Friday, May 24, 2013

ጥቋቁር አይጦችና ጥቋቁር ድመቶች



19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አከባቢ የነጫጭ ድመቶች ፋብሪካዎች የጥረ እቃ ድርቅ ስለመታቸው ስራ ሊያቆሙ ግድ ሆኖባቸው ነበር፡፡ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የተወሰኑ ነጫጭ ድመቶች ወደ ጥቋቁር ድመቶች ሃገር በመሄድ ለችግሩ መፍትሔ የሚሆን መላ አገኙ፡፡በጥቋቁር ድመቶች ሃገር የሚገኙ ንጥረነገሮችም አንድም በማታለል ከልሆነም በማስገደድ ወደ ሃገራቸው በመውሰድ የፋብሪካዎቻቸው እስትንፋስ ለማቆየት ቻሉ፡፡ያ መላ በመላው ንጫጭ ድመቶ ሃገራት ስለተደረሰበት እርሰ በርሳቸው መፎካከር ጀመሩ፡፡

ይህን የተገነዘበው አቶ ቫን ቢስማርክ የተባለ አንድ ነጭ ድመት ጎረቤቶቹ የሆኑትን ሌሎች ነጫጭ ድመቶችን ወደ ሃገሩ በመጥራት የጥቋቁር ድመቶችን ሃገራት አርሰ በርሳቸው ሳይጣሉ እንዴ መቀራመት እንደነበረባቸው ተመካከሩ፤ ተስማሙም፡፡ይህ ይሆነው በነጫጭ ድመቶቹ አቆጣጠር 1884- 1885 ነበር፡፡ከዛም የጥቋቁር ድመቶች ሃገራት(ከአንድ በስተቀር) እንዳለ በነጫጭ ድመቶች ቅኝ ግዛት ስር ወደቁ፡፡

በተናጠል ታግለው ነጫጭ ድመቶችን ከሃገራቸው ማባረር ያስቸገራቸው ጥቋቁር ድመቶች በተራቸው የጥቋቁር ድመቶች አንድነት ለመመስረትና የጋራ ጠላቶቻቸው የሆኑት ነጫጭ ድመቶችን ታግለው ከአህጉራቸው ለማባረር  1945(የነጫጭ ድመቶች አቆጣጠር)  እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ እንቅስቃሴው እየተጠናከረ መስለመጣም 1963(የነጫጭ ድመቶች አቆጣጠር) የጥቋቁር ድመቶች አንድነት ድርጅት ተመሰረተ፡፡

የድርጅቱ መቀመጫም በነጫጭ ድመቶች ቅኝ ግዛት ያልወደቀችው የጥቋቁር ድመቶች ሃገረ እንዲሆን ተወሰነ፡፡ይህ ድርጅት የጥቋቁር ድመቶች አህጉር እንዳለ ከነጫጭ ድመቶች ቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት ሚና እንደነበረው ይነገራል፡፡ኢምፔሪያሊዝም(የነጫጭ ድመቶች ልዕልና)፣ኮለኒያሊዝም(የነጫጭ ድመቶች ቅኝ ግዛት) ኒዮ ኮለኒሊዝም(የነጫጭ ድመቶች ዳግመ ቅኝ ግዛት) ለማዳከም ብሎም ለማስወገድ የማይናቅ ትግል አድጓል እያደረገም ይገኛል፡፡

የጥቋቁር ድመቶች አንድነት ድርጅት 2001(የነጫጭ ድመቶች አቆጣጠር(ጥቋቁር ድመቶች ለምን በነጫጭ ድመቶች አቆጣጠር እንደሚጠቀሙ አይገባኝም))  ወደ የጥቋቁር ድመቶች ህብረት ተሸጋገረ፡፡አንድነቱና ህብረቱም ከተመሰረቱ 50 ዓመት ሞላቸው(50 ጎልማሳ ሆኑ)፡፡ይህ 50 ዓመት የወርቅ እዩ በልዩ ታድያ ሰሙኑን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ጥቋቁርና ነጫጭ ድመቶች በጋራ እንደሚያከብሩትም ይነገራል፡፡

ይህ በዓል ሌላ ልዩ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ የሚታሰብ ክስተት ይፈፀማል የሚባል ወሬ እየተናፈሰ ይገኛል፤ ከሰማይ እንደ ወረደ የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ የተጠራ የጥቋቁር አይጦች ‹‹ሰላማዊ ስልፍ››!፡፡እንዚያ ጥቋቁር አይጦች ጥቁር በጥቁር ለብሰው ነው አሉ የጥቋቁር አይጦቹን 50 ዓመት በዓል ላይ ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ የተዘጋጁት፡፡ጥቋቁር አይጦቹ ‹‹ስላማዊ ስልፍ›› የማድረግ መብታችን ይመለስ፤ በሽብርተኝነት ወንጀል ተፈርዶባቸው የታሰሩት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞቻችን ይፈቱ፤የሃይማኖት መብታችን ይከበር ብለው በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ ሞስሊሞች ይፈቱ፤የስራአጥነትና የንሮ ውድነት አዙሪቶች አፋጣኝ መፍትሔ ይበጅላቸው እና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችና ትእዛዞችን ለማስተላለፍ ተዘጋጅቷል፡፡

ጥቋቁር ድመቶቹ ግን ከአሁን በፊት በተካሄደው የጥቋቁር አይጦች ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ(ድመቶቹ የጥፋት ሰልፍ ይሉታል)›› የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት በመድረሱ ‹‹የሰላምም ይሁን የጥፋት ሰልፍ መውጣት አትችሉም፡፡›› እያሉ ይገኛሉ፡፡አሻፈረኝ ብለው ‹‹በጥፋት ሰልፉ›› ላይ ከተገኙም ድንጋይና ብረት ፈጭቶ ድቄት የሚያደርግ ጥርስ የታጠቁ ጥቋቁር ደመቶች ተዘጋጅተው እንደሚጠበቋቸው ይወራል፡:

ስለሆነም ጥቁር ለባሽ ጥቋቁር አይጦች ሆይ ለውድመት የተዘጋጀ ሌላ ትርፍ ህይወትና ንብረት የለንምና በየጉድጓዳችሁ ተቀብራችሁ ዋሉ እንላለን፡፡የባሰ አታምጣ ነውና ‹‹የጥፋት ስልፋችሁ›› አንፈልግም፤ የናንተ የአዞ እምባ ለሃገር ለወገን አይበጅም፤የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ነችና ጨዋታችሁ አላማረንም፤አያዋጣንም እንላለን፡፡አይሆንም ካላችሁ ግን ወርድ ከራሴ ብያለሁ፤የወጥመድና የድመት ቁርስ ትሆናላችሁ፡፡




No comments:

Post a Comment