Friday, May 10, 2013

የሰልፉ ነገር እኔ የለሁበትም!

 




ሰማያዊ ፓርቲ በ50ኛው የአፍሪካ ሕበረት የምስረታ በዓል ዳጋፊዎቹ ጥቁር በጥቁር ለብሰው እስካሁን ድረስ በሃገራችን ሰሚ ያላገኙ ጭሆቶች ከመላው ዓለም ለሚመጡ የበዓሉ ተሳታፊዎች ለማሰማት ሌላ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ሰልፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡‹‹ሰማያዊ ዓይን›› ይሚባል ትያትር አይቻለሁ ልበል?‹‹ባለቀለም ህልሞች›› የሚባል ፊልምስ ነበረ አይደለም እንዴ? ግን ትያትሩም ሆነ ፊልሙ የተጠቀሰው ቀለም ነበራቸው? እኔ አላየሁም፡፡እናንተስ?

አሁን ደሞ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ›› መጣልን፡፡ግን ‹‹ሰማያዊ›› ሲባል ምን ማለት ይሆን? ‹‹የፌስቡክ አርበኞች›› ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቴን ይከበርልኝ እንዳሉት እኔም የመጠየቅ መብቴን ይከበርልኝ እላለሁ... ለህዝብና ለመንግስት፡፡ጥያቄው የሚቀርበው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይሆን በፌስቡክ አደባባይ መሆኑን ይታወቅልኝ፡፡እናም ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ›› ማለት፡-

       አንድ

 ኢህአዴግን ከስልጣን አባርሮ በኢትዮጵያ ለመንገስ ከሰማይ የተላከ ፓርቲ ማለት ነው? ወይስ ከሩቅ ሲመለከቱት ሰማያዊ ቀለም ያለው የሚመስል ነገር ግን ልክ እንደ ሰማይ ሲቀርቡት ምንም ዓይነት ቀለም የሌለው(color blind) መሆኑን ነው? በእኔ እምነት ፓርቲው ቀለም አልባ ወይም የማይታይ የማይዳሰስ መሆን አለበት፡፡ምክንያቱም ሰማያዊ መስሎ በመታየት ካልሸወደው በስተቀር ከፈለገው ቢመጣ ኢህአዴግን ከስልጣን ማባረር ቀርቶ በኢህአዴግ ግዛት ውስጥ መብረርም የሚቻለው አይመስለኝ፡፡ለምክንያቱ ምክንያት ላቅርብ መሰለኝ፡፡
1. ከሰማይ ቢላክ ኢህአዴግን ከስልጣን ማባረር አይችልም፡፡ መንግስቱ ሲነግስ ከሰማይ የተላከው ሃይለስላሴን ከወንበሩ ስር እንደቀበረው ይታወቃል፡፡ታድያ መንግሰቱን የገነደሰው ኢህአዴግ መንግስቱ ያደረገውን ማድረግ እንዴት ያቅቷል?የማይተሳብ ነው፡፡አንድ ነገር ግን ጠርጥሬያለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሰማይ ቤት ግዛት ሳይነሮው አይቀርም፡፡ እናም ደጋፊዎቼ ናቸው ያላቸውን በስኮላርሽፕ አማካኝነት እስከወድያኛው ሊልካቸው የፈለገ ይመስለኛል፡፡በሰማያዊ ስኮላርሽፕ ዲያስፖራ መሆን አይቻልም፡፡ወደ ሃገር ቤት ብር መላክ፣የአነጋገርና የአለባበስ ለውጥ ማምጣትና  አባይ እንዳይገነባ ‹‹ሰላማዊ›› ሰልፍ ማደረግም አይታሰብም፡፡መጠንቀቅ ነው ታድያ፡፡
2. ከጫካ ቢመጣም ኢህአዴግን ከስልጣኑን ንቅንቅ ማድረግ አይችልም፡፡የኢህአዴግና የጫካ ፍቅር የወላጅና የልጅ ያህል ነው፡፡ ኢህአዴግ በምሬት ተረገዘ፡፡ ጫካ ውስጥ ተወለደ፡፡ ጫካ ውስጥ አደገ፡፡ የጫካ ነገስታት የሚባሉ እንደ አምበሳ፣ነበር፣ዘንዶ ወዘተ ሁሉ ገድሎ በጫካው ነገሰ፡፡ግዛቱን ለማስፋፋት ወደ ከተማ ወጣ፡፡የከተማ አውሬዎች ‹‹ አንዲት ጥይትና አንድ ሰው ብቻ እስኪቀር ድረስ እንዋጋለን›› ብለው ቢፎክሩም በመስክ መነፅር ጎፈሬውን ሲመለከቱት  ሐሞታቸው ፈሰሰ፡፡እናም ‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም››  የሚሉት ፈሊጥ ረስተው ለራሳቸው ቅድምያ ሰጡ፡፡ የኢትዮጵያ ‹‹ደፋሩ፣ጀግናው፣አገር ወዳዱ...›› እግሬ አውጪኝ አሉ፡፡ ፈረጠጡ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ግን ከተማ ውስጥ ነው ውልደቱም እድገቱም፡፡ አባቱም ጫካ ሳይሆን የቅንጅት ልጅ መሆኑን ነው ፓርቲው በአንደበቱ የሚናገረው፡፡ቅንጅትን ብትንትኑን ያወጣው ማን ነበር? ተበትኖስ የት ሄደ? ወደ ጫካ አልሄደም፡፡ ከኢህአዴግ በፊት ነበር አሉ ጫካ ውስጥ የገባው... አሲምባ ተራራ፡፡አልቀናውም እንጂ ያኔም ኢህአዴግን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር ይባልል... አጥፍቶ መጥፋትም አልሆነለትም፡፡ ለዛም ነው ዳግም  ወደ ጫካ ከመሞከር ይልቅ የአመሪካና የአውሮፓ ጎደናዎችን ለመሽግነት የመረጣቸው፡፡

ሁለት

ሰማያዊ ቀለም ያለው ፓርቲም ሊሆን አይችልም፡፡ምክንያቱም በኢትዮጵያ ባንዴራ ላይ ሰማያዊ ቀለምና የከኮብ ምልክት የጨመረው ኢህአዴግ ነው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ ደሞ ከቅንጅት እንጂ ከኢህአዴግ ጋር ምንም ግንኙነት እንደ ሌለው ተናገሯል፡፡ቢሆን ቢሆን አገር ወዳድነቱን ለማስመስከር አሮንጓዴ፣ብጫ ወይም ደሞ ቀይ ፓርቲ መሆን ነበረበት... ኢህአዴግ ያልነካት የኢትዮጵያ በንዴራን ለመወከል፡፡

ሶስት

ቅንጅት ለምን ነበር የተቀናጀው?የኢትዮጵያ ህዝብን ነፃ ለማውጣት እንዳትሉኝ እዳንተዛዘብ፡፡ቅንጅት ከኢጎው ነፃ ለመውጣ ነበር እንደ ብትቶ ከዚያም ከዚያም የተጠቀቀመው፡፡ቅንጅት እንደ ስሙ የተቀናጀ አልነበረም፡፡ በእርግጥ የቅንጅት መሪዎችና አባሎቻቸው በአንድ ጋን ውስጥ ነበሩ፡፡ነገር ግን አንደ ወሃና እንደ ዘይት ለየቅል ሲንሳፈፉ ነበር የኖሩት፡፡በመጨረሻም ጋኑ ሲሰበር ወሃው(የዋሁ ህዝብ) ወዲህ ዘይቱ ወድያ ሆነ፡፡ወሃው አሁንም ወሃ ነው፡፡ፀሐይ የመታው ተኗል፣ ያመለጠው ብዙ ተምሯል ተማሯልም፡፡ዘይቱ ግን ምንም አልሆነም፤ አሁንም አየተንሳፈፈ ይገኛል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የዘይቱ ፍንጣሪ ይመስላል፡፡ በየዋሃን እጅ እሳት ለጨበት ተዘጋጅቻለሁ እያለን ይገኛል፡፡የአዲስ አበባ ወጣቶች ሆይ፣ እኔ የለሁበትም፡፡ነገሩ በፌስቡክ እንደ መቃወም፣ የተቃወመውን like፣ share ወይም comment እንደማድረግ ቀላል አይደለም፡፡‹‹ሰላማዊ›› ሰልፉ ለሰላምም ይሁን ሰላም ለማደፍረስ፣ ኢህአዴግየ እናንተን ማየት አልፈልግም ካለ አደራ ችላ እንዳትሉት፡፡አያዋጣችሁም፡፡ ለኢህአዴግ መወገኔን እንዳይመስላችሁ ለናንተ ብየ ነው፡፡በ97 የተቀጠፉት ወጣቶች፣የተሰባበሩት አውቶብሶች፣የወደሙ ንብሮቶች ዳግም አልተመለሱም፡፡እሺ፣ አውቶብሶቹ ተጠግነው ወደ ስራ ተመልስ ሊሆን ይችላል፡፡ ልጆችስ? እነ ደኩተር ብርሃኑ ነጋም ከአንድ ደቂቃ በላይ የህሊና ፀሎት አላደረጉላቸውም ፤ እነንኳንስ ሊጠገኑ ቀርቶ፡፡

የህሊና ፀሎት ማንም ከሞት አላዳነም፡፡እኔ እስከማውቅው ድረስ ሰው ከሞት የሚድነው በቅዱሳን መፃሕፍት ብቻ ነው፡፡ሰው ሞቶ ከተቀበረ በኋላ  happy birthday ምናምን ብሎ ነገር እኔ አይገባኝም፡፡ኢህአዴግ ‹‹ቃሌ ከሚጠፋ የተወለደው ይጣፋ›› ብሎ ‹‹ሰላማዊ›› ሰልፍ እንደት ወጡ ቢፈቅድላችሁም አደራ ድንጋይ እዳትወረውሩ፡፡ድንጋይ ብትወረወሩ ቦምብ ወይም አውቶማቲክ እንደሚወረወርባችሁ እወቁ፡፡

ይህ ሁሉ የሰልፍ አምሮትና ሱስ ከየት መጣ?የኢትዮጵያ ህዝብ በንሮ ውድነት ምክንያት መኖር ያንገሸገሸው ከአፄ ሃይለስላሴ ዘመነ ምንግስት ጀምሮ መሆኑን በዓሉ ግርማ ‹‹በደራሲው››ና ‹‹በሐዲስ›› መፅሐፎቹ ላይ አስፍሮት ይገኛል፡፡ሰልፍ የተጀመረው ከዛን ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡መንግስት ለመደገፍ ሰልፍ፣ለመቃወም ሰልፍ፣ዳቦ ለመግዛት ሰልፍ፣ስኳር ለመግዛት ሰልፍ፣የውሃ፣የመብራትና የስልክ ክፍያ ለመፈፀም ሰልፍ፣ታክሲና አውቶብስ ለመሳፈር ሰልፍ... ሰልፍ!ሰልፍ! ሰልፍ! በቃ ለመኖርም ሆነ ለመሞት ተሰልፈናል፡፡ ለዛም ሳይሆን አይቀርም የኢትዮጵያውያን አማካይ ዕድሜ ከ40 በታች ወርዶ የነበረው፡፡ አሁን 59 መድረሱን ምንጮች ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከሌሎች ሃገሮች ሲነፃፀር ዕድሜቻን አጭር ነው፡፡

ለምን? ምክንያቱም ፈጣሪ ስለማያዳላ ነዋ፡፡ተፈጥሮ ከማንም ምንም አትፈልግም፡፡ሃብታም፣ድሃ፣ባለስልጣን፣ቄስ ጳጳስ፣ሼክ፣ፓስተር ምናም ሳትል እኩል በአሸዋ ይ እነዳአነፀቻቸው ሁሉ ከአሸዋው ትጠራርጋቸዋለች፡፡ ዓለም እንደ ባለስልጣኖቻችን ሙሰኛ አይደለችማ! እናም እኛ ኢትዮጵያውያን ለንሮም ለሞትም ተሰልፈን እያለን ማንን ታስቀድማለች?በስልፋችን መሰረት ነው የምታስተናግደን፣የምታስወግደን፡፡

ስለዚህ፣የአዲስ አበባ ልጆች ሆይ! ልብ አርጉ፡፡ ሰልፍ ካማራቹ ዳቦና ስኳር ግዙ ... ብር ካላችሁ ማለቴ ነው፡፡ለወላጆቻችሁ የውሃ፣የመብራትና የስልክ ክፈሉላቸው... ይመርቋችሁማል፡፡አዲስ አበባን በታክሲና በአውቶብስ ተሳፍራችሁ ጎብኟት፡፡መሳደብና መደባደብ ካማራችሁም ወደ ፌስቡክ ጎራ በማለት ግለታችሁ ማርገብ ትችላላችሁ፡፡አይ! ያላችሁ እንደሆነ፣ እኔ የለሁበትም፡፡ሰልፍ ሰልችቶኛል፡፡ጥቁር  መልበስም አልወድም፡፡ቸር ያሰማን!






























No comments:

Post a Comment