Saturday, May 25, 2013

አንድነታችን



የአንድነታችን ምሰሶ፣
በዘረኝነት በጭፍን ጥላቻ ተገረስሶ፣
ኦና እንዳይ ሆን ተገርስሶ፣ተደረማምሶ፣
ሰላምና ፍቅር፣
የአብሮነታችን ምስጢር፣
ተራት ተረት ሆኖ እንዳይ ቀር፣
እንዋደድ፤እንተዛዘን፤እንተሳሰብ፤ እንከባበር፡፡
እኛ እናንተን፣ እናንተ እኛን
ስትወቅሱን፣ስንቅሳቹ፣ ስንወቃቀስ፣
ስንከሳችሁ፣ሰትከሱን፣ስንካሰስ፣
ስንሰዳደብ፣ስንደባደብ፣ ስንቧቀስ፣
የዘር ሐረጋችን ስሩ ተመሶ እንዳይበጣጠስ፣
እንቻቻል፤እንታረቅ፤ወደ አብሮነታችን እንመለስ፡፡
እናት አባቶቻችን እኩል ያወረሱን ቤት፣
ስንጯጯኽ፣ስንናከስ እንደ ወሻና ድመት፣
ጓ! ብሎ እንዳይከፈት፣ጠላት እንዳይገባበት፣
መናናቅ፣ጥላቻና በቀሉን ትተን፣
በዘመነ ጉለባላይዜሽን ስንናቆር፣ስንበታተን፣
ዓለም ጉድ! እንደይሰኝ፣እንደይስቅብን፣እንደይንቀን
የመፈቃቀድ፣የመፈቃቀር፣የእኩልነት መፈክር አንግበን
በአንድ አዳራሽ ተሰባስበን፣
እንነጋገር፤እንደማመጥ፤እንምከርበት
‹‹ልዩነታችን ውበታችን ነው›› አንድነታችን እናስምርበት፡፡






No comments:

Post a Comment