁንም ልብ እንበል ተንታኝ አልወጣኝም) ሁነሃልና ፡፡ ‹‹የኮምቢተር ባለሙያዎች ያስቸገረ (መስራት ያቃታቸው)የድረገፅ ንድፍ(ዲዛይን) እኔው በቀላሉ አስተካከልኩት›› አልክ፤ ታዝበን ዝም አልን፡፡የህግ ምሁራን ህጉን በትክክል ከመተረጎም አልፈው የፕሮግራመሮች ስራ በማቃልልና  ችግሮች ሲከሰቱም በመፍታት ላይ መሆናቸውን ስናውቅ ደስአለን(ደስታ ሕንጉሊጣ)፡፡ ‹‹ዓረና  የትግራይ ጠላት ነው›› አልክ፤ ‹‹ከአክራሪዎች የዋለች ካድሬ አክራሪነት ተምራ መጣች›› የሚባል የአበው አባባል አስታውሰን ጭጭ አልን፡፡ የባለ ሰይጣኖቻችን የቅርብ ጓደኛ መሆንህን ቦርጭህን  የዘጠኝ ወር እርጉዝ ፣ መላጣህም የዝንጀሮ ቂጥ አስመስለህ ተናገርክ(ፃፍክ)፤ እነሱ ታዛዥ መቼ ጠልተው ያውቃሉ? በለን ራሳችን ጠየቅን፡፡ እነዚህና ሌሎች ያልዘረዘርኳቸው እንደ ሽሮ የሚያንተገትጉ ውጥረቶች ሳይሆኑ አይቀሩም ‹‹ኦቨር ወይት›› ያደረጉህና ብትተዋቸው ይሻልል፡፡ መተው ካቃተህም ቀስ በቀስ ለመቀነስ ሞክር፡፡እውነቴን ነው! እኛ ካንተ ብዙ እንጠብቃለን፤ ካሁኑ ጀምረህ ‹‹ሩጫየን ጨርሻለሁ›› ብለህ በእርካታ የምትወፍር ከሆነ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡



 

  (ምኽሪ ውሓኻ ብደውኻ፤ ቆብ አብላ ሸው አብላ)

No comments:

Post a Comment