በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉመሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ወ/ሮ ሃይማኖት ተስፋይ ባለቤታቸው ከተጠረጠሩት ወንጀል ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ሲያሸሹ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከፖሊስ የገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ወ/ሮ ሃይማኖት ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው በሌሎች ግለሰቦች እጅ እንዲደበቁ ያሸሺቸው ሰነዶች በተለያዩ ቦታዎች በአቶ ገብረዋህድ ስም የተመዘገቡ የቤትና የቦታ ካርታዎች ናቸው፡፡
ወ/ሮ ሃይማኖት ካርታዎችን ሲያሸሹ ጥቆማ የደረሰው የደህንነትና የፖሊስ ሃይልም ክትትል በማድረግ ካርታዎቹን ከተደበቁበት ቦታ ይዘዋቸዋል፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከትላንት በስትያ ግንቦት 2/ 2005 ዓ/ም በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ቤት በተደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያና የውጭ ሃገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ ኢሬቴድ
No comments:
Post a Comment