Monday, May 20, 2013

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 50 ደረሰ



የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ደሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው አቶ ገብረዋህደ ወለግወርጊስ ጭምሮ በሙስና ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር የዋሉት ተጠርጣቲዎች 50 መድረሱን ሬድዮ ፋና በድረገፁ አስፈሯል፡፡

በነ ዳዊት ኢትዮጵያና መሃመድ ኢሳ መዝግብ የተዘረዘሩ 13 ተጠርጣሪዎች ላይ የኮሚሽኑን የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ወደ 7 ዝቅ በማድረግ ከነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ጋር እንዲታይ ለግንቦት 19 ቀጥሯል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ዛሬ አዳዲስ 11 ተጠርጣሪዎችን ለችሎቱ አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።ከተጠርጣሪዎቹ መሃከልም የባለስልጣኑ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማስከበር ኃላፊው አቶ አምባው ሰገድ አብርሃ እንዲሁም በባለስልጣኑ የሚሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለዓብ ዘርዓብሩክ ይገኙበታል።

እንዲሁም ከሰሞኑ ከሃገር ለመውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት በባለስልጣኑ የአቃቂ ቃሊቲ ህግ ማስከበር ቡድን አስተባባሪ አቶ ተመስገን ስዩምና የባለስልጣኑ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ተመስጌንን ጨምሮ 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር 50 አድርሶታል።
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች እስካሁን ደንበኞቻቸው በህገመንግስቱ የተሰጣቸውን መብት እየተጠቀሙ አይደለም በማለታቸው ችሎቱ በተለይ ከኮሚሽኑ መብታቸውን የማስከበር ከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚጠበቅበት አሳስቧል።

ምንጭ፡ ሬድዮ ፋና

No comments:

Post a Comment