በአሁኑ
ግዜ የጃዋር ሞሐመድን ያህል የመገናኛ ብዙሐን ቀልብ የሳበ ፅንፈኛ ያለ አይመስለኝም፡፡የፌስቡክ መንደር ጃዋር ጃዋር ካለች ሰነባብታለች፡፡ቲዊተር የጃዋር ስምና አክራሪ አስተሳሰቦቹን እየደጋገመች በማስተጋባት ላይ ነች፡፡ዩቲዩብ በምስልና በድምፅ የተደገፉ የጃዋር ንግግሮችን ዘግባ ማስቀመጥ ለጎብኝዎች በነፃ እያስኮመኮች ትገኛለች፡፡የአዲስ አበባ መፂሔቶች በመጀመርያ ገፆቻቸውን ምስሉን በማተም የልዩ ዘገቦቻቸው ርእሰ አንቀፅ አድርገውት ከርመዋል፡፡
ጃዋር
የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ መሆኑንና አሁንም በኮሎምብያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በመከታተል እንደሚገኝ ዕንቁ መፂሔት በቅፅ 6 ቁጥር 95 የሐምሌ እትሟን አስፍራዋለች፡፡ከሚሰጣቸው ፅንፈኛ አስተያየቶች የምንረዳው ግን በስመጥር የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ዘመናዊ ትምህርት የሚከታተል ሳይሆን በዓረብ ሃገራት በሚገኙ የሙጃህዲን ትምህርት ቤቶች የእስልምና አክራሪነት በመሰልጠን ላይ የሚገኝ ነው የሚመስለው፡፡ከአፉ የሚወጡ ቃላት በምክንያት የተደገፉና የእስልምና መሰረታዊ አስተምህሮ መሆኑን የሚታወቀውን ሰላማዊነት ሳይሆን ሞስሊሞችም ሳይቀር በመግደል የራሳቸው እምነት በሃይል ለማስፋፋት የዘመቱት ሙጃህዲኖችን ነው የሚመስለው፡፡ይህ ስሜታዊነቱ ደሞ የኢትዮጵያውያን አብሮ የመኖር ባህል የሚያናጋ አነጋገር እንዲከተል አድርጎታል፡፡አርቆ ማሰብ ተስኖታል፡፡
‹‹እኔ ከኢትዮጵያዊነቴ በፊት ኦሮሞ ነኝ፡፡›› ይሁን መብቱ ነው፡፡‹‹ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጪ ነች፡፡›› ብሎ ሲል ነገሩ ተገለጠልን… ያው በአሜሪካ የዘመተ የኦነግ ታጣቂ መሆኑን ታዘብን፡፡በዚህ ግን አላቆመም ‹‹ስለ እስልምና መናገር የጀመርኩት ከጎንደር የመጣ አንድ ጓደኛየ ካገኘሁ በኋላ ነው›› በማለት ተንተባተበና(ሲንተባተብ የፈጠራ ወሬ ለማውራት እየተታገለ እንደሆነ አስተውያለሁ፡፡) ጎንደር የሚኖሩ ሞስሊሞች የሃይማኖት ነፃነት አጥተው እንደሚኖሩ፣በኦሮምያ ክልል የሚኖሩ ሞስሊሞች ግን ማንም ቀና ብሎ ሊያያቸው እንደማይደፍር ቢሞክርም በመንጫ እንደሚሉት የህፃናት ጀብደኝነት መቅደዱን ቀጠለ፡፡ስለሆነም የኦሮም ሞስሊሞች የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብትና የፖለቲካ ስልጣን መቆጣጠር እንዳለባቸውና የሌሎች ሞስሊሞች ነፃነት የብዛታቸውን ያህል በመንጫ ማረጋገጥ እንዳለባቸው በስሜት አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡
ይህ አነጋገር በጅሃዳዊ ሃረካትና በአኬልዳማ የኢትቪ ተከታታይ ዘጋቢ ፊልሞች ያየናቸው የሰው ህይወትና የሃገር ንብረት ለማውደም የታቀዱ ግንደሞ በድህንነቶች የከሸፉ ሰይጣናዊ ዝግጅቶች እውነትነት ሊኖራቸው እንደሚችል ያሳያል፡፡የኢትዮጵያችን ሰላም በሰለጠነው ዓለም ሰልጥነው ሳይሆን ሰይጥነው በሚመጡ አክራሪዎች እየተፈተነ ይገኛል፡፡አክራሪነትን ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት በሚል ሰበብ ልአላዊ ሃገሮችን በመውረር የሚትታወቀው አሜሪካም የአክራሪነት ፈጣሪና ስፖንሰር መሆንዋን ግሃድ ያወጣ ርኩስ ተግባር ነው፡፡አዎ! አሜሪካ የአክራሪው ግንቦት ሰባት መስራችና መሪ የሆነው ዶ/ር ብርሃኑን እሽሩሩ እያለች ትገኛልች፡፡ኦነጎችም እዛው ናቸው፡፡የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናትም እዛው ሆነው የጥፋት መርዛቸውን በመርጨት ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያችን ታሪክ በዳይና ተበዳይ ብሔር አለ የሚል እምነት የለኝም፤ለወደፊትም ይኖረኛል አልልም፡፡የኢትዮጵያውን
ድህነት፣ኋላ ቀርነት፣ምሃይምነት፣በሽታ፣የመልካም አስተዳደር እጦት ዕድሜ፣ፆታ፣ ብሔርና ሃይማኖት አይለይም፡፡ድሮም ዘንድሮም የንፁኃን የምሬት እምባና ደም ሚፈሰው ከቅንድባቸው ርቀው ማይት በማይችሉ ነፍሰ በላ ባለስልጣናት ነው፡፡የእማማ ኢትዮጵያ ባለስልጣናት በወገኖቻቸው ላይ(በተለይም በስልጣናቸው ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ ብለው ያሰቧቸውን ወገኖችን) ያልፈፀሙት ግፍ የለም፡፡በጣም የሚያሳዝነው ግን ይህ ሰይጣናዊ ሴራቸው የሚፈፅሙት አንዱ ብሔር በሌላው እንዲሳና በጠላትነት እንዲፈርጀው በማድረግ ነው፡፡ይኸው መርዛቸው ዛሬም ድረስ ሊሽር አልቻለም፤ እርሰበርሳችን በጎሪጥ እንድንተያይና ያለፈው ታሪክ እያጣቀስን እንድንወነጃጀል አድርጎናል፡፡የተማሩም ያልተማሩም ወገኖቻችን ይህ እውነታ ማየት ተስኗቸው እንደሁነኛ የስልጣን መወጣጫ መንገድ ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡በኢትዮጲያውን ጫንቃ ተፈናጦና
እንደ መዥገር ተጣብቆ እንደ ቅቤ አቅልጦ፣እንደ ብረት ቀጥቅጦ በመግዛት ከቤተሰቡ ጋር ተንደላቅቆ ለመኖር የሚከጅለው ሁሉ የመጀመርያዋ
እቅዱ ያቺ የተለመደችው መርዝ መዝራት ነች፡፡
እኔና መሰሎቼ በጃዋር አነጋገር አዝነናል ተበሳጭተናል፤ጃዋር ምን ነካው? አሜሪካስ
ምን አስቀመሰችብን? ብለን እንድንጠይቅ ተገደናል፡፡ጃዋራውያን ግን የልብ ልባቸው የሞላላቸው ይመስላል፡፡
ምን
አለ ጃዋር ምን አለ
አኸ
መንጫየን ይዠ
አኸ
ሁሉንም ገዝግዠ
አኸ
እነግሳለሁ አለ፡፡
በማለት እየጨፈሩ ይገኛሉ፡፡‹‹እውር እውርን ቢከተል ተያይዞ ገደል›› ነውና በምስራቅም
ተማሩ በዕራብ፣ ወደ ሰሜንም አቀኑ ወደ ደቡብ ያው ‹‹ውሃ ቢወቅጡ እምቦጭ›› ሆኗል፡፡አንድ አንድ ወገኖችም ‹‹የእንትና ዘመድ…››
የሚሉት ኋላ ቀር አባባል በማስተጋባት ቡራ ከረዩ እያሉ ነው፡፡ዘሮ ዘሮ እነሱም መርዙን ቀምሷልና ምላሶቻቸው፣ብዕሮቻቸውና ብሩሾቻቸው
መርዝ ከመርጨት ወደ ኋላ አይሉም፤የኸው እንደ ሐምሌው ዶፍ እያወረዱት ይገኛሉ፡፡
የስልጣኔ ፋና ወጊ
የሶስት ሽህ ዓመታት የጥበብ አውራ
እማማ ኢትዮጵያ፡፡
የአፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት
የቀኝ ገዢዎች ወገሻ
ስራስሩን ምሰሽ፣
ቅጠላቅጠሉን ቀጥቅጠሽ
በፀበል ለቁጠሽ ስጭን የመርዙን ማርከሻ፡፡


No comments:
Post a Comment