Monday, May 20, 2013

በኢራቅ የደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ከ60 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በዙዎች ደሞ ለጉዳት ተዳርጓል



በኢራቅ ሶስት ከተሞች(ባግዳድ፣ባስራና ሳማራ) የደረሰው በመኪና ላይ የተጠመደ የቦምብ ፍንዳታ ከ60 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳርግ ብዙዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ኢራቅ በአሜሪካ ከተወረረች ወዲህ 11 ዓመታት ያስቆጠረች ሲሆን ከመጋቢት11 ቀን 1995 እስከ መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ከ112,017 እስከ 122,438 የሚደርሱ ሲቪል ዜጎችዋን አጥታለች፡፡

ዓለም ግን በኢራቅ እየደረሰ ስላለው የሰውና የንብረት ውድመት ጀሮ ደባ ልበስ ያለው ይመስላል፡፡በአሜሪካ በቦስቶን ማራቶን የደረስ የፍንዳታ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ቀጥፎ መቶዎች ለጉዳት ዳርጎ የነበረ ሲሆን በዓለም ደረጃ ሲራገብ ነበር የሰነበተው፡፡የኢራቁ ውድመት ግን ከነካቴው የተረሳ ይመስላል፡፡



ምንጭ  ፡http://www.bbc.co.uk/news/

No comments:

Post a Comment