ሃገራችን በማህበራዊ፣በምጣኔ ሃብትና በፖለቲካ ኋላ ቀር የሆነችው መሪዎቻችን በሚከተሉት የአስተዳደር ስልት አማካኝነት ብቻ
አለመሆኑን የሚያስረዳ ነገር ሰሙኑን ተከስቷል፡፡ክስተቶቹ ተቃዋሚዎች የሚያራምዱት ብሔር ከብሔር፣ ወገን ከወገን የመለያየት ሴራ
ያለበት መሆኑንም ያመለክታሉ፡፡አንደኛው በባህርዳር የተከሰተው የንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ ትላልቅ የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሃብቶች በሙስና ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር መዋላቸውን
ነው፡፡
የሁለቱም ክስተቶች አንድምታ በግራና ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች
እይታ ለየቅል ነበር፡፡በፌደራል ፖሊሱ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የብሔርና የፖለቲካ ትርጉም መስጠት አጉል ፅንነኝነትን ያመለክታል፡፡ፖለቲካስ
ይሁን ሊባል ይችላል፣ ነገር ግን አንድ ግለሰብ ብሔርን ሊወክል አይችልም፡፡ፖሊስ ይሁን፣የመንግስት በለስልጣን ይሁን ምን ይሁን
የሚፈፅማቸው ተግባራት ራሱን እንጂ የትኛውም ብሔር ተልእኮ አይኖራቸውም፡፡
የነመላኩ ፈንታ በህግ ቁጥጥር መሆን በአንዱ ጫፍ ገዢው መንግስት
ለተንኮልና የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ብቻ የሸረበው ሸራ ነው የሚል አልቧልታ ያስተጋባል፡፡መላኩ የታሰረው በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ
የፓርቲው ደጋፊ የሆኑ ባለሃብቶችን በመተናኮሉ ነው የሚሉ ፅንፈኛ ወገኖች አሉ... እንደነ ተመስገን ደሳለኝ ያሉ የፕሮፎሰር መስፍን ቡችላዎች፡፡
እነ
አብረሃ ደስታ ደሞ ኢህአዴግ በሙስና(በጥቅም) የተመሰረተ ፓርቲ ስለሆነ የሙሰኞች መታሰር አንድም የመጠላለፍ ተንኮል ነው አልያም
ዘላቂነት የሌለው እርምጃ ነው ይላሉ፡፡ምክንያቱን ሲያስረዱ ደሞ ኢህአዴግ ሙሰኛ ስለሆነ ሙሰኞችን አሰረ ማለት ራሱን አሰረ ማለት
ነው፤ ይህ ማለት ደሞ ኢህአዴግ ይጠፋል በማለት ይሞግታሉ፡፡ይህ መንገድ የከሰሩ ፖለቲከኞች አካሄድን ታመለክታለች፡፡ሚጢጢየ ተንኮል
ብትሆንም ህዝቡ ሙሰኞችን እንዳይዋጋና ተስፋ ቆርጦ እያለቀሰ ዝም እንዲልላቸው በማሰብ የሸረቧት ሸራ ነች፡፡ህዝቡ በመልካም አስተዳደር
እጦት በሎም በሙስና ተማርሮ ሲያለቅስ ተቆርቋሪ መምሰል አብረው የአዞ እምባ ለማንባት ብቻ፡፡እነሱ ስልጣን ካልያዙ በስተቀር ከመልካም
አስተዳደር እጦትና ከሙስና መንሰራፋት ልንፀዳ እንደማንችል እየነገሩን ነው፡፡ ነገር ግን የእነሱም ማንነት ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል
... በኢህአዴግ ታኝከው የተተፉናቸውና፡፡ኢህአዴግ በሙስና ሲመሰረት ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩ ናቸው አብርሃ እንደጣኦት የሚያመልከው
ፓርቲ መስራቾች፡፡ የኢህአዴግ አባል ሆኖ ከሙስና የፀዳ መሆን የማይቻል(ከባድ) ከሆነ ገብሩ አስራትና አረጋሽም ሙሰኞች ናቸው ማለት
ነው፡፡አብርሃም ያው ነው... በእነርሱ የተጠመቀ አዲስ ተከታይ ነውና፡፡
በሌለው
በኩል ደሞ መንግስት እንደውም ዘግይቷል ቀደም ብሎ እርምጃ መውሰድ ነበረበት የሚሉም አሉ፡፡እንደውም መዘግየቱም ይሁን፤ ነገር ግን
ሊቀጥልበት ይገባል በማለትም ያክላሉ፡፡እውነት ነው፤ የፈለውገው መንግስት ያስተዳድረን ሙስናን ያጥፋልን፤መልካም አስተዳደርን ያስፍንልን፤
ከድህነት ያላቅቀን ነው ይምንለው፡፡
አለዚያ ሃገሬን ሃገሬን አይልም ወይ ሰው
ምንትስ ሲሉት ሆድ እየባሰው፡፡ እያሉ በማንጎራጉር ችግሮች አይፈቱም፤ ሃገር ከድህነትና ኋላ ቀርነት መንጋጋ አያስጥሉም፡፡እነዚህ
ጠላቶች ከለተመቱ ደሞ የመልካም አስተዳደር እጦትም ሆነ ሙስና ሊወገዱ አይችሉም፡፡ይህ ማለትም ሁሌም ምዕራባውያን ጥገኞች ሆነን
ቀረን ማለት ነው፡፡ሁሌም የስደት ንሮ፣ ሁሌም በባይቷርነት ህይወታችን ልንመራ፡፡ታድያ ሃገር ካለሰው ምንድን ነች? መልሱ በሚከተለው
ግጥም ያገኙታል፡፡
ካለሰው
ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር
ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?
የኔ ውብ ከተማ
ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር
የኔ ውብ ከተማ
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡
ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?
የሰውን ልብ ነው፡፡
ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ
ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሃን ኩሬ
በሺ ብርሃን ጎርፍ
ምን ያደርጋል?
ምን ያሳያል?
ካለሰው ልብ ብርሃን
ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ ተስፋ ሻማ
ጨለማ ነው
ሁሉም ጨለማ፡፡
በዓሉ ግርማ፡፡(1984)፡፡‹‹ኦሮማይ››፡፡
በዓሉ ግርማ ነገሩን ጨርሶታል፡፡ሃገር ጋራ ሸንተረር ብቻ አይደለም፡፡ሃገር
ኗሪው ህዝብ ብቻም አይወክልም፡፡ ኢትዮጵያ ማለት በኢትዮጵያ ድምበር ውስጥ ያለው መልክአ ምድር ብቻ ሳይሆን በዛው የሚኖር ህዝብም
ይጨምራል፡፡አድርገውና፣የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለ ወደ አመሪካ ቢሰደድ አመሪካ ኢትዮጵያ ልትሆን አትችልም፡፡ኢትዮጵያ ካለ ኢትዮጵያውያን፣
ኢትዮጵያውያን ደሞ ያለኢትዮጵያ ዋጋ የላቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብን እየገደሉ ‹‹ኢትዮጵያ ወይም ሞት››
ማለት የአመክንያ ድህነት ያሳያል፡፡
አንድ ነገር ስንወድም ሆነ ስንጠላ በምክንያት ተደግበፈን መሆን
አለበት፡፡ አለዚያ ግን በጭፍን ስሜት ተገፋፍተን የወደድነውን ነገር መልሰን በጭፈን ስሜት የማንጠላበት ማረጋገጫ አይኖረንም፡፡ምክንያቱም
ሁሉ ጊዜ አንድ ዓይነት ስሜት አይኖረንምና ነው፡፡
ሚዛናዊ ዘገባ ነው እስካሁን ያየሁት በርታ
ReplyDelete